ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን ተሻግረው በሽበርተኝነት የተፈረጀውን የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ሲሉ ማይካድራ ላይ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ያላቸውን እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል። ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የቀረቡት በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ መዝገብ የተካተቱት አራት ተከሳሾች ብርሃኑ ...
Read More »በጭልጋ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ከ5 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ከተማ የፌደራል ፖሊሶች በወዱት እርምጃ ከ5 እስከ 6 የሚደርሱ ወጣቶች መገደላቸውን፣ ከ10 ያላነሱ ወጣቶች ደግሞ መቁሳላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል። የቅማንት ተወላጆች የራስ አስተዳደር መብት ይሰጠን በሚል ላቀረቡት ጥያቄ ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት “ጥያቄያቸው በክልሉ ውስጥ እንደሚገኙት እንደ ሌሎች ብሄረሰቦች ሊታይላቸው” ይገባል የሚል ውሳኔ አሳልፏል። ጥያቄ ...
Read More »በሊቢያ በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትሪፖሊ አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት ሰሞኑን እንደ አዲስ በተጀመረው አፈሳ ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች ከ500 ያላነሱ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙም ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ የተያዙት በህወጥ አዘዋዋሪዎች ሲሆን፣ ገንዘብ ካላመጡ እንደማይለቀቁ እንደሚነገራቸው ገልጸዋል፡፡ አንድ ከእስር ቤት ያመለጠ ወጣት ሲናገር፣ በእስር ቤቱ ውስጥ ዱላ የቀን ተቀን ህይወት ነው፣ ...
Read More »ፍርድ ቤቱ በዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ ለብይን ቀጠሮ ሰጠ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፣ ልደታ ምድብ ሰኔ 8/2007 ዓም በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ላይ በቀረበው የሽብረተኝነት ክስ ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥቁር ለብሰው ፍርድ ቤት የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም በቀረበለት የቪዲዮ ማስረጃ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። አቃቤ ህግ ...
Read More »በግል ድርጅቶች የተቀጠሩ ስራቸውን በገፍ እየለቀቁ ነው
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፕሮቪደንት ፈንድ ያላቸውን የግል ድርጅት ሠራተኞችን ገንዘብ በመውሰድ በጡረታ እንዲተዳደሩ ለማድረግ የተረቀቀው የግል ድርጅቶች ማህበራዊ ዋስትና አዋጅ ማሻሻያ በበርካታ ሰራተኞች ዘንድ ተቃውሞ ማስከተሉን ተከትሎ በተለይ ፕሮፌሽናል ባለሙያዎች የግል ድርጅቶችን በገፍ እየለቀቁና ለመልቀቅ የመልቀቂያ ደብዳቤ እያቀረቡ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት እየተሰራበት ያለው አዋጅ ቁጥር 715/2003 ለማሻሻል በምርጫው ማግስት ለፓርላማው የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ከሰኔ ...
Read More »ምርጫ በሁዋላ ኢትዮጵያዉያን ሌሎች የትግል አማራጮችን እየፈለጉ እንደሆነ ዘጋርዲያን ዘገበ
ኢሳት ዜና (ሰኔ 4 2007 ዓም) የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማፈኑን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲዎች “ ቅድሚያ ለነጻነት ” ወደሚል ትግል ማዘንበላቸውን የእንግሊዝ ዘ-ጋርዲያን ጋዜጣ ሐሙስ ለንባብ ባበቃው እትሙ ዘገበ። ገዢው የኢሃዴግ መንግስት በቅርቡ በተካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በብቸኝነት ለድል መብቃቱም በመንግስት ላይ ጥያቄ ያላቸው አካላት ሌሎች አማራጮችን እንዲመለከቱ ማስገደዱንም ጋዜጣው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዙሪያ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል። በቅርቡ ...
Read More »አልሸባብ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ እንደዘገበው በማእከላዊ ሶማሊያ በተደረገው ጦርነት ታጣቂ ሃይሉ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታውቋል። ጃሚዮ በተባለ መንደር የሚኖሩ ነዋሪዎች በሁለቱ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት መካሄዱንና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ሲተኮሱ መስማታቸውን ተናግረዋል። አልሸባብ አገኘሁት ያለውን ድል በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተበባለ ነገር የለም። ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሆርሲድ ሚዲያ እንደዘገበው ደግሞ የአልሸባብ ተዋጊዎች የኢትዮጵያ የመከላከያ ...
Read More »የፌደራል ጸረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣኖችን ሃብት ይፋ ለማድረግ ወኔው አንሶታል ተባለ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን የመንግስት ተሿሚዎችን፣ ተመራጮችንና የመንግስት ሠራተኞች ሃብት የመመዝገብ ሥራዎችን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እያከናወነ ቢሆንም ባሉበት ጫናዎች ምክንያት መረጃውን ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ አለመቻሉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ኮምሽኑ የባለስልጣናትን ሀብት እንዲመዘግብ ስልጣን ሲሰጠው በመንግስትና በሕዝብ መካከል መተማመን ይፈጥራል ተብሎ ነው፣ ይሁን እንጅ ኮምሽኑ የባለስልጣናቱን ሃብት ምዝገባ ከማካሄድ በስተቀር ...
Read More »60 የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ለ3 ቀናት ግምገማ አካሄዱ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀናት በደብረ ዘይት ከተማ በተካሄደው ግምገማ ባለስልጣኖቹ እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመገምገሚያ ነጥቦቹ “አመራሮቹ በየምርጫ ምደባቸው የነበራቸው ውጤታማነትና ውስጣዊ ስኬት፤ በተቋማቸው የነበረው የኪራይ ሰብሳቢነት ትግልና የተመዘገበ ውጤት፣ እንዲሁም ግለሰባዊ ድክመታቸው ” የሚሉ ሲሆኑ፣ በግምገማውም ባለስልጣኖቹ ከኤ እስከ ዲ ያሉ ውጤቶችን አግኝተዋል። በህወሃት አባላት የሚመሩ ተቋማት ...
Read More »በምርጫው ሰሞን ቀንሶ የነበረው የእህልና የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ተመልሶ እየናረ ነው
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት15 ምርጫ ከመካሄዱ 2 ሳምንት በፊት መንግስት ዋና ዋና የሚባሉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ እንዲቀንስ ቢያደርግም ፣ ከምርጫው በሁዋላ ተመልሶ መውጣቱን ዘጋቢያችን ገልጿል። ምስር በኪሎ ከ50 ብር በላይ፣ በርበሬ ከ120 ብር በመሸጥ ላይ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ዘይትና ስኳር ተመልሰው ከገበያ መጥፋታቸውን የስጋና የወተት ምርቶች እንዲሁም በሁሉም የእህል ዘሮች ላይ ጭማሪ መታየቱን ዘግቧል። የመንግስት ...
Read More »