የቂሊንጦ ታሳሪዎች እጣ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን፣የቤተቦቻቸውን ደህንነት ለማወቅ ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት የሄዱ የታሳሪ ቤተሶቦች በታጣቂዎች ድብደባ፣ እንግልትና ማዋከብ ተፈጸመባቸው።

ነሃሴ  ፴ ( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ከስፍራው እንደዘገበው የእስርቤት ኃላፊዎቹ ትናንት ወደ ቂሊንጦ የሄዱ የታሳሪ ቤተሰቦችን “ ሁኔታውን እስከማክሰኞ ድረስ እናሳውቃችኋለን” ብለው የነበረ ቢኾንም፣ የልጆቻቸው፣ የአባቶቻቸው፣ የባለቤቶቻቸው፣ የእህቶቻቸው፣ የወንድሞቻቸውና የወዳጆቻቸው ሁኔታ አላስችል ብሏቸው ዛሬ ወደዚያው ሲያቀኑ “ እስከ አርብ ድረስ ጠብቁ” ተብለዋል። ይህም ሳይበቃ ታጣቂዎቹ የእስረኞችን ቤተሰቦች በመስደብ፣ በመገፍተር፣ በማዋከብና ዱላ በመጠቀም እንዲበተኑ አድርገዋል። ...

Read More »

በደቡብ ጎንደር እብናት ከተማ ሕዝቡ የራሱን አስተዳደር መሰረተ

ነሃሴ  ፴ ( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እየተቀጣጠለ የመጣው ሕዝባዊ እቢተኝነት አድማሱን በማስፋት በእብናት እና አርባያ ከተሞች ጨምሮ በአጎራባች የገጠር ገበሬ ማኅበራት ሕዝቡ የጎበዝ አለቃዎች በመምረጥ የራሱን አስተዳደር መስርቷል። የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች ራሳቸውን በማደራጀት ከተማዋን ተቆጣጥረው አስተዳዳሪዎቻቸውን ከመምረጣቸውም በተጨማሪ በግፍ የታሰሩ ወጣቶችን  አስፈትተዋል። በከተማዋ ምንም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴ የሌለ ሲሆን የመንግስት ቢሮዎችን ጨምሮ የግል ድርጅቶች ዝግ ሆነው ሕዝቡ በቤት ውስጥ ተቀምጧል። ከዚህም ሌላ  አቅም ለሌላቸው ዜጎችና የጎዳና ተዳዳሪዎች ገንዘብ በማዋጣት ነጋዴዎችና ወጣቶች አስተዋጾ እያደረጉ እንደሆነ ተገልጻል። ወጣቶቹ እብናትን ከሌሎች ከተማዎች የሚያገናኙ አውራ ጎዳናዎችን በመዝጋት እራሳቸውን ከጥቃት በመከላከል ላይ ናቸው። የገዥው ፓርቲ ታጣቂዎች ሙሉ ለሙሉ ከከተማዋ ተጠራርገው የወጡ ሲሆን፤  ሕዝቡ ካሁን በኋላ በህወሃት ኢህአዴግ አስተዳደር አንገዛም ሲል የአቋም መግለጫ ማውጣቱም ታውቋል።

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ የተጠቀመው መጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ አስመልክቶ ግልጽና ገለልተኛ የሆነ ምርመራ እንዲደረግ ዩናይትድስቴትስ አሣሰበች

ነሃሴ  ፴ ( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ ውስጥ በተቃዋሚዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው አደገኛ እርምጃ መንግስታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ማሣሰቡንና  በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ እንዲደረግ  መጠየቃቸውን በተመድ የአሜሪካ ቋሚ መልዕክተኛና የፕሬዚዳንት ኦባማ ካቢኔ አባል የሆኑት አምባሳደር ሳማንታ ፓወር በጁባበሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። አምባሳደር ሳማንታ ፓወር  ትናንት ከቀትር በኋላ በሰጡት በዚሁ መግለጫቸው የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት  ልኡካን በደቡብ ሱዳን ያደረጉትን  ጉብኝት ማጠናቀቃቸውን በመጥቀስ  በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ከአፍሪካ ህብረት ባለሥልጣናት ጋር ለመወያዬት ዛሬ ሰኞ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያቀኑ ገልጸዋል። ሳማምታ ...

Read More »

በደሴና በኮምቦልቻ ወጣቶች እየታሰሩ ናቸው

ነሃሴ  ፴ ( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ  ከቀትር በኋላ በደሴ ከተማ የተጀመረውን የሥራ ማቆም አድማ ለማደናቀፍ የጸጥታ ኃይሎች በግዳጅ አንዳንድ የንግድ ተቋማትን ማስከፈት ጀምረዋል። ከዚህም ባሻገር  ሕዝባዊ እቢተኝነቱን ያስተባብራሉ የተባሉ ወጣቶች በተናጠል እየታሰሩ መሆናቸው ታውቋል። የከተማዋ ነጋዴዎች የማዋከብና የማስፈራራት ሰለባ ቢሆኑም  የደሴ ከተማ  የፀጥታ ድባብ ውስጥ መወደቋን ምንጮቻችን አስታውቀዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኮምቦልቻ የተቃውሞ ጥሪ መደረጉን ተከትሎ ሹመኞች ሰሞኑን ነጋዴዎችን እና የመንግስት ሰራተኞችን ሰብስበው አስፈራርተዋል። አርብ ዕለትም  በከንቲባው ጽ/ቤት የዞንና የወረዳ ባለሥልጣናትና  ከነጋዴዎች ጋር የተሰበሰቡ ሲሆን፤ ከንቲባው ደነቀ ምትኩና ም/ከንቲባው አቶ አዲሱ ነጋዴዎችን በግልጽ አስፈራርተዋል። ስብሰባው “ድርጅቶቻችሁን ብትዘጉ ንግድ ፈቃዳችሁን እንቀማለን፣ እርምጃ እንወስዳለን” በሚለው የከንቲባዎቹ ዛቻ ቢጠናቀቅም፤ ህብረተሱቡ በተለይም ወጣቱ የለውጥ ጥያቄውን ሊያቆም ባለመቻሉ ትናንት እሁድ ምሽት  የከተማዋ ወጣቶች በታጣቂዎች እየታፈሱ ተወስደዋል። በከተማዋ አውቶቡስ መናኸሪያ አካባቢም እሳት መነሳቱን ተከትሎ ትናንት ምሽቱን ከተማዋ ሙሉ በሙሉ ...

Read More »

በአማራና ኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ አድማሱን አስፍቶ እንዲቀጥል ተጠየቀ

ኢሳት (ነሃሴ 27 ፥ 2008) በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት አድማሱን አስፍቶ ወደ ተለያዩ አነስተኛ የገጠር ቀበሌዎች ድረስ በተዳረሰበት በአሁኑ ወቅት፣ በሌሎች የክልሉ ዞኖች የሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች የህዝባዊ እምቢተኝነት አድማ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ። በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል በጎንደር እና በጎጃም በሁሉም ከተሞችና የገጠር መንደሮች በአጋዚ ወረራ የታፈነውን ህዝብ ...

Read More »

ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአለም እርሻና ምግብ ድርጅት (FAO) አስታወቀ

ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአለም እርሻና ምግብ ድርጅት (FAO) አስታወቀ ኢሳት ( ነሃሴ 27 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ ብዙ መሻሻል ባለማሳየቱ፣ አሁንም ድረስ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን እርዳታ ፈላጊ መሆናቸውን የዓለም ምግብ ድርጅት (FAO) በዚህ በነሃሴ ወር ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ። የዓለም ምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎቶችን አስመልክቶ ሰፊ ሪፖርት ባወጣው በዚህ በነሃሴ ወር ...

Read More »

ህዝባዊ ተቃውሞ አድማሱን አስፍቶ እንዲቀጥል ተጠየቀ

ኢሳት (ነሃሴ 27 ፥ 2008) በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች የተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት አድማሱን አስፍቶ ወደ ተለያዩ አነስተኛ የገጠር ቀበሌዎች ድረስ በተዳረሰበት በአሁኑ ወቅት፣ በሌሎች የክልሉ ዞኖች የሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች የህዝባዊ እምቢተኝነት አድማ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ። በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል በጎንደር እና በጎጃም በሁሉም ከተሞችና የገጠር መንደሮች በአጋዚ ወረራ የታፈነውን ህዝብ ...

Read More »

በመላ ሀገሪቱ እየቀጠለ ባለው ተቃውሞና እየተወሰደ ባለው የኅይል እርምጃ ዙሪያ የተጠናከረ ሪፖርታዥ

ነሃሴ  ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር ዞን በደራ ወረዳ በአርብ ገበያ በአርሶ አደሮችና በመከላከያ አባላት መካከል የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ነው። የግጭቱ ምክንያት ትናንት ምሽት ከእስቴይ ወረዳ 90 ኩንታል ጤፍ ጭኖ የመጣ የጭነት መኪና አርብ ገበያ ሲደርስ በህዝብ እንዲቆም ከተደረገ በኋላ ወደ መጣበት እንዲመለስ በመደረጉ ነው « ህዝቡ ከእንግዲህ ጤፍም ሆነ ሌላ ማናቸውም ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን አይሁዶች ከሌሎች እስራዔላውያን በበለጠ በወንጀል ድርጊት መጠርጠራቸው ትክክል ነው ሲሉ የእስራኤል ፖሊስ ኮሚሽነር ተናገሩ

ኢሳት (ነሃሴ 26 ፥ 2008) የእስራዔል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽነር የኢትዮጵያ ዝርያ ያላቸው አይሁድ-ኢትዮጵያውያን ከሌሎች አይሁዶች በበለጠ በወንጀል መጠርጠራቸው ትክክል ነው ብለው መናገራቸው ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ። ፖሊስ አዛዡ አይሁድ ኢትዮጵያውያን በወንጀል ድርጊት መጠርጠራቸው ትክክል መሆኑን የተናገሩት በአንድ ትልቅ ስብሰባ ላይ ተጋብዘው በተናገሩበት ወቅት ነው። የእስራዔል ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ሮኒ አልሼይች በእስራዔል በሚኖሩ አይሁድ ኢትዮጵያውያን ላይ በምን ምክንያት የእስራዔል ፖሊስ እርምጃ እየወሰደ ...

Read More »

በኮንሶ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ስራ ማቆማቸው ተነገረ

ኢሳት (ነሃሴ 26 ፥ 2008) የደቡብ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓም የኮንሶ ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ውድቅ መደረጉን የሚግልጽ ደብዳቤ መጻፉን ተከትሎ፣  በወረዳዋ የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆማቸው ተነገረ። የኮንሶ ህዝብ ከ50 ሺ በላይ ፊርማ አሰባስቦ/ ባለበት ልዩ ወረዳ ሆነው እንዲቀጥሉ አለዚያም ወደ አንድ ራሱን የቻለ ዞን እንዲያድጉ አቅርበው የነበረ ...

Read More »