(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 4/2010) የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተቋሙ ውስጥ ምግብ በመከልከላቸው ግቢያቸውን ጥለው መውጣታቸው ተነገረ። ተማሪዎቹ በዩኒቨርስቲው የሚቀርብላቸው ምግብ በመቆሙ ሕይወታቸውን ለማቆየት ግቢያቸውን ለቀው ወደ ሐሮማያ ከተማ ለመሔድ ተገደዋል። ዩኒቨርስቲው ለተማሪዎቹ ምግብ እንዳይሰጥ የከለከለው በግቢው ውስጥ የትምህርት ማቆም አድማ በመጀመሩ ነው ተብሏል። የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግቢያቸው ውስጥ ተማሪዎች በወታደራዊ እዝ/ኮማንድ ፖስት/በመታሰራቸው ይህንኑ በመቃወም ትምህርት አቁመዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሁለት ተማሪዎች ለአዲስ ...
Read More »የኢህአዴግ ነባር አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የኢህአዴግን መስመር ያስቀጥላል የሚል እምነት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው
የኢህአዴግ ነባር አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር የኢህአዴግን መስመር ያስቀጥላል የሚል እምነት እንደሌላቸው እየተናገሩ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 04 ቀን 2010 ዓ/ም) ነባሮቹ የኢህአዴግ አመራሮች አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢህአዴግን መስመር የማስቀጠል ፍላጎት አለው ብለው እንደማያምኑ እየተናገሩ ነው። የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት ነባር ከሆኑት የኢህአዴግ አመራሮች መካከል አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሃዬ፣ በረከት ስምዖን፣ ህላዊ ዮሴፍ፣ ስዩም መስፍንና ሌሎችም በድርጅቱ ውስጥ የቆዩ ...
Read More »የወልቃይት ተወላጆች አዲስ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ
የወልቃይት ተወላጆች አዲስ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 04 ቀን 2010 ዓ/ም) የአዲ ረመጥ ወረዳ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎች ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንዳመለከቱት “የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ትግራይ ቅርንጫፍ” የካቲት 2 ቀን 2010 ዓም አዲስ ክስ እንደቀረበባቸው አመልክተዋል። “ከወንጀል ሕግ አልፎ በሽብርተኝነት ተከሰው የነበሩ ሰዎች ክሳቸው በተቋረጠበት ሁኔታ በእኛ ላይ አዲስ ክስ መመስረቱ የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ...
Read More »የሱዳኑ ፕሬዝዳትን አልበሽር የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አዘዙ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2010) የሱዳኑ ፕሬዝዳትን ኦማር ሃሰን አልበሽር በሃገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ትዕዛዝ አስተላለፉ። ትዕዛዙ የተላለፈው በሃገሪቱ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሌሎች ቡድኖች በብሔራዊ ደረጃ በሚካሄደው ውይይት ላይ ለመሳተፍ በቅድሚያ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በጠየቁት መሰረት መሆኑ ታውቋል። የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች ለመልቀቅ ከውሳኔ ላይ የደረሱት በተቃዋሚዎች ጫና ነው ይላል ሮይተርስ በዘገባው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ...
Read More »አንድ የአልጄሪያ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከሰከሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2010) አንድ የአልጄሪያ ወታደራዊ አውሮፕላን ተከሰከሰ። በአደጋው የአውሮፕላኑን ሰራተኞች ጨምሮ 257 ሰዎች አልቀዋል። ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ከአልጄሪያ ርዕሰ መዲና አልጀርስ ወጣ ብሎ የተከሰከሰው ይህ ወታደራዊ አውሮፕላን በአብዛኛው ያሳፈረው ወታደሮችን ሲሆን ወደ ሌላ የአልጄሪያ ግዛት በመጓዝ ላይ እያለ በተነሳ በአጭር ግዜ ውስጥ መከስከሱም ተመልክቷል። የአልጄሪያ መንግስታዊ ቴሊቪዥን የሃገሪቱን መከላከያ ሚኒስቴር ጠቅሶ እንደዘገበው 247 መንገደኞችንና 10 የአውሮፕላኑን ሰራተኞች የያዘው አውሮፕላን ...
Read More »የዋልድባ መነኮሳት ክሳቸው ተቋረጠ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2010)በአሸባሪነት ተከሰው ከአመት በላይ በወህኒ ቤት የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ መወሰኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ሁለቱን የዋልድባ መነኮሳት ጨምሮ 114 ሰዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ የተወሰነ ሲሆን ይህም መንግስት እስረኞችን ለመልቀቅ ያሳለፈው ውሳኔ አካል እንደሆነም ተመልክቷል። ከዋልድባ አበረንታ ገዳም በምንኩስና ይኖሩ የነበሩትና የዋልድባ ገዳም መታረሱን በመቃወማቸው ሲፈለጉ ቆይተው ከአመት በፊት ወደ ወህኒ የተጋዙት አባ ገብረኢየሱስ ኪዳነማርያም ከሌላው መነኩሴ ...
Read More »በትግራይ ክልል ሚሊሻዎችና በአፋር አርብቶ አደሮች መካከል ግጭት ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2010) በትግራይ ክልል ሚሊሻዎችና በአፋር አርብቶ አደሮች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ። ሁለት የትግራይ ሚሊሻ አባላት በግጭቱ መገደላቸው ታውቋል። በአፋር ክልል ኩናባ ወረዳ ዋህደስ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሱዳ በተባለ ተራራ ላይ ትላንት የተጀመረው ግጭት ዛሬም ቀጥሏል። የትግራይ ክልል ከሚሊሺያዎች በተጨማሪ ልዩ ሃይልና መከላከያ መሰለፋቸውን የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ለኢሳት በላከው መረጃ ላይ ተመልክቷል። በሌላ በኩል ለኤርትራ አጎራባች በሆነው ቢር ...
Read More »በኤች አር 128 የተገኘው ድል ለሚቀጥለው ስራ ብርታት የሚሰጥ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 3/2010)በኤች አር 128 የተገኘው ድል ለሚቀጥለው ስራ ብርታት የሚሰጥ በመሆኑ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለወሳኙ ትግል እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀረበ። ትላንት ኤች አር 128 የተሰኘውን ረቂቅ ሰነድ የአሜሪካን ኮንግረስ በሙሉ ድምጽ ካሳለፈው በኋላ ለኢሳት ቃልመጠይቅ የሰጡት የኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል አመራር አባላት እንደገለጹት በኤች አር 128 የተገኘው ድል የመጨረሻው አይደለም፡ ቀሪ ተግባር የሚጠብቀን በመሆኑ በሞራልና አሸናፊነት መንፈስ ወደፊት መራመድ አለብን ...
Read More »የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ያጸደቁት ኤች አር 128 በመባል የሚጠራው ህግ ሉአላዊነትን የሚጥስ ነው በማለት አገዛዙ ተቃውሞውን ገለጸ
የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ያጸደቁት ኤች አር 128 በመባል የሚጠራው ህግ ሉአላዊነትን የሚጥስ ነው በማለት አገዛዙ ተቃውሞውን ገለጸ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 03 ቀን 2010 ዓ/ም) የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት በኢትዮጵያ ስብአዊ መብት እንዲከበር ለማስገደድ ያጸደው ህግ በርካታ ለነጻነታቸው የሚታገሉ ዜጎችን ያስደሰተ ቢሆንም፣ በአገዛዙ በኩል ግን በበጎ መልኩ አልታዬም። ይህ በርካታ አስገዳጅ አንቀጾችን የያዘው ህግ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የተፈጸሙት ግድያዎችና አፈናዎች በተመድ ገልለተኛ ...
Read More »በትግራይና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ።
በትግራይና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ። (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 03 ቀን 2010 ዓ/ም) በአፋር ክልል ኩናባ ወረዳ ዋህደስ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሱዳ በተባለ ተራራ ትናንት ማክሰኞ በትግራይ ታጣቂ ሚሊሻዎችና በአፋር አርብቶ አደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከትግራይ ሚሊሻዎች በኩል ሁለት መሞታቸውን የዓይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ በዚህ አካባቢ በሚሊሻዎቹና በአርብቶ አደሮቹ መካከል ተደጋጋሚ ግጭቶች ሲቀሰቀሱ ቆይተዋል። ...
Read More »