(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010)ከሞያሌ በሳምንቱ መጀመሪያ የተሰወሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መክዳታቸውን ምንጮች ለኢሳት አረጋገጡ። የከዱት የሰራዊቱ አባላት ቁጥርም 38 እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል። እነሱን ለመፈለግ የወጣው ሃይልም አለመመለሱ ታውቋል። ሆኖም ለአሰሳ በወጣው ሃይል ውስጥ በተፈጠረ ውዝግብ አንድ ወታደር ሲገደል አንድ መቁሰሉን ምንጮቹ ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው የኦሮሞ ተወላጅ ወታደሮች መሆናቸውም ተመልክቷል። በሳምንቱ መጀመሪያ ከሞያሌ ተነስተው ለአሰሳ የወጡት ወታደሮች ከ24 ሰአታት በላይ መሰወራቸውን ተከትሎ ...
Read More »የኦሮሚያ ክልል የሜቴክን ህገወጥ ድርጊት ማስቆሙን አስታወቀ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010) የኦሮሚያ ክልል ውሃ ሃብት ቢሮ ሜቴክ ከክልሉ የድንጋይ ከሰል በማውጣትና በመሸጥ ሲያከናውን የነበረውን ህገወጥ ድርጊት ማስቆሙን አስታወቀ። ቢሮው “ህገ ወጥ የሆነ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር በድብቅ ቢፈጸምም ከብዙሃኑ ህዝብ እይታ ግን ፈጽሞ ሊሰወር አይችልም” በሚል ባወጣው መግለጫ ሜቴክን ብቻ ሳይሆን የክልሉን ሃብት በመዝረፍ የተሰማሩ አካላት ላይ የምወስደውን ርምጃ እቀጥላለሁ ብሏል። የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/በሕግ ከተቋቋመበትና ከተሰጠው ...
Read More »በመከላከያ አመራር ላይ ከፍተኛ ብወዛ እየተደረገ ነው
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 15/2010) በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ በመከላከያ አመራር ላይ ከፍተኛ ብወዛ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ። ብወዛው በተለይ የኦሮሞና አማራ ተወላጆች ላይ የተነጣጠረ መሆኑንም ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በጄኔራል መኮንኖች አካባቢ አመራሩ በሕወሃት ጄኔራሎች በመያዙ ብወዛው ከዚያ በመለስ ባለው የስልጣን መዋቅር ላይ ማተኮሩ ተመልክቷል። በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ በተጠናከረው ብወዛ በቅድሚያ የተሸጋሸጉ የ12 መኮንኖች ዝርዝር ለኢሳት ደርሶታል። በዚህም መሰረት ኮለኔል አበራ ለማ፣ኮለኔል ...
Read More »አመታዊው የምስጋና ቀን ተከብረ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010)አመታዊው የምስጋና ቀን/ታንክስ ጊቪንግ/ዛሬ በአሜሪካኖች ዘንድ ተከብሮ ዋለ። በአሜሪካ የሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያንም ሁኔታና አቅም በፈቀደ መጠን በአሉን ያከብራሉ። በአሜሪካውያኑ ዘንድ በያመቱ በህዳር ወር 4ኛው ሀሙስ ላይ የሚከበረው የምስጋና ቀን/Thanksgiving/ ምስጋና የሚሰጥበትና ቤተሰብና ጓደኛ ሰብሰብ ብሎ የሚያከብረው ቀን ነው። በአሜሪካና ካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ሁኔታው እንደፈቀደላቸው ሰብሰብ ብለው ያከብሩታል። በአሉ በካናዳ ባለፈው ወር ተከብሯል። በአሉ በካሪቢያን ደሴቶችና በአፍሪካም በላይቤሪያ እንደሚከበር ...
Read More »አንድ ኢትዮጵያዊ በካናዳ ዊኒ ፔግ የ5 አመት አስራት ተፈረደበት
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010)የንግድ አጋሩን ለማስገደል ተንቀሳቅሷል በሚል የተወነጀለው ኢትዮጵያዊ በካናዳ ዊኒ ፔግ የ5 አመት አስራት ተፈረደበት። በፖለቲካ ጥገኝነት በካናዳ የሚኖረው አቶ አማረ ገብሩ እስራቱን ሲጨርስ ከሀገር እንደሚባረርም ይፋ ሆኗል። ይህን ቤተሰቡን ያስደነገጠውን የማባረር ርምጃ ለማስቀረትም ጠበቆች እስራቱን በይግባኝ ለማስቀነስ በመሯሯጥ ላይ መሆናቸውን የካናዳው ሲ ቲ ቪ ኒውስና ዊኒ ፔግ ፍሪ ፕሬስ በዘገባቸው አመልክተዋል። አቶ አማረ ገብሩ ስሟ ካልተጠቀሰው የ31 አመት ...
Read More »ለኢትዮጵያ የአባይ ጉዳይ የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010) የአባይ ጉዳይ ለእኛም የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለጹ። ቃል አቀባዩ አቶ መለስ አለም የአባይ ግድብን በተመለከተ ከግብጽ ጋር ውጥረት መከሰቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ኢትዮጵያ በራሷ አቅም አባይን መገደቧን ትቀጥላለች። የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በቅርቡ አንድ የአሳ ፋብሪካን ሲመርቁ አባይ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው ማለታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው የአባይ ግድብ ...
Read More »የአሜሪካ የኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ባለስልጣን ርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 14/2010) የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሆቴሎችና በልዩ ልዩ ቦታዎች አገልግሎት በሚሰጡ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የአሜሪካ የኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ባለስልጣን ርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን አስታወቀ። በዋናነት በአሰሪዎቹ ላይ ያነጣጠረውና ተቀጣሪዎቹንም የማይተወው ርምጃ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ክስ መመስረትንም ይጨምራል። ተቀጣሪዎቹ ደግሞ በሌላ ወንጀል የሚፈለጉ ካልሆነ በቀር ከአሜሪካ እንዲባረሩ ይደረጋል ብሏል ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ። በግዙፎቹ የንግድ ተቋማት ላይ የተነጣጠረ ነው የተባለው የአሜሪካ የኢሚግሬሽንና ...
Read More »በሞያሌ የተሰወሩትን ወታደሮች ፍለጋ ቀጥሏል
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 13/2010)በሞያሌ ከትላንት በስቲያ የተሰወሩትን ወታደሮች ለመፈለግ የወጣው አሳሽ ቡዳን ዛሬም ፍለጋውን መቀጠሉ ተገለጸ። ከ30በላይ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ከተሰወሩ በኋላ በ10ኛው ክ/ጦር ባሉ ወታደሮች ዘንድ ውጥረት ነግሷል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የሬዲዮ መገናኛ ኦፕሬተር መታሰሩን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ወታደሮቹ ከተሰወሩ በኋላ በክ/ጦሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ በሆኑ የሰራዊቱ አባላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንንም ለማወቅ ተችሏል። ከትላንት በስቲያ ሰኞ ነው። በ10ኛ ...
Read More »የዚምባቡዌ አዲስ ፕሬዝዳንት አርብ ቃለ ማሃላ ይፈጽማሉ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 13/2010)የዚምባቡዌ አዲስ ፕሬዝዳንት የፊታችን አርብ ቃለ ማሃላ እንደሚፈጽሙ ታወቀ። ሀገሪቱን ለ37 አመታት የገዙት ሮበርት ሙጋቤን ከስልጣን መልቀቅ ተከትሎ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ኤመርሰን ናንጋግዋን በፕሬዝዳንትነት ለመሾም ዝግጅት እየተደረገ ነው። ዚምባቡዌን ለ37 አመታት የመሩት ሮበርት ሙጋቤ ትላንት ከስልጣን መልቀቅን ተከትሎ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑትና ከሁለት ሳምንት በፊት በሙጋቤ በሙጋቤ ከስልጣኝ ተወግደው የነበሩት ኤምርሰን ናንጋግዋ በፕሬዝዳንትነት እንደሚሾሙ ከሀገሪቱ የሚወጡ መረጃዎች ...
Read More »መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመንግስት ትላልቅ ፕሮጀክቶች በብቸኝነት ሲሚንቶ እያቀረብኩ ነው አለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 13/2010)መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመንግስት ትላልቅ ፕሮጀክቶች በብቸኝነት ሲሚንቶ ማቅረብ የቻልኩት ልዩ ሲሚንቶዎችን በብቸኝነት የማመርት በመሆኔ ነው አለ። የኤፈርት ኩባንያ አካል የሆነው መሶቦ ሲሚንቶ ለግዙፍ ፕሮጀክቶቹ በብቸኝነት እንዲያቀርብ የተደረገው ግዙፉ የሙገር ሲሞንቶ ፋብሪካ በህወሃት ስርዓት በተለያየ መንገድ የማምረት አቅሙ እንዲዳከም ከተደረገ በኋላ መሆኑ ይታወቃል። በህወሃት ንብረትነት የሚተዳደረው ኤፈርት ኩባንያ አካል የሆነው የመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በ2009 ብቻ በኢትዮጵያ ለተከናወኑ የፕሮጀክት ...
Read More »