(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 6/2010) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ መቀጠሉ ታወቀ። የደህንነቱ ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንዲፈርስ ጠይቀዋል። ብአዴንና ኦህዴድ ራሳችሁን አጥሩ በሚል በሕወሃት የቀረበው ሃሳብም ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። ይህ ከፍተኛ ውዝግብ ያስከተለው ስብሰባ ሸምጋዮች እንዲገቡበት የቀረበው ሃሳብም ውድቅ ተደርጓል። ስብሰባው ረዥም ጊዜያትን እንደሚወስድም ተገምቷል። ሆኖም ስብሰባው ሳያልቅ የማረጋጊያ መግለጫ በቀጣዮቹ ቀናት ይወጣል ተብሎም ...
Read More »በመላው የኦሮሚያ አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) የጨለንቆውን ጭፍጨፋ በመቃወም በመላው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። ተቃውሞው አዲስ አባባ ዙሪያ መድረሱንም ለማወቅ ተችሏል። በወለጋ ጊምቢና ነጆ፣ በጂማ በአጋሮና በአብዛኛው የምስራቅ ሀረርጌ ከተሞች ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል። በሞያሌ በአጋዚና በህዝቡ መሃል ግጭት ተፈጥሯል። በአምቦ የተገደሉ የአጋዚ ወታደሮች ቁጥር መጨመሩም እየተነገረ ነው። ዛሬ በኦሮሚያ ክልል የተካሄዱትን ተቃውሞች በተመለከተ የተዘጋጀውን ዝርዝር ዜና ብሩታዊት ግርማይ ታቀርበዋለች ባለፈው ሰኞ ...
Read More »ህዝባዊው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ህዝባዊ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። በአይከል ከተማ ህዝቡ አደባባይ በመውጣት የህወሃትን አገዛዝ ማውገዙ ታውቋል። በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ ናቸው። ህወሀት ከስልጣን እንዲወርድ ተማሪዎቹ ጠይቀዋል። በጎንደር ዩኒቨርስቲ ዛሬም ትምህርት አልተጀመረም። አንድ የመንግስት ተሸከርካሪ ዩኒቨርስቲው ደጃፍ ላይ ወድሟል። በወልዲያ ከ70በመቶ በላይ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወተዋል። በኡርጌሳ ወሎ ህዝቡ ከአጋዚ ሰራዊት ጋር እንደተፋጠጠ መሆኑ ታውቋል። ...
Read More »ዚምባቡዌ መንግስቱ ሃይለማርያምን አሳልፌ አልሰጥም አለች
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) ዚምባቡዌ የቀድሞ የኢትዮጵያን ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሐይለማርያምን አሳልፋ እንደማትሰጥ አስታወቀች። የዚምባቡዌ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባለፈው ወር ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ ሀገሪቱ መንግስቱ ሃይለማርያምን ወደ ሀገራቸው እንድትሰድ በመጎትጎት ላይ ናቸው። የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ሃይለማርያም አጋርና ወዳጅ የሆኑት ሮበርት ሙጋቤ አሁን በስልጣን ላይ ባይሆኑም ዚምባቡዌ ኮለኔል መንግስቱን አሳልፋ እንደማትሰጥ አንድ የሀገሪቱ ባለስልጣን ማረጋገጫ ሰጥተዋል። የዚምባቡዌ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሙጋቤ ...
Read More »የኢትዮጵያው አገዛዝ የውጭ ብድር ቁጥጥር ያድርግ ተባለ
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 5/2010) የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ክርስቲን ላጋርድ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ብድር ቁጥጥር እንዲያደርግና የወጭ ምርቶች ተወዳዳሪነትን እንዲያሰፋ ጠየቁ። ኢትዮጵያ ይህን ርምጃ ካልወሰደች ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊገጥማት እንደሚችል ዳይሬክተሯ አሳስበዋል። የአገዛዙ ቃለ አቃባዮች ግን የዳይሬክተሯ ጉብኝት ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ተሰሚነቷ በመጨመሩና ኢኮኖሚዋ በማደጉ የተካሄደ ነው ሲሉ የተሳሳተ መግለጫ ሰጥተዋል። በኢትዮጵያ የገንዘብና የእህል ዋጋ ግሽበት በእጅጉ እየጨመረ በመምጣቱ ...
Read More »በተለያዩ ከተሞችና ዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 4/2010) በተለያዩ ከተሞችና ዩኒቨርስቲዎች ተቃውሞዎች ሲደረጉ መዋላቸው ተገለጸ። የአጋዚ ሰራዊት ዛሬም ግድያ ፈጽሟል። ህዝቡ ደግሞ በአምቦ ሁለት የአጋዚ ወታደሮችን መግደሉ ታውቋል። በጨለንቆ ከትላንት በስቲያ የተደረገውን ጭፍጨፋ በመቃወም በበርካታ ከተሞች ተቃውሞዎች ተካሂደዋል። በሰሜን ወሎ ኡርጌሳ ትላንት የጀመረው ተቃውሞ ቀጥሎ 3 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ህዝቡ በቁጣ አንድ ከባድ ተሽከርካሪ መሰባበሩ ታውቋል። በደብረታቦር ዩኒቨርስቲ የአጋዚ ሰራዊት ተማሪዎች ላይ በመተኮስ ግድያ መፈጸሙን ...
Read More »ትራምፕ የኦባማን ላይብረሪ መጸዳጃ ቤት ለማጽዳት እንኳን ብቁ አይደሉም ተባለ
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 4/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኦባማን ላይብረሪ መጸዳጃ ቤት ለማጽዳት እንኳን ብቁ አይደሉም ሲል በአሜሪካ የሚታተም አንድ ታዋቂ ዕለታዊ ጋዜጣ በርዕሰ አንቀጹ አሰፈረ። ዩ ኤስ ኤ ቱደይ የተሰኘው ይህ ጋዜጣ ጠንከር ያለ ትችት በመሰንዘር የሚታወቅ ጋዜጣ ባይሆንም ትላንት ማክሰኞ ይዞ የወጣው ርዕሰ አንቀጽ ግን በአሜሪካ በሚገኙ ሌሎች መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኗል። የጉዳዩ መነሻ የሆነው የፕሬዝዳንት ትራምፕ ትላንት በቲውተር ...
Read More »የጋምቤላ ክልል እዳውን ከፍሎ ጨረሰ
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 4/2010) የጋምቤላ ክልል ለ10ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአል ከፌደራል መንግስት የተበደረውን የ346 ሚሊየን ብር ብድር በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ሆኖ መክፈሉ አስታወቀ። ክልሉ ብድሩን ይክፈል እንጂ አሁንም በክልሉ በርካታ ችግሮች መኖራቸውን የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ጠቁሟል። ክልሉ ባለፈው መስከረምና ጥቅምት ለመንግስት ሰራተኞች በወቅቱ ደሞዝ መክፈትል አቅቶት በርካታ ችግሮች መፈጠራቸውን ኢሳት በወቅቱ ባቀረበው ዘገባ አመልክቶ ነበር። የብሔር ብሔረሰቦች ...
Read More »የሕወሃት መሪዎች የአሜሪካንን ሽምግልናና ድጋፍ ይጠይቁ ተባለ
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 4/2010) በኢትዮጵያ ሕግና ስርአት ሙሉ በሙሉ ከመፍረሱ በፊት የሕወሃት መሪዎች የአሜሪካንን ሽምግልናና ድጋፍ እንዲጠይቁ አንድ የአሜሪካ የቀድሞ ዲፕሎማት ጥሪ አቀረቡ። ሀገሪቱን ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርአት ለመውሰድና ሁሉም ፓርቲዎች የሚሳተፉበት ጉባኤ ለማካሄድ የአሜሪካንን አደራዳሪነትና ሽምግልና ሕወሃት እንዲጠይቅ ሀሳብ አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ኽርማን ኮህን በማህበራዊ ገጻቸው ትላንት ባሰራጩት አጭር መልዕክት የሕወሃት መሪዎች ሁሉ ...
Read More »የህወሃት አገዛዝ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ዘጋ
(ኢሳት ዜና–ታህሳስ 4/2010) በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የህወሃት አገዛዝ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን መዝጋቱ ታወቀ። ፌስቡክና ትዊተርን የመሳሰሉት ማህበራዊ ድረ ገጾች ዝግ መሆናቸው ታውቋል። ወትሮም ደካማ የነበረው የኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት አሁን ላይ ጭራሹኑ የፌስ ቡክና ትዊተር ድረገጾች እንዲዘጉ ሲደረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የወጡ መረጃዎች እንዳይሰራጩ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል። በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ዜጎች መገደላቸው በተለይ ...
Read More »