ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አስቀድሞ የህዝብ ግንኙነት ስራ መሰራቱን ተከትሎ በመንግስት ሰራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የነበረው የደሞዝ ጭማሪ የታሰበውን ያክል አለመሆኑን ተከትሎ በሰራተኛው ዘንድ ቅሬታ ከፈጠረ በሁዋላ መንግስት ተጨማሪ ምርመራ ሊያደርግ መሆኑ ታውቋል። “የደሞዝ ማስተካከያ የተባለው የታለመውን የፖለቲካ ትርፍ አለማስገኘቱ ብቻ ሳይሆን በእቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ በማስከተሉና የኑሮ ውድነቱን በማባባሱ በየመድረኩ ተቃውሞ እየጋበዘ ነው በሚል ሪፖርት ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚሰጠውን ስልጠና አወገዘ
ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ” ለተማሪዎች በግዳጅ የሚሰጠውን ካድሬያዊ ስልጠና እና ትውልድን የማኮላሸት ሴራአጥብ ቀንእናወግዛለን!” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ላለፉት 23 ዓመታትህወሓት/ኢህአዴግስራዬብሎካዳከማቸውናጉዳዬከማይላቸውዘርፎችውስጥ የሚመደበውየትምህርትስርዓቱመሆኑን ገልጾ፣ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ ሲገደዱ መቆየታቸውና የኢህአዲግአባልካልሆኑምስራሊያገኙእንደማይችሉእየተነገራቸውበፍራቻለአባልነትየተመዘገቡብዙዎችእንደሆኑየአደባባይሚስጥርነው ብሎአል። በያዝነውወርበሁሉምዩኒቨርስቲዎችተማሪዎችእንዲሰበሰቡናስልጠናእንዲወስዱ፣ ስልጠናውን ያልተከታተለም መደበኛ ትምህርቱን እንደማይቀጥል ማስፈራሪያአይሉትማሳሰቢያበገዢውፓርቲበኩልመተላለፉንናተማሪዎቹበግድስልጠናውንእንዲወስዱመገደዳቸውሳያንስወደግቢከገቡበኋላ ተመልሰውመውጣትእንደማይችሉመደረጉን አስታውሰዋል። ህወሓት/ኢህአዴግይህንንስልጠናሲያካሂድም ህግንበጣሰመልኩየትምህርትማዕከላትንየፖለቲካማራመጃእናየአንድፓርቲርዕዮተ-ዓለም ማስፈፀሚያማድረጉን፣ይህንፋይዳቢስስልጠናበሁሉምዩኒቨርሲቲዎችናከ800.000 በላይለሚሆኑተማሪዎችበሚሰጥበትወቅትከፍተኛ የህዝብሀብትእያባከነመሆኑን፣ ተማሪዎችየእረፍትጊዜያቸውንበነፃነትማሳለፍሳይችሉበአስቸኳይወደዩኒቨርስቲዎችእንዲመለሱመገደዳቸው ፣ በሚሰጠውስልጠናምላይበአክራሪነትበብሔርተኝነትናበመሳሰሉትጉዳዩችሽፋንበተማሪዎችዘንድመርዛማጥላቻንእየረጨመሆኑን ሰማያዊ ፓርቲ ገልጿል። ...
Read More »በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች የአገራችን ችግሮች በስልጠና አይፈታም አሉ
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ” የመንግስትን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን ለከፍተኛ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ማስተዋወቅ” በሚል የጀመረው ስልጠና በወሎ ዩኒቨርስቲ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ተማሪዎች በአገሪቱ ውስጥ የሚታዩ በርካታ ችግሮችን እያነሱ ጥያቄዎችን እየጠየቁና አስተያየቶችንም እየሰጡ ነው። በወሎ ዩኒቨርስቲ በመካሄድ ላይ ባለው ስልጠና ተማሪዎች ኢህአዴግ እራሱን ከቀድሞ ስርአቶች ጋር ማወዳዳሩን እንዲያቆም ጠይቀዋል። ቀድሞ ስርአቶች ያልተማሩ በመሆናቸው ስህተት ቢሰሩ አይገርምም ያሉት ተማሪዎች፣ ...
Read More »ለቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባለት ጥሪ ቀረበ
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየወረዳዎች የተለጠፉት ማስታወቂያዎች ” በተለያዩ ጊዜያት በአገር መከላከያ ሰራዊት ስታገለግሉ የነበሩና በተለያዩ ጊዜያት ወደ ወረዳችን የተመለሳችሁ የሰራዊት አባላት በሙሉ የወረዳው አስተዳደርና ጸጥታ ጽ/ቤት ለመዝግባ ስለሚፈልጋችሁ እስከ ነሃሴ 21 እየቀረባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን” ይላሉ። ማስታወቂያዎቹን ለማውጣት ለምን እንዳስፈለገ ግልጽ ባይሆንም፣ መከላከያን እየከዱ የሚጠፉ የሰራዊት አባላት በመበራከታቸውና አዳዲስ ተመልማዮችም በመጥፋታቸው ምናልባትም ነባሮችን የመመለስ ስራ ለመስራት ሳይሆን ...
Read More »ለመለስ ፋውንዴሽን ሕዝብ ገንዘብ እንዲያዋጣ በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ለወራት ሲካሄድ የነበረው ከፍተኛ ቅስቀሳ ውጤት ባለማምጣቱ እንዲቆም መደረጉ ተሰማ፡፡
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዛሬውዕለት 2ኛሙትዓመታቸውበመታሰብላይየሚገኙትየቀድሞጠ/ሚኒስትርእናየኢህአዴግሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ራዕያቸውን ለማስቀጠል ይረዳል በሚል መጋቢት 28 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የመለስ ፋውንዴሽን ምስረታ በይፋ ከተበሰረ በኋላበሕዝብየሚጎበኝመናፈሻእናደረጃውንየጠበቀቤተመጻህፍትለመገንባት፣ለችግረኞችነጻየትምህርትዕድልለመስጠትየሚያስችልህንጻለመገንባት ሕዝቡገንዘብ እንዲዋያጣበቴሌቭዥን፣በራዲዮእናበጋዜጣለበርካታወራትተከታታይቅስቀሳሲደረግ ቆይቷል። ለጉዳዩቅርበትያላቸውምንጮችእንደጠቆሙትሕዝቡበተለይምየመንግሥትሠራተኛውእምቢታውንበተግባርካሳየበኋላሠራተኛውየአባይግድብን መዋጮስላለበትለ ጊዜውለመለስፋውንዴሽንተጨማሪመዋጮመጠየቅእንዲቆምከበላይአካላትትዕዛዝበመተላለፉማስታወቂውምበመንግሥት መገናኛብዙሃንመተላለፉ እንዲቆምመደረጉንአስታውሰዋል፡፡አንድበመንግሥትሥራላይየሚገኙባለሙያለዘጋቢያችንእንደተናገሩትየመንግሥትሠራተኛው ከአነስተኛደመወዙለአባይግድብ እየተቆረጠመሆኑንአስታውሰውየመለስፋውንዴሽንዕርዳታጥያቄበመ/ቤታችንበመጣጊዜሁሉምሠራተኛበአንድድምጽ «አሁንስአልበዛምወይ» ሲልምሬቱንና ቁጣውንበመግለጹየመ/ቤቱአመራሮችክፉኛበመደናገጥዳግምጥያቄውንሳያነሱመቅረታቸውንአስታውሰዋል፡፡ “ሠራተኛውበከፋየኑሮውድነትእየተገረፈ፣በዚህላይ ደግሞለቦንድግዥወዶም፣ሳይወድምደመወዙእየተቆረጠባለበትበዚህወቅትሌላዙርመዋጮጨርሶ የሚሰማበትጆሮ፣የሚሸከምበትትከሻየለውም፣በዚህምክንያትመዋጮየመሰብሰብዕቅዳቸውድጋፍአላገኘም”ሲሉተናግረዋል፡፡ ፋውንዴሽኑመጋቢት 28 ቀን 2005 ዓ.ምበተመሰረተበትዕለትማምሻውንበሸራተንሆቴልበተካሄደየገንዘብማሰባሰብሥነሥርዓትባለሃብቶችንናየጎረቤትአገራትን ድጋፍሳይጨምርከክልሎችብቻከ74 ሚሊየንብርበላይመሰብሰቡይታወሳል፡፡ በወ/ሮአዜብመስፍንየሚመራውፋውንዴሽኑከተመሠረተአንድዓመትተኩልገደማቢያስቆጥርምእስካሁንገንዘብከመሰብሰብ፣የመሠረትድንጋይከማስቀመጥናችግኝ ከመትከልየዘለለሥራአለማከናወኑን ምንጮች ጠቅሰዋል። እስካሁን በግዴታ ከሰራተኛው ...
Read More »በጎንደር ዩኒቨርስቲ በግቢ ጽዳት ሰበብ ከፍተኛ ገንዘብ እየተመዘበረ መሆኑን የዩንቨርስቲው ሰራተኞች አጋለጡ፡፡
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት የገዢውመደብየፓርቲአባላትእናአመራሮች ቀድም ብሎ የግቢውንጽዳት ሲያከናውኑ የነበረውን ድርጅት በማባረር እና የራሳቸውን ድርጅት በማቋቋም ከዚህ ቀደም በወርይከፈልከነበረው 150 ሽህብርላይ 350 ሺህብርበመጨመርዩንቨርስቲውለጽዳት ብቻበየወሩከ500 ሺህብርበላይእንዲያወጣበማድረግበአራትወርውስጥ 1.4ሚሊዮንብርለግልጥቅማቸውአውለዋል። በዚህግቢውስጥየሚሰራውጽዳትስራከመጀመሪያዎቹስምንትወራትጀምሮ ውል ተቀብሎሲሰራበቆየውድርጅትእናአሁንበዩንቨርስቲውአመራሮችየሚሰራውስራምንም ዓይነትልዩነትአለመታየቱን ፣ በፊትምምንምዓይነትየጽዳትጉደለትእንዳላዩበማጽዳትስራውላይተሰማርተውበመስራትላይያሉሰራተኞች፣ፕሮክተሮችእናተማሪዎች በተደረገላቸውቃለመጠየቅተናግረዋል፡፡ በማጽዳትስራውያሉተቀጣሪሰራተኞች፣ፕሮክተሮችእናተማሪዎችየተከሰተውስራአሳዛኝእናሆንተብሎየራስን ጥቅም ለማጋበስ የታሰበበትመሆኑንተናግረዋል፡፡ በጽዳትስራውምንምዓይነትየአደረጃጀትምሆነጽዳትዕቃዎች የአቅርቦትልዩነትሳይኖርይህንየተጋነነክፍያተመካክረውበመውሰድ የጽዳትስራውንሲሰራየነበረውንድርጅትከጨዋታውጭበማድረግለኪሳራመዳረጋቸውትክክል አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ስማቸውንመግለጽያልፈለጉየዩኒቨርስቲውነባርየአስተዳደርሰራተኞችእንደተናገሩትጉዳዩለዩኒቨርስቲውከፍተኛአመራሮችበተደጋጋሚቀርቦላቸው ነገዛሬ በሚልቸልበማለትችግሩንሳይፈቱትየበጀትአመቱመጠናቀቁ፣ ሆንተብሎየተወሰኑግለሰቦችእንዲጠቀሙየተተወየአደባባይሚስጥርመሆኑን መታዘባቸውንና በዩኒቨርስቲው ከፍተኛአመራሮችአሰራርማፈራቸውንበምሬትተናግረዋል፡፡ የጽዳትስራውንሲሰራየነበረውንድርጅትባለቤትለማነጋገርበሞከርንበትጊዜየድርጅቱባለቤት የጽዳቱንስራበሚከታተለውየአስተዳደርዘርፍየተያዘበትንከ500 ሽህብርበላይለማስለቀቅለሦስትወራትሲመላለስከቆየበኋላበቅርቡለዚሁስራሲንቀሳቀስበደረሰበትየመኪናአደጋበሁለትእግሮቹእናበቀኝእጁላይ በደረሰ ከፍተኛአደጋበጎንደር ...
Read More »የአዲስ አበባ ፖሊሶች ለስልጠና እንዲከቱ ተደረገ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በኮልፌ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ከተጠናቀቀ በሁዋላ መደበኛ ፖሊሶች ደግሞ በተለያዩ የማሰልጠኛ ቦታዎች በግዳጅ ገብተው ስለመንግስት ፖሊሲና እቅድ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው። በኮልፌ በአዛዥ ፖሊሶች ሲጠየቁ የነበሩት ጥያቄዎች በመደበኛ ፖሊሶች ተጠናክረው መቅረባቸው ታውቋል። ከትናንት ጀምሮ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ግንቦት 20 እየተባለ በሚጠራው ትምህርት ቤት ውስጥ 500 የሚደርሱ ፖሊሶች ገብተዋል። እያንዳንዱ ፖሊስ ...
Read More »በምስራቅ ሃረርጌ ከፍተኛ ረሃብ ተከሰተ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የምስራቅ ኢትዮጵያ ወኪል እንደዘገበው በምስራቅ ሃረርጌ ኦሮምያ ቆላማ ክፍል በሚገኙ ግራዋ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ፣ ፈዲስ ፣ ሚዲጋ እና ሚደጋ ቶላ ወረዳዎች የተከሰተው ረሃብ አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር ህዝቡን ለስደት ሊያደርገው ይችላል። ባለፈው እሁድ 50 የሚሆኑ የወረዳው ህዝብ ተወካዮች ሀረር ከተማ በመግባት አቤቱታቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ ተወካዮቹ ህዝቡ አንድ ጊዜ ነቅሎ ከመሰደዱ በፊት መንግስት ...
Read More »የአቶ መለስ የመቃብር ቦታ ላለፉት 2 አመታት በወታደር በመጠበቅ ላይ መሆኑ ታወቀ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ዘጋቢ በቦታው ተገኝቶ ያነሳቸው ፎቶዎች ወታደሮች ከመቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው ሲጠብቁ ያሳያል። መቃብሩ ለምን መጠበቅ እንዳስፈለገ ግልጽ የሆነ ነገር የለም። የአንድ ሰው መቃብር በወታደሮች በእየቀኑ እንዲጠበቅ ሲደርግ ይህ በአለም ታሪክ የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም በማለት ዘጋቢያችን አስተያየቱን ገልጿል። የመለስ 2ኛ የሙት አመት በመላ አገሪቱ በሚገኙ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ዘንድ እንዲዘከር እየተደረገ ነው። በአዲስ አበባም ...
Read More »በቁጫ ወረዳ የታሰሩት ፍትህ አጥተው እየተሰቃዩ መሆኑን ተናገሩ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ ከታሰሩ በርካታ ወራትን ያስቆጠሩት የአገር ሽማግሌዎች ፍትህ አጥተው እየተሰቃዩ መሆኑን ገልጸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ የወረዳ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳታቸው እና የጸጥታ ሃይሎች የሃይል እርምጃ መውሰዳቸውን ለጠ/ሚኒስትሩና ለሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በማመልከታቸው መታሰራቸው ይታውቃል። ከ400 ያማያንሱት እስረኞች ዛሬ ነገ እንፈታለን ብለው ተስፋ ቢያደርጉም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚችል ባለስልጣን ...
Read More »