ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ምስራቃዊ አካባቢዎች በዝናብ እጥረት ለረሃብ የተጋለጡ አርሶአደሮች በዚህ ችግር ላይ እያለን በአካባቢው አመራሮች ግብር እንድንከፍል በመገደዳችን ከፍተኛ ችግር ላይ ነን በማለት ተናገሩ፡፡ በድርቁ የተጎዱት አካባቢ የሚኖሩ የመንግስት ሠራተኞች በተለይ ለኢሳት ሲናገሩ ‹‹ የዝናቡ እጥረት እንዳለ ሆኖ መንግስት ለአርሶ አደሮች ግብአት አላቀረበም፡፡አርሶ አደሩ በዚህ ዓመት የሚቀምሰው አንዳች ነገር በእጃቸው ሳይኖር ግብር ...
Read More »በኮንሶ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ውጥረቱ ቀጥሏል
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ሰገን ዞን የኮንሶ ወረዳ ሕዝብ በዞን ደረጃ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር መጠየቁን ተከትሎ የክልሉ መንግስት ልዩ ታጣቂ ኃይል ወደአካባቢው በማስገባት ነዋሪዎችን በማሰር፣ በመደብደብ እና በማስፈራራት ላይ ይገኛል። የዞኑ ባለስልጣናት ሕዝቡ ተሰብስቦ የዞን ይሰጠን ጥያቄ አላቀረብንም በማለት እንዲያወግዝ በማስጨነቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትየመብት ጥያቄው አንቀሳቀሾች ናቸው የተባሉ የወረዳውን ፖሊስ አዛዥ ጨምሮ የተለያዩ ...
Read More »ለ6 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከ150 ሚሊዮን ብር ባላነሰ ገንዘብ የግል መኖሪያ ቤት እየተሰራላቸው ነው
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለከፍተኛ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት መኖሪያ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 25 ሚሊየን ብር የሚያወጡ፣ 6 ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች በአዲስ አበባ ሲኤምሲ አካባቢ ከፍተኛና ምቹ ቦታ ተመርጦ እየተገነቡላቸው መሆኑን የፌዴራል መንግሥት ቢሮዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተክለጻድቅ ተክለአረጋይን ለ ሸገር ኤፍ ኤም 102 ተናግረዋል። የሕንጻ ግንባታ ስራቸው በመጠናቅ ላይ ያሉት እነዚህ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ...
Read More »በጂንካ በተካሄደው ቤት የማፈራረስ ዘመቻ በርካታ ዜጎች መጠለያ አልባ ሆኑ
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ አርኪሻ ቀበሌ ኬላ መንደር ነዋሪዎች ቤቶቻቸዉ በዶዘር እንዲፈርስ በመደረጉ ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸዉንና በእሪታና ለቅሶ መንገድ በመዝጋት ጥቅምት 25፣ 2008 ከሰዓት በኃላ በማሰማታቸዉ ልዩ ኃይልና ፖሊስ ለመበተን ሲሞክሩ ቦታ እየቀያየሩ ተቃውሞአቸውን እስከ ምሽት ሲያሰሙ ቆይተዋል። ጥቅምት 27ትም እንዲሁ ቤት ማፍረሱም ተቃዉሞዉም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ ፎቶ ለማንሳት የሚሞክሩትን ካሜራና ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ዞን የልዩ ሃይል አባላት ከህዝቡ ጋር እየተታኮሱ ነው
ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ በተለይ በማውራ የተጀመረው በህዝብ እና በክልሉ ልዩ ሃይል መካከል የተፈጠረው ግጭት ወደ ታጭ አርማጭሆ የተዛመተ ሲሆን፣ አርሶ አደሩ ከልዩ ሃይሎች ጋር ባደረጉት ተኩስ እስኩን በትንሹ ከ10 ያላነሱ የልዩ ሃይል አባላት ሲገደሉ፣ ከአርሶ አደሮች ደግሞ 6 የሚሆኑት ተገድለዋል። 9 የሚሆኑ የልዩ ሃይል አባላትም ቆስለዋል። የፌደራል ፖሊስ ...
Read More »በአማራ ክልል በየጊዜው የሚካሄደው የመከላከያ ሰራዊት ምልመላ እንዳልተሳካ ተገለጸ፡፡
ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የገዢው መንግስት የውስጥ ችግሩን በሰለጠነ አካሄድ ከመፍታት ይልቅ በጦር ኃይሉ ቁጥርና የመሳሪያ ብዛት ለማስፈራራት የጀመረውን አካሄድ ከማጠናከር በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች እየሞከረ ያለው የሰራዊት ምልመላ እንዳልተሳካ የድርጅቱ የቀድሞ ታጋዮችና ተሰናባች የሰራዊቱ አባላት በተለይ ለኢሳት ተናገሩ፡፡ ከድርጅቱ ጋር በመወገን ደርግን ለመጣል በተደረገው ትግል ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉት ተሰናባች የሰራዊቱ አባላት እንደተናገሩት ረዢምና መራራ ...
Read More »ኢህአዴግ በራሱ አባሎች ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው
ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በነሃሴ ወር በመቀሌ ከተማ በተካሄደው የግንባሩ 10ኛ ጉባዔ፣ የአባላት ጥራት ጉዳይ አሳሳቢ ሆናል ካለ በሁዋላ በቅርቡ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በግንባሩ ከፍተኛ አመራር ክትትል የሚደረግበት ይህ አፈጻጸም ከላይ አስከታች ድረስ ባሉ መዋቅሮቹ የሚገኙትን ወደ 7 ሚሊየን ይጠጋሉ የተባሉ የግንባሩን አባላት በመገምገም እርምጃ ይወስዳል ተብሎአል፡፡ እንደምንጫችን ገለጻ ከሆነ በዚህ ሒደት እጅግ ...
Read More »በቦረና ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ
ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ የዞኑን ሰብሳቢ ጠቅሶ እንደዘገበው በገላና ወረዳ የወረዳውን ሰብሳቢ አቶ በድሉ መንግስቱን ጨምሮ 10 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታስረዋል።ጥቅምት 24/2008 ዓ.ም የታሰሩት የድርጅቱ አባላት ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንና በቤተሰብም አለመጎብኘታቸውን ዘግቧል። የወረዳው ሰብሳቢ አቶ በድሉ መንግስቱ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚደርሳቸው ለፖሊስ ሲያመለክቱ ቢቆዩም ምንም ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል።
Read More »አርቲስት ደበበ እሸቱ በምርጥ ተዋናይነት ተሸለሙ
ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ቀያይ ቀምበጦች በሚለው ፊልም ላይ ባሳየው የተዋናይነት ብቃቱ በካናዳ ቫንኩቨር የGolden Leopard Award ተሸላሚ ሆኗል። አርቲስት ደበበ ሽልማቱን በተወካዩ በኩል ተቀብሏል። የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተሩ ኢትዮዽያዊዉ ቤተ እስራኤላዊዉ ባዚ ጌቴ ሲሆን፣ ፕሮዲዩሰሩ ደግሞ ኢላድ ፔሌግና የእስራኤል የፊልም ስራ ማዳበሪያ ቢሮ ናቸው። በተለያዩ የእስራኤል ከተሞች የተሰራውን ፊልም ለማዘጋጀት ...
Read More »የሶማሊያ የፓርላማ አባል የኢትዮጵያ ጦር መኖር ግጭቶችን እንዳባባሰው ተናገሩ
ጥቅምት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፍሪካ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጦር ስር ካሉት ሰራዊቶች ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሚገኝበት ጌዶ አውራጃ ውስጥ በሚፈጽማቸው ዘግናኝ ግፎች ምክንያት በአካባቢው ነዋሪዎች እንደማይፈለግና ለአገራቸው ሰላም ማጣት የኢትዮጵያ ጦር ተጠያቂ ነው ሲሉ የሶማሊያ ፌዴራል ፓርላማ አባል ማህመድ አሊ መጋን አስታወቁ። የኢትዮጵያ ጦር ድብቅ ዓላማ ይዞ በጌዶ ግዛት የፖለቲካ ልዩነቶችን በማስፋት ነዋሪዎቹ እርስበርስ ...
Read More »