በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጣናን ለመታደግ ማሽን ገዝተው ወደ አገር ቤት ላኩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ጣና ሃይቅን ከእንቦጭ አረም ወረራ ለመታደግ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 2 ዘመናዊ ማሽኖችን ገዝተው መላካቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። ሁለቱ ማሽኖች ካናዳ ከሚገኝ ማሽን አምራች ድርጅት በ92 ሺ 350 የአሜሪካ ዶላር መገዛታቸውን፣ ተጨማሪ ማሽኖችን ለመግዛትም ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር የመስክ ጥናት እያካሄዱ መሆኑን አዘጋጆች ገልጸዋል። ከዚህ ...
Read More »የአርመንያው ፕሬዝዳንት ከስልጣን ለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2010) የአርመንያው ፕሬዝዳንት በሃገሪቱ የተቀሰቀሰባቸውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ስልጣናቸውን መልቀቃቸው ተሰማ። በቅርቡ ስልጣናቸውን ይለቃሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ሰርዝ ሳርግስያን ባለፈው ማክሰኞ ራሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውም ተሰምቷል። ይህን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽም የሀገሪቱን ስልጣን አላግባብ ተቆጣጥረውታል የተባሉት ሰርዝ ሳርግስያን ስልጣናቸውን በግዴታ እንዲለቁ አድርጓቸዋል ተብሏል። በአርመኒያ በተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ኒኮል ፓሲኒያ የተጠራውን ተቃውሞ ተከትሎ የአርመኒያ ህዝብ አደባባይ በመውጣት የሃገሪቱ ...
Read More »በሽር ማክትሃል ከእስር ተለቆ ወደ ቶሮንቶ መመለሱ ተነገረ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2010)በኢትዮጵያ እስር ቤት ለ11 አመታት ሲማቅቅ የቆየውና የካናዳ ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከእስር ተለቆ ወደ ቶሮንቶ መመለሱ ተነገረ። ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ በምህረት የተለቀቀው በሽር ማክትሃል የተባለው ኢትዮጵያዊ በሽብር ተከሶ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት እንደነበር ይታወሳል። በሽር ማክትሃል ከኢትዮጵያ ወደ ካናዳ በማምራት በስደት ሲኖር ቆይቶ ዜግነት ካገኘ በኋላ ወደ ኬንያ በማምራት የልባሽ ጨርቅ ይነግድ ነበር። ቀጥሎም በሶማሊያ ተመሳሳይ ንግድ ...
Read More »የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የገዛሀኝ ነብሮን ግድያ የግል መርማሪ ቀጥሮ ሊያጣራ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2010) በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የአክቲቪስት ገዛሀኝ ገብረመስቀልን ግድያ የግል መርማሪ ቀጥሮ ሊያሰራ መሆኑ ታውቀ። ባለፈው ቅዳሜ በጥይት ተመቶ በተገደለው የአክቲቪስት ገዛሀኝ/ነብሮ/ አሟሟት ኢትዮጵያውያን ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። ግድያው በህወሃት ኤምባሲ በኩል መፈጸሙን የሚያሳዩ ፍንጮች እንዳሉ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሰብሳቢ ለኢሳት በሰጡት ቃለመጠይቅ ላይ ገልጸዋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል ሆኖ ሀገሩን ከአደጋ ለማዳን በዱር በገደሉ ተዋግቷል። በልጅነቱ የተሸከመው ሀገራዊ ሃላፊነትና ...
Read More »ዶናልድ ያማማቶ በኢትዮጵያ፣ኤርትራና ጅቡቲ የሚያደርጉትን ጉዞ ጀመሩ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2010) በአሜሪካ ወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር ሚስተር ዶናልድ ያማማቶ በኢትዮጵያ፣ኤርትራና ጅቡቲ የሚያደርጉትን ጉዞ ጀመሩ። እሁድ ኤርትራ ርዕሰ መዲና አስመራ የገቡት ዶናልድ ያማማቶ ከዚያም ወደ ጅቡቲ አቅንተው አዲስ አበባ ላይ ተልዕኳቸውን እንደሚፈጽሙ ተመልክቷል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ያማማቶ ትላንት እሁድ ኤርትራ ቢገቡም ከኤርትራ ባለስልጣናት ጋር የሚነጋገሩት ዛሬ ሰኞ ...
Read More »የሰብአዊ መብት ረገጣ የፈጸሙ ግለሰቦች ለፍርድ አልቀረቡም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2010) በኢትዮጵያ በአገዛዙ ታጣቂዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችና ወንጀሎች ተጣርተው ፈጻሚዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንዳልተደረገ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሪፖርት አመለከተ። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2017 ሪፖርት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባሰፈረው የሰብአዊ መብት አያያዝ በሃገሪቱ ተጠያቂነት ባለመኖሩ በርካታ የሰብአዊ ጥሰቶች በመፈጸም ላይ ናቸው። በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተወሰዱ የማሻሻያ ርምጃዎች አዎንታዊ ለውጥ መታየቱንም ሪፖርቱ አመልክቷል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ የሰብአዊ መብት አያያዝ ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትን አነጋገሩ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 12/2010)ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትን አነጋገሩ። የወልቃይት ጉዳይ በህገመንግስቱና በህጉ የሚፈታ ነው ማለታቸውም ተገልጿል። ዛሬ በጎንደር ጎሃ ሆቴል ከጎንደር ህዝብ ጋር በተደረገ ውይይት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመቀሌ ስለወልቃይት የተነሳው ከማንነት ጋር የተያያዘ ጥያቄ አይደለም በማለት መግለጻቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የሱዳን የድንበር ጉዳይንም በተመለከተ ከሱዳኑ መሪ አልበሽር ጋር እንደሚነጋገሩ አስታውቀዋል። በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይም ተነስቶ ...
Read More »የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት ጉዳይ በህገ መንግስቱ መሰረት ይፈታል ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ
የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት ጉዳይ በህገ መንግስቱ መሰረት ይፈታል ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) አዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ጎንደር ከተማ ተገኝተው ከህዝቡ ጋር ባደረጉት ስብሰባ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ በህግ ሊፈታ እንደሚችል ህዝቡ ማመን አለበት ብለዋል ፡፡ “ህገ መንግስቱ ይህን ጉዳይ ሊፈታ ይችላል፡፡ በቀጣይም ከወልቃይት ኮሚቴዎች ጋር ውይይት አደርጋለሁ ‘ማለታቸውን የክልሉ ...
Read More »በሽንሌ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ በሞያሌ እንደገና ግጭት ተነሳ
በሽንሌ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ሲካሄድ በሞያሌ እንደገና ግጭት ተነሳ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮ ሶማሊ ክልል በሺንሌ ዞን ዛሬ ሲካሄድ በዋለው ተቃውሞ ህዝቡ የወረዳ አስተዳዳሪዎችን ከከተማ ከማባረሩ በተጨማሪ እስር ቤት ሰብሮ በመግባት እስረኞችን አስፈትቷል። ኤረር ውስጥ የአብዲ ኢሌ የእህት ልጅ የሆነው የወረዳው አስተዳዳሪ የአቶ ሃሰን አብዲ ኢሌ መኖሪያ ግቢ ተሰባብሯል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ የሽንሌ ህዝብ ተቃውሞውን ...
Read More »ዶ/ር አብይ ለፍትህ፣ ለነጻነትና ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንዲሰሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አሳሰቡ
ዶ/ር አብይ ለፍትህ፣ ለነጻነትና ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንዲሰሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አሳሰቡ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጎንደር ከተማ የተገኙትን አዲሱን ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ለመቀበል በተዘጋጀ ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት፣ የአማራ ህዝብ በተለይም የክልሉ ህዝብ የዶ/ር አብይን የጠ/ሚኒስትርነት ስልጣን በደስታ የተቀበለው፣ ህዝቡ ለውጥ በመፈለጉና እርሳቸውም የለውጥ ምልክትና ተስፋ ተደርገው በመቆጠራቸው ነው። ዶ/ር አብይ እስካሁን ...
Read More »