ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ የመንገድ ባለስልጣን መስሪያ ቤት በመንገዶች ዳርቻ ያሉ ዓመታዊ ግብር ተከፍሎባቸው የቆሙ ቢልቦርድ የንግድ ማስታወቂያዎችን ለድርጅቶቹ ምንም ዓይነት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ተለዋጭ ቦታ ሳይሰጣቸው ሳይሰጣቸው ከተለጠፉበት ማንሳቱን ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል። ንብረታቸው የተወሰደባቸው የከተማዋ ነዋሪዎች እንደዚህ ዓይነት ሕገወጥ ድርጊት በሕግ ሽፋን መፈፀሙ እንዳስከፋቸው እየገለፁ ነው። የመንገድ ባለስልጣኑ በበኩሉ በሬድዮ ለሶስት ቀናት ማስታወቂያ ...
Read More »ኦህዴድ ማስተር ፕላኑ እንዲቆም ውሳኔ አስተላለፈ
ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2008) የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞኖች የተቀናጀ ማስተር ፕላን እንዲቆም ውሳኔ አሳለፈ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ለሶስት ቀናት በአዳማ ተሰብስቦ ማስተር ፕላኑ እንዲቆም መወሰኑን በገለጸበት ማግስት ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን፣ ግድያም ቀጥሎ ዛሬ አምቦ ከተማ አንዲት ህጻን ስትገደል ሌላ ህጻን ቆስላለች። በድሬደዋና በአምቦ ዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞ መቀጠሉ ተመልክቷል። በምዕራብ ሃረርጌ በቀጠለው ተቃውሞ ደግሞ 23 ተማሪዎች ተይዘው መታሰራቸው ...
Read More »በአማራ ክልል ከመልካም አስተዳደር ችግር ጋር በተገናኘ 200 የሚጠጉ አመራሮች ከስልጣን ተነሱ
ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2008) በአማራ ክልል ከመልካም አስተዳደር ጋር በተገናኘ በህብረተሰቡ ላይ ችግር ፈጥረዋል የተባሉ ወደ 200 የሚጠጉ አመራሮች ከስልጣን ተነሱ። በክልሉ በሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎች እንዲሁም ቀበሌዎች ውስጥ በተለያዩ መንግስት ሃላፊነት በማገልገል ላይ የነበሩት እነዚሁ ሃላፊዎች ከአመራርነታቸው እንዲነሱ ከተደረጉ በኋላ ጉዳያቸው ወደህግ መወሰዱንም ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ከተደረጉት መካከል 90 የሚሆኑንት በድርቅ ለተጎዱት ሰዎች የሚሰጥ ድጋፍን ...
Read More »በሃረማያ ዩንቨርስቲ የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ በአጎራባች ቀበሌዎች ተዛመተ
ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2008) ሰኞ በሃረማያ ዩንቨርስቲ የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ በአካባቢው መዛመቱንና በአካባቢው ውጥረቱ አለመርገቡን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የዩንቨርስቲው አስተዳደር ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቢያቀርብም ተማሪዎቹ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በምስራቅ ሃረርጌ አካባቢ ባሉ ከተሞች ረቡዕ ተመሳሳይ ተቃውሞ ሲያካሄዱ ያረፈዱ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ከፍተኛ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ መሆኑም ታውቋል። ተቃውሞው በአዲስ መልክ ቀጥሎ ...
Read More »ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የጸጥታና የደህንነት ሃላፊዎች በናዝሬት ከተማ ተሰበሰቡ
ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ በርካታ ከተሞች ዳግም የተቀሰቀሰውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ተከትሎ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ከፍተኛ የጸጥታና የደህንነት ሃላፊዎች በናዝሬት አዳማ ከተማ ሃገር አቀፍ ምክክር ጀመሩ። በዚሁ በሶስት ቀናቶች በሚቆየው ሃገር አቀፍ የጸጥታ ምክክር ከ200 በላይ የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች እንዲሁም ከፍተኛ የጸጥታ ስራ ሃላፊዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በአይነቱ የመጀመሪያው ነው በተባለው በዚሁ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደው ስላለው ተቃውሞ ከዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ማብራሪያ ጠየቀ
ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በህብረቱ ዋና መቀመጫ ብራሰልስ ከተማ ተገኘተው በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ስላለው ተቃውሞ ማብራሪያን እንዲሰጡ ጠየቀ። ሆኖም የተዘጋጀላቸውም ጋዜጣዊ መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተሰርዟል። የቀረበላቸውን ጥያቄ ተከትሎ በብራሰልስ የሚገኙት ዶ/ር ቴዎድሮስ በጉዳዩ ዙሪያ ከህብረቱ አባል ሃገራት በርካታ ጥያቄዎች ይቀርብላቸዋል ተብሎ በመጠበቅ ላይ መሆኑን ...
Read More »ኦህዴድ ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ ቢልም ተቃውሞ ግን ቀጥሎአል
ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ አንድ ክንፍ የሆነው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መተውን ባስታወቀ ማግስት በአምቦ፣ በአርሶ ኬፈሌና በሌሎችም የኦሮምያ ክፍሎች ተቃውሞው ቀጥሎአል። በአምቦ የተካሄደው ተቃውሞ ደም አፋሳሽ የነበረ ሲሆን፣ አንድ ሰው መገደሉና በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል። ከቆሰሉት መካከል ህጻናትም ይገኙበታል። ከአምቦ ከተማ በተጨማሪ በ ጃርሶ ወረዳ ቀሬ ጎሓ ...
Read More »የወልቃይትን ህዝብ ትግል የሚያስተባብሩ ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች እየተዋከቡ ነው
ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “የወልቃይት ሕዝብ አማራነቱ ይከበርለት” በማለት ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ በፌዴራልና በአማራ ክልል እየቀረቡ አቤቱታ ሲያሰሙ የነበሩ የኮሚቴ አባላት ወደአካባቢቸው በሰላም ለመመለስ መቸገራቸው ታውቋል። “የወልቃት ሕዝብ አማራ ነው፣ በትግራይ ክልል ሊተዳደር አይገባም” በማለት ጥያቄ ያነሱት ተወላጆች፣ የትግራይ ክልል አሁንም ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖችን በተናጠልና በጋራ በማጥቃትና በማሳደድ ስራ በመጠመዱ ምክንያት የኮምቴ አባላቱ ያለስጋት ...
Read More »በቀን ከ150 በላይ ኢትጵያዊያን ከአገራቸው ይሰደዳሉ ተባለ
ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ውስጥ አብዛሃኞቹ በእድሜ ወጣቶች ሲሆኑ፣ በጾታ ስብጥር ደግሞ በመቶኛ ሲሰላ 94 ከመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከላካይ ኮሚቴ በሂልተን ሆቴል ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ለፍልሰቱ ዋናው ምክንያት ሥራ አጥነትንና ሕገወጥ ደላሎችን በምክንያትነት አቅርቧል። ወላጆች ተበድረው ለደላላ በመክፈል ልጆቻቸውን ወደ ውጭ ሀገራት እንደሚልኩ ...
Read More »ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ 760 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ያስፈልጋል ተባለ
ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው የእርዳታ መጠን ከ760 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ መድረሱን መንግስት ማክሰኞ ባቀረበው የእርዳታ ጥያቄ አስታወቀ። አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በበኩላቸው ለምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎች በቀጣዮቹ ሶስት ወራቶች ውስጥ ድጋፍ ካልጀመሩ ችግሩ የከፋ እንደሚሆን በድጋሚ አሳስበዋል። ከ10 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተረጂዎች የእርዳታ ጥሪን ያቀረቡ ...
Read More »