በሱዳን በስድስት ጎረምሶች የተደፈረችው ወጣት ክስ ተመሰረተባት

ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው እሁድ ጉዳዩዋን ለማየት የተሰየመው  ፍርድ ቤት ቀጠሮው እንዲተላለፍ ወስኗል።

ፖለስ በበኩሉ ኢትዮጵያዊቷ ወሲቡን የፈጸመችው እና በቪዲዮ እንዲቀረጽ የፈለገችው ተስማምታ ነው በማለት ዝሙት በመፈጸም ክስ  ሊመሰርት በሂደት ላይ ነው።  ፖሊስ ክሱን ለመመስረት የተነሳሳው  ወጣቷ እንደተደፈረች ወዲያውኑ ለፖሊስ ሪፖርት አላደረገችም በሚል ነው። ወጣቷ በበኩሉዋ ደፋሪዎቹ እንገድልሻለን በማለት ስላስፋሩዋት ወዲያዉኑ ሪፖርት ለማድረግ እንዳልቻለች ትገልጻለች።

በአሁኑ ጊዜ በሞርጋን እስር ቤት ውስጥ የምትገኘው ቀድሪያ እንድሪስ ነፍሰ ጡር መሆኑዋም ታውቋል። ኢሳት ሰሞኑን ቀንጭቦና በውል እንዳይለይ አደብዝዞ ያቀረበው ቪዲዮ  ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የውስጥ ምንጮች ያገኘው ነው።  አጠቃላይ ቪዲዮው የሱዳን ወጣቶች በኢትዮጵያዊቷ ወጣት  ላይ አስጸያፊ የወሲብ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ ያሳያል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ቢገባም፣ የሱዳን መንግስት ራሱን ከወቀሳ ለመከላከል ልጂቷን በዝሙት ወንጀል ለመክሰስ መነሳሳቱን መረጃውን የሚያደርሱን ወገኖች ይገልጻሉ።