ኮለኔል ጋዲሳ ጉማ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)የመጀመሪያውን የአየር ሃይል አውሮፕላንን ከሲውዲን ወደ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሶስት ኢትዮጵያውያን ጋር እያበረሩ የገቡት ኮለኔል ጋዲሳ ጉማ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የበረራ ትምህርትን የተከታተሉትና የመጀመሪያ የአብራሪ ክንፍ ያገኙት ኮለኔል ጋዲሳ ጉማ የቀዳማዊ ሃይለስላሴ የክብር ተሸላሚም ነበሩ። 35 አመታትን በአየር ሃይል ውስጥ ያገለገሉት ኮለኔል ጋዲሳ በክብር በጡረታ ከተሸኙ በኋላ በሌላ ዘርፍ ሀገሬን ላገልግል በማለት በተለያዩ ...

Read More »

ታዋቂው ገጣሚና ጋዜጠኛ ሰለሞን ደሬሳ ከዚህ አለም በሞት ተለየ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)ታዋቂው ገጣሚና ጋዜጠኛ እንዲሁም የፍልስፍና መምህር ሰለሞን ደሬሳ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ሰለሞን ደሬሳ ከዚህ አለም በ80 አመቱ በሞት የተለየው በስደት በሚኖርባት አሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ሚኒያፖሊስ ከተማ ነው። ልጅነት፣ዘበት እልፊቱ ወለሎታትና የናይጄሪያው ጸሃፊ ወሌ ሾዬንካ ስብስብ ስራዎችን ጨምሮ 3 መጽሀፍትን ለአንባቢያን ያበረከተው ሰለሞን ደሬሳ የአንድ ልጅ አባት ነበር። ገጣሚና ጋዜጠኛ እንዲሁም የፍልስፍና መምህር የነበረው ሰለሞን ደሬሳ የተወለደው በ1930 ...

Read More »

የኢሳት 7ኛ አመት የምስረታ በአል በፔንሲልቫንያ ፊላዴልፊያ ከተማ ተካሄደ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)የኢሳት 7ኛ አመት የምስረታ በአል ከፍተኛ ገቢ በማሰባሰብ በፔንሲልቫንያ ፊላዴልፊያ ከተማ ተካሄደ። በዝግጅቱ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታድመው በኢትዮጵያ ሕዝቡ እያካሄደ ላለው የነጻነት ትግል ኢሳት እያደረገ ያለውን ድጋፍ በማድነቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ በማከናወን ከፍተኛ ገንዘብ አበርክቷል። በታሪካዊቷ የአሜሪካ ፊላዴልፊያ ከተማ በተዘጋጀው በዚሁ ስነስርአት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ ኤርሚያስ ለገሰ፣ጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸውና ድምጻዊ ሻምበል በላይነህ ናቸው። በዝግጅቱ ላይ ለታዳሚዎች ...

Read More »

በዶክተር መረራ ጉዲና ላይ የአቃቢ ህግ ምስክሮች ተሰሙ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)በኦፌኮ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ላይ የአቃቢ ህግ ምስክሮች ተሰሙ። ዶክተር መረራ እጃቸውን በብረት ካቴና እንዳይታሰሩ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት የአቤቱታ ደብዳቤ ይፋዊ ምላሽ አላገኘም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመተላለፍ የወንጀል ክስ የቀረበባቸው የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና የእምነት ክህደት ቃላቸውን ጥቅምት 6/2010 በሰጡበት ወቅት ድርጊቱን አልፈጸምኩም፣ጥፋተኛም አይደለሁም ማለታቸውን ተከትሎ አቃቢ ህግ ምስክሮችን ለጥቅምት 24/2010 አቅርቦ እንዲያሰማ ፍርድ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ህዝቡን እያማረረ መሆኑ ተሰማ።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010) በኢትዮጵያ የተከሰተው የኑሮ ውድነት ህዝቡን እያማረረ መሆኑ ተሰማ። ኢሳት ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በመደወል ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት የኑሮ ውድነቱ የመኖር ህልውናቸውን አደጋ ውስጥ ከቶታል። በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የዕለት ጉርሳቸውን መሸመት አቅቷቸው አደጋ ውስጥ መውደቃቸውን ነው የተናገሩት። በሌላ ዜና በሀዋሳ ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ምሬት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። ከዋጋ ግሽበትና ከብር የመግዛት አቅም መቀነስ ጋር በተያያዘ ...

Read More »

በኮሬና ጉጂ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች መካከል ተከስቶ የነበረው ግጭት መቀጠሉ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)በኮሬና ጉጂ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች መካከል ተከስቶ የነበረው ግጭት መቀጠሉ ተነገረ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በደቡብና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች በወሰን ማካለል ሰበብ የአካባቢው ባለስልጣናት ያቀናበሯቸው ግጭቶች ለአያሌ ዜጎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። በደቡብ ኮሬና በጉጂ ኦሮሞዎች መካከል በተከሰተው ግጭት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለከፍተኛ ስቃይና ችግር መዳረጋቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል። የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት ለዘመናት ተከባብረው፣ተዋደውና ተዋልደው ይኖሩ የነበሩት ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦን የሙስና ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)በቅርቡ ከፖሊሲ ምርምርና ጥናት ተቋም ምክትል ሃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ስራቸውን የለቀቁት አቶ በረከት ስምኦን የሙስና ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በተለይም በ300 ሚሊየን ብር ወጪ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ደብል ትሪ ባለ አራት ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል የርሳቸውን ነው በሚል ምርመራ ተጀምሯል። በአቶ በረከት ላይ የተጀመረው ምርመራ ሌሎች አሏቸው የተባሉና በግለሰቦች ስም የተያዙ ንብረቶችንም እንደሚጨምር ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሰራተኞች በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 23/2010) የሕወሀትን የግፍ አገዛዝ ለማስወገድ የኢትዮጵያ ሰራተኞች በጋራ እንዲቆሙ በስደት የሚገኙ የቀድሞ ማህበራት መሪዎች ጥሪ አቀረቡ። በአሁኑ ጊዜ ያለው ትልቁ አጀንዳ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ማዳን እንጂ በሰራተኛ ሕጉ ላይ አንቀጾችን የማስተካከል ጉዳይ እንዳልሆነ የቀድሞ የሰራተኛ መሪዎች ባወጡት መግለጫ አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በቅርቡ የሰራተኞች መብትን የሚመለከተውን አዋጅ በመቃወም የስራ ማቆም አድማ ለመጥራት ማቀዱን መግለጹ ይታወሳል። የቀድሞው የሰራተኛ ...

Read More »

የካታላን መሪዎች ዛሬ ስፔን ማድሪድ ፍርድ ቤት ቀረቡ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 23/2010)ካታላንን ከስፔን በመገንጠል ነጻ ሀገር መሆኗን ያወጁት የካታላን መሪዎች ዛሬ ስፔን ማድሪድ ፍርድ ቤት ቀረቡ። ከፕሬዝዳንቱ ጋር ወደ ቤልጂየም ከተሰደዱት 6 ሚኒስትሮች ሁለቱ ወደ ስፔን መመለሳቸው ታውቋል። ፕሬዝዳንቱን ጨምሮ አራቱ ሚኒስትሮች ተላልፈው እንዲሰጡት የስፔን መንግስት ይጠይቃል ተብሎም እየተጠበቀ ነው። የካታላን ምክትል ፕሬዝዳንት ኦሪዮ ጆንኩራስን ጨምሮ ዛሬ ማድሪድ ብሔራዊ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የካታላን ከፍተኛ ባለስልጣናት በእምነት ማጉደል፣በመንግስት ላይ በማመጽና ...

Read More »

የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበር አቋርጠው ሶማሊያ መግባታቸው ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 23/2010) ከባድ መሳሪያ የታጠቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበር አቋርጠው ሶማሊያ መግባታቸው ታወቀ። ለቪኦኤ የሶማሌኛው አገልግሎት ምስክርነታቸውን የሰጡ የዶሎ ከተማ ነዋሪዎች እንደተናገሩት አውቶማቲክ መሳሪያዎች በተጠመደባቸው ፒካፖች ታጅበው የሶማሊያን ድንበር አቋርጠው የገቡት የኢትዮጵያ ወታደሮች በቁጥር አንድ ሺ ይገመታሉ። በትንሹ በ30 ተሽከርካሪዎች ተጭነው ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ድንበር አቋርጠው ሶማሊያ የገቡት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአልሻባብ ላይ የሶማሊያ መንግስት ለመክፈት ላቀደው መጠነ ሰፊ ...

Read More »