(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 16/2011) በአፍሪካ ሕብረት ጽሕፈት ቤት ውስጥ የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ አጼ ሃይለስላሴ ሐውልት ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለጸ። ለአፍሪካ ሕብረት ምስረታ ከፍተኛ ሚና ተጫውተው ሳለ አስተዋጽኧቸው ግን መዘንጋቱና የክዋሜ ንክሩማህ ሐውልት ብቻ መቆሙ ብዙዎችን ያነጋገረ ነበር። በአፍሪካ ሕብረት ምስረታም ሆነ የአፍሪካ ሃገራት ከቅኝ ግዛት ለመውጣት በሚያደርጉት ትግል በኢትዮጵያ መሪነታቸው ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ንጉስ ሃይለስላሴ ሐውልታቸው በአፍሪካ ሕብረት ጽሕፈት ቤት ...
Read More »የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ስልጣን ለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 16/2011) የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት ስልጣናቸውን ለቀቁ። አዲስ ፕሬዝዳንትም ተሰይሟል። በአዲስ አበባ ለአንድ ሳምንት ግምገማ ሲያደርግ የቆየው የጋምቤላ ክልል ገዢ ፓርቲ በገዛ ፈቃዳቸው የለቀቁትን ሊቀመንበሩንና ምክትላቸውን በሌሎች መተካቱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበርና የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ጋትሉዋክ ቱትና ምክትላቸው አቶ ሰናይ አኩዎር ይቅርታ ጠይቀው በለቀቁበት የአዲስ አበባው ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መገኘታቸውን ለማወቅ ...
Read More »አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዝዳንት በመሆን ተሰየሙ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 15/2011) አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት በመሆን በዛሬው እለት ተሰየሙ። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው ስነ ስርአት የኢፌዴሪ 4ኛ ፕሬዝዳንት የሆኑት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዲፕሎማትነት የረዥም አመታት ልምድ አዳብረዋል። ከንግስት ዘውዲቱ ወዲህ የመጀመሪያዋ እንስት ርዕሰ ብሔርም ሆነዋል። በ1942 አዲስ አበባ ከተማ የተወለዱትና የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሊሴ ገብረማርያም ትምህርት ቤት የተከታተሉት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ከፍተኛ ትምህርታቸውን በፈረንሳይ ሞንተሌ ዩኒቨርስቲ ተከታትለዋል። ...
Read More »በዜጎች ላይ በየትኛውም መንገድ የሚወሰደው የሃይል ርምጃ ተቀባይነት የለውም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 25/2011) አስተዳደራዊና የማንነት ጥያቄዎችን በሚያነሱ ዜጎች ላይ በየትኛውም መንገድ የሚወሰደው የሃይል ርምጃ ተቀባይነት የለውም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ አወጣ። ፓርቲው ዛሬ በአዲስ አበባ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የአዲስ አበባ ነዋሪን የመደራጀት መብት እንዲከበር፣ የራያ የማንነት ጥያቄ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጠው፣ በሀረር በስርዓት አልበኞች ርምጃ ነዋሪው ላይ ለተጋረጠው አደጋ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቋል። በንጽሃን ዜጎች ላይ የኃይል ርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ...
Read More »የአሰቦት ገዳም መነኮሳት የድረሱልን ጥሪ አሰሙ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 15/2011)በምዕራብ ሐረርጌ ሜኤሶ ወረዳ የሚገኘው የአሰቦት ገዳም መነኮሳት የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው ተባለ። በታጣቂዎች ተከበናል፣ለቃችሁ ውጡ ተብለናል፣ የሚደርስልን የለም የሚሉት የገዳሙ መነኮሳት በተኩስ ድምጽ ተሸብረናል በማለት ለኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ አቅርበዋል። ከጥቅምት ሰባት ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ከፍተኛ ማዋከብ እየተፈጸሙ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል። የሜኤሶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከታጣቂዎቹ ጎን በመሆን ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ መነኮሳቱ ላይ ...
Read More »የራያ ተወላጆች በአላማጣና ቆቦ መንገዶችን ዘጉ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 17/2011) የራያ ተወላጆች በትግራይ ልዩ ሃይል አፈሳው መቀጠሉን በመቃወም በአላማጣና ቆቦ መንገዶች መዝጋታቸው ተገለጸ። በተለይ ወደ መቀሌ የሚወስዱ መንገዶችን በድንጋይና በግዙፍ እንጨቶች በመዝጋት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዲገታ መደረጉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የራያ እናቶች ታፍሰው የተወሰዱ ልጆቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ ላይ ናቸው። የትግራይ ክልል መስተዳድር በራያ ላይ እየወሰደ ያለውን ርምጃ በመቃወም ለፊታችን እሁድ በጎንደር ሰልፍ ተጠርቷል። በሌላ በኩል የማንነት ጥያቄዎች እየቀረቡ ...
Read More »የአፋር ልዩ ሃይል የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉ ወጣቶች ላይ ጉዳት አደረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 25/2011) በአዋሽ ሰባተኛ የአፋር ልዩ ሃይል የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸሙ ተገለጸ። በአፋር ክልል የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ በቀጠለበት በዚህን ወቅት ልዩ ሃይሉ አዋሽ ሰባተኛ ላይ የወሰደው ርምጃ ቁጣን ቀስቅሷል። በርካታ ወጣቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአይን እማኞች ገልጸዋል። የአፋርን ክልል የሚመራው ፓርቲ ለውጥ አደናቃፊ ነው በሚል በክልሉ በአብዛኛው አከባቢ የተጀመረው ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ህወሃት በአፋር ክልል ...
Read More »በምስራቅ ሃረርጌ አወዳይ ውጥረት ተከሰተ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 15/2011)በምስራቅ ሃረርጌ አወዳይ ውጥረት መከሰቱ ተገለጸ። ከሀረር ከተማ መግባትና መውጣት እንዳልተቻለም ዘግይቶ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በአወዳይ የተከሰተው ግጭት በአካባቢው ባሉ ስርዓት አልበኞች ከተወሰደ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ ጋር የተያያዘ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል። ከሃረር፣ ድሬዳዋና ወደሌሎች አካባቢዎች ለመንቀሳቀስ እንዳልቻሉ መንገደኞች ለኢሳት ባደረሱት የጽሁፍ መልዕክት ላይ ገልጸዋል። ከሃረር አወዳይ መንገድ ላይ የሚንቀሳቀሱ የህዝብ ማመላለሺያ አውቶብሶችን የሚያስቆሙት ስርዓት አልበኞች ተሳፋሪዎች ላይ እንግልት ...
Read More »የሰገን ዞንን እንደገና ለማዋቀር የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ ነዋሪዎች ነቀፋም ድጋፍም እየገለጹ ነው
የሰገን ዞንን እንደገና ለማዋቀር የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ ነዋሪዎች ነቀፋም ድጋፍም እየገለጹ ነው ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ/ም ) የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን በ2003 ዓ/ም ኮንሶ፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ሰገን ከተማ/ጉማይዴ/፣ ቡርጂ እና አሌን በማጣመር ከተመሰረተ በሁዋላ አልፎ አልፎ የተቃውሞና የግጭት ማዕከል ሆኖ ቆይቷል። በተለይ የኮንሶ ህዝብ በዚህ ዞን ስር ለመቀጠል ፈቃደኛ ባለመሆኑ፤ የተለያዩ ተከታታይ ተቃውሞዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። ከ2008 ...
Read More »በዴር ሱልጣን በግብጽ የሃይማኖት መሪዎችና በእስራዔል ፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 14/2011)በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሱልጣን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እንዳይታደስ በከለከሉ የግብጽ የሃይማኖት መሪዎችና በእስራዔል ፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ። እድሳቱን ለማከናወን ወደ ቤተክርስቲያኑ ሊገቡ የነበሩ ሰራተኞችን የግብጽ ጳጳሳትና መነኮሳት ክልከላ ማድረጋቸውን ተከትሎ የእስራዔል ፖሊስ ርምጃ ወስዷል። ከአንድ ዓመት በፊት ጣሪያው የተደረመሰውን የኢትዮጵያ ገዳም ለማሳደስ ከፍተኛና እልህ አስጨራሽ ትግል መካሄዱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያን ይዞታ ለመንጠቅ በየጊዜው ሙከራ የሚያደርጉት ግብጻውያን ገዳሙ እንዳይታደስ ...
Read More »