ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በሁለት የአኝዋክና ንዌር የመንግስት ባለስልጣናት መካከል የተነሳው ጸብ ወደ ብሄረሰብ ግጭት በማምራቱ የከተማዋና አካባቢው ነዋሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በከተማዋ ውስጥ እንደልብ መንቀሳቀስ አለመቻሉን የገለጹት ነዋሪዎች፣ እስካሁን ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ ለማወቅ አለመቻሉን ገልጸዋል። በከተማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የመንግስት መስሪያቤቶች ተዘግተዋል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማዋ ቢሰማሩም ግጭቱን ሊያስቆሙት አለመቻላቸውንም ነዋሪዎች ...
Read More »በሃዋሳ ከተማ ያሉ የበረንዳ ዳስ ሱቆች ካለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንዲፈርሱ እየተደረገ ነው
ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ዋና ከተማ ሃዋሳ በተለምዶ አረብ ሰፈር አሮጌ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የበረንዳ ዳሶችን ካንድ ቀን በፊት ብቻ ማሰጠንቀቂያ በመስጠት አፍራሽ ግብረ ኃይል በማሰማራት ሕገወጥ ግንባታ በሚል ሱቆቹን ማፍረሱ ቀጥሏል። ሕጋዊ የቫትና ቲኦቲ ግብር ከፋይ የሆኑት ነጋዴዎች ሁኔታውን በመቃወም ተቃውሟቸውን ቢገልፁም፣በአፀፋው የክልሉ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን በመደብደብ አካላዊ ጉዳት ...
Read More »በኢትዮጵያ አንድ አምስተኛ የሚሆነው ሕዝብ ለረሃብ ሊጋለጥ ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ
ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በአሳሳቢ የርሃብ አደጋ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በሚቀጥሉት ወራት አደጋው በእጥፍ እንደሚጨምር ቅድመ ጥናቶች አረጋግጠዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ግብረሰናይ የረድኤት ተቋማት በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ከተከሰተው የርሃብ አደጋዎች በኢትዮጵያ ያለው ርሃብ አድማሱን በማስፋቱ ከአጠቃላይ የአገሪቱ ሕዝብ ውስጥ አንድ አምስተኛ የሚሆነው ወይም ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ በርሃብ አደጋ ውስጥ ...
Read More »በአፍሪካ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እየተባባሰ መምጣቱ ተገለጸ
ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ተከትሎ አጠቃላይ በአሃጉሩ የሸቀጥ ዋጋ እየናረ ነው። የአፍሪካ ሕብረት የኤኮኖሚ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ሞንታይ እንዳሉት የሸቀጦች ዋጋ መውረድ፣ የዶላር የወለድ መጠን በአሜሪካ መናር፣ አሳሳቢ ድርቅና የጎርፍ አደጋዎች በሃጉሪቱ ያለውን ምጣኔሃብታዊና ማኅበራዊ ችግሮች ይበልጥ አባብሰውታል ። ዶ/ር አንቶኒ “ችግሩ በመባባሱ ምክንያት የስራ አጡ ቁጥር እየጨመረ፣ የኑሮ ...
Read More »በሰሜን ጎንደር በማንኛውም ጊዜ ግጭት ሊነሳ ይችላል ሲሉ ነዋሪዎች አስጠነቀቁ
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ ፈጥሮታል በሚባለው በአማራና ቅማንት የሰሜን ጎንደር ተወላጆች መካከል ያለው ግጭት ለጊዜው ጋብ ያለ ቢመስልም፣ ድጋሜ ግጭት ለማስነሳት ውስጥ ለውስጥ የቅስቀሳ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አንዱ በሌላው ላይ የሚያካሂደው የማጥላላት ዘመቻ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በዚሁ የቅስቀሳ ስራ ላይ የኢህአዴግ ሹሞች ሙሉ በሙሉ እጃቸውን ማስገባታቸው ታውቋል። ...
Read More »በኮንሶ የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ነው
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንሶ ህዝብ ራሱን ችሎ በዞን እንዲተዳደር ያቀረበው ጥያቄ ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች ለእስር ከተዳረጉ በሁዋላ አሁንም አካባቢው በልዩ ሃይል ፖሊሶች እንደተከበበ መሆኑን ነዋሪዎች ከስፍራው ገልጸዋል። የልዩ ሃይል አባላት ከጥያቄው ጀርባ አርበኞች ግንቦት7ቶች አሉበት በማለት ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎች፣ አሁን ደግሞ ” ጥያቄው የእኛ አይደለም” ብላችሁ ፈርሙ በማለት በግድ ...
Read More »የውጭ ምንዛሬ እጥረት ማዳበሪያ በበቂ እንዳናስገባ አግዶናል ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእር ሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በውጪ ምንዛሪ ችግር ምክንያት ለእርሻ ግብአት የሚውል ማዳበሪያ በበቂ መጠን መግዛት እንዳልተቻለ ለፖርላማው ገልጸዋል፤፡ ለመስኖና እና ለበልግ እርሻ ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶአደሩ እንዲቀርብ ለማድረግ 832 ሺህ 400 ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ለመግዛት ታቅዶ በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር ጋር ተያይዞ በመተማመኛ ሰነድ (ሌተር ኦፍ ክሬዲት) ...
Read More »መንግስት በረሃቡ ላይ የያዘው አቋም የአለማቀፍ መንግስታት ተወካዮችን ግራ እያጋባ ነው
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በያዝነው ፈረንጆች አመት ከ15 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ለርሃብ የተጋለጠ መሆኑ እየታወቀ በመንግስት በኩል ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተደርጎ የሚሰጠው መግለጫ በለጋሽ አገራት ዘንድ ብዥታ መፍጠሩን የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ተናግረዋል። ስማቸው እንደይገለጽ የገለጹ የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንዳሉት በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የሚሊዮኖችን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉ በገሃድ እየታየ ቢሆንም፣ መንግስት ችግሩን ...
Read More »ባለፈው አመት በምስራቅ አፍሪካ ጭቆናው ተባብሶ መቀጠሉን ሂውማን ራይትስ ወች ገለጸ
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው የሰአብዊ መብት ድርጅት ባወጣው ዘገባ የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት የሰብአዊ መብት አያያዞችን ለማሻሻል ያደረጉት ጥረት አነስተኛ መሆኑንና በአንዳንድ አገሮች ተባብሶ የቀጠለበት ሁኔታ እንደነበር ገልጿል። ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ በተወሰነ መጠን ደግሞ ዩጋንዳ ሃሳብን በማፈን፣ የሰዎችን የመሰብሰብ ነጻነት በመንፈግ እንዲሁም ከምርጫ በፊትና በሁዋላ በሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ቀዳሚዎች ሆነዋል። ሩዋንዳ የተቃውሞ ሃሳቦች እንዳይስተናገዱ ...
Read More »ኢንሳ የአየር ላይ ፎቶ በማንሳት ላይ የሚገኘው ለሱዳን ተሰጥቷል የሚባለውን አልፋሽጋ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ መሆኑ ታወቀ
ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ጥር ወር መግቢያ ጀምሮ የአየር ላይ ፎቶ እየተነሳ ያለው አካባቢ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ” ኢትዮጵያ መሬቱ የእኛ መሆኑን እውቅና ሰጥታለች” በማለት ለአልጀዚራ የተናገሩት አልፋሽጋ እየተባለ የሚጠራው ቦታ መሆኑ ታውቋል። ትናንት ኢሳት የመረጃና ደህንነት ኢንፎረሜሽን ባለሙያ በማናገር በሰራው ዘገባ ላይ በአሁኑ ሰአት የአየር ላይ ፎቶ ለማንሳት ምልክቶችን መሬት ላይ የማስቀመጡ ...
Read More »