በትግራይና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ።

በትግራይና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተነገረ።
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 03 ቀን 2010 ዓ/ም) በአፋር ክልል ኩናባ ወረዳ ዋህደስ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሱዳ በተባለ ተራራ ትናንት ማክሰኞ በትግራይ ታጣቂ ሚሊሻዎችና በአፋር አርብቶ አደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከትግራይ ሚሊሻዎች በኩል ሁለት መሞታቸውን የዓይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።
እንደ ነዋሪዎቹ ገለጻ በዚህ አካባቢ በሚሊሻዎቹና በአርብቶ አደሮቹ መካከል ተደጋጋሚ ግጭቶች ሲቀሰቀሱ ቆይተዋል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆእጣጠር በ2014 በአካባቢው በተፈጠረ ተውመሣሳይ ግጭት አብደላ ኢድሪስ የተባለ የአፋር ተወላጅ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በትግራይ ሚሊሻዎች መገደሉን ያወሱት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ገዳዮቹ እስካሁን ለፍርድ አለመቅረባቸው በተደጋጋሚ ለሚያገረሹት ግጭቶች አንድኛው ምክንያት መሆኑንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
የአፋር ህዝብ የነጻነት ታጋይና አክቲቪስት አባድር ጉዳዩን አስመልክቶ ለኢሳት በሰጠው ማብራሪ ግጭቶች የሚነሱት የአፋርን ለም መሬትና ደን ለመውሰድ በተደረገ ሙከራ ነው ብሏል።