አንድ የትምህርት ሚኒስቴር አውቶቡስ ተገልብጦ 6 ሰዎች ሞቱ

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አውቶቡሱ 40 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደብረማርቆስ በጉዞ እያለ ነበር አባይ በረሃ ውስጥ የተገለበጠው። 6 ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ 11 ሰዎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል::

ተሰፋሪዎቹ በደብረማርቆስ የሚካሄደውን የትምህርት ፊስቲቫል ለማክበር እየተጓዙ ነበር።