በአማራ ክልል ባሉ ከተሞች የነዳጅ እጥረት ተከሰተ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 16/2010) በአማራ ክልል ባሉ ከተሞች ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ ተነገረ። በዚህም ሳቢያ በየአካባቢዎቹ የትራንስፖርት መስተጓጎል ተፈጥሯል። የነዳጅ እጥረቱ መንስኤ ምን እንደሆነ በውል ባይታወቅም ችግሩ ከውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ምንጮች ይናገራሉ። በባህርዳር ፣ ወረታ ፣ጎንደር ፣ ደብረታቦር ፣ ወልዲያ ፣ ደብረማርቆስ ፣ ኮሶበርና መሰል ከተሞች ቤንዚንና ናፍጣ በነዳጅ ማደያዎች ባለመኖሩ የትራንስፖርት ችግር ተፈጥሯል። የኢሳት ምንጮች ...

Read More »

በኢትዮጵያ 8 ሚሊየን ሕዝብ አስቸኳይ እርዳታ ካላገኘ ሕይወቱ አደጋ ላይ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 16/2010) በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉ 8 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ እርዳታ ካላገኙ ሕይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑ ተነገረ። የአለም የምግብ ፕሮግራም ይፋ ባደረገው የአስቸኳይ ጊዜ ሪፖርት እንደተመለከተው 1 ነጥብ 8 ሚሊየን የሶማሌ ክልል ነዋሪ ኢትዮጵያውያን በሕይወት ለመቆየት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። የአለም የምግብ ፕሮግራም ይፋ ባደረገው የአደጋ ጊዜ ሪፖርት በዚህ በተያዘው የምዕራባውያኑ 2018 ዓመተ ምህረት 7 ነጥብ 9 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ...

Read More »

በሽንሌ ዞን የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ሌሎች ዞኖችም ተዛመተ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 16/2010) በሶማሌ ክልል ሽንሌ ዞን የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ ሌሎች ዞኖችም በመዛመት ላይ መሆኑ ታወቀ። የክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ ከስልጣን እንዲወርዱና ፍትህና ነጻነት እንዲሰፍን በሽንሌ አራት ወረዳዎች የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ ደገሀቡር መግባቱን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። የክልሉ ልዩ ሃይል ተቃውሞውን ለማስቆም የሃይል ርምጃ ተጠቅሞ ከ100 በላይ ሰዎች መታሰራቸው ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ዛሬ ሹሙትና የካቢኔ ...

Read More »

በሽንሌ ዞን ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው

በሽንሌ ዞን ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በሶማሊ ክልል በሽንሌ ዞን የተጀመረው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። ባርባርታ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ወጣቶች የአብዲ አሊን አገዛዝ በመቃወም የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን በመጠየቅ ላይ ሲሆኑ ፣ ሃድሃጋላ በሚባለው አካባቢ የክልሉ ልዩ ሃይል በነዋሪዎች ላይ ተኩስ መክፈቱ ታውቋል። በተኩስ ልውውጡ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ የታወቀ ነገር የለም። ትምህርት ...

Read More »

ከ 8 ሚሊዮን ያላነሱ ኢትዮጵያዊያን አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል ተመድ አሳሰበ

ከ 8 ሚሊዮን ያላነሱ ኢትዮጵያዊያን አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል ተመድ አሳሰበ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በመላው ኢትዮጵያ በተከሰተ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ምክንያት ከ 8 ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ። ከአፋጣኝ እርዳታ ፈላጊ ዜጎች ውስጥ 1.8 ሚሊዮን የሚሆኑ የርሃብ ተጠቂዎች በሶማሊያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ሕይወታቸውን ለማዳን አፋጣኝ የምግብ እርዳታ ይገባቸዋል ሲል ተመድ ...

Read More »

የደራሲ ይስማእከ ወርቁን ሕይወት ለመታደግ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በባሕርዳር ከተማ ሊዘጋጅ ነው

የደራሲ ይስማእከ ወርቁን ሕይወት ለመታደግ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በባሕርዳር ከተማ ሊዘጋጅ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 16 ቀን 2010 ዓ/ም) ወጣቱ ደራሲና ገጣሚ ይስማእከ ወርቁ ባጋጠመው የመኪና አደጋ ምክንያት የመናገርና የማስታወስ ክህሎቱን አጥቷል። ይህን የአገር ባለውለተኛ በገቢ በማገዝ በውጭ አገር ሕክምናውን እንዲከታተል ለማድረግ በከተማዋ ወጣት የኪነጥበብ አድናቂዎች አማካኝነት እንቅስቃሴ ተጀምሯል። አዘጋጆቹ የደራሲው ቀዳሚው ስራ በሆነው ”ዴርቶጋዳ” በተሰኘው መጽሐፉ ውስጥ የተጠቀሱትን ...

Read More »

በሽንሌ ዞን የሚካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ አካባቢው በመከላከያ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደረገ

በሽንሌ ዞን የሚካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ አካባቢው በመከላከያ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደረገ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በሽንሌ ዞን ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየውን ተቃውሞ ተከትሎ ወታደራዊ እዙ በቀጥታ የሚያዛቸው ወታደሮች አካባቢውን እንዲቆጣጠሩት መደረጉ ታውቋል። በክልሉ መሪ አቶ አብዲ ኢሌ በቀጥታ የሚታዘዙት የልዩ ሃይል አባላት አካባቢውን ተቆጣጥረው የቆዬ ሲሆን፣ እነዚህን ሚሊሺያዎች በመተካት የክልሉ ኮማንድ ፖስት ከዛሬ ጀምሮ አካባቢውን እንደሚቆጣጠረው ለህዝቡ ...

Read More »

የህውሃት ካድሬዎች ትንኮሳ እንዲቆምላቸው የሃይማኖት አባቶች ጠየቁ፡፡

የህውሃት ካድሬዎች ትንኮሳ እንዲቆምላቸው የሃይማኖት አባቶች ጠየቁ፡፡ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) የህገ መንግስቱን አንቀጾች በትክክል መተርጎም በማይችሉ የህውሃት ካድሬዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ቀኖና የሚደረጉ ትንኮሳዎች ይቆምላቸው ዘንድ የእምነት አባቶች ጠየቁ፡፡ በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና በመላው ዓለም የሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች የሚገለገሉበት የቃልኪዳን ቀለም የያዘ ምልክት የስርዓቱ ካድሬዎች እንደ ባንዲራ በመቁጠር የእምነቱ ተከታዮችን በተለያዩ ጊዜ ...

Read More »

የኢንሳው ዳይሬክተር ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ መስሪያ ቤቱ ትርምስ ውስጥ ነው

የኢንሳው ዳይሬክተር ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ መስሪያ ቤቱ ትርምስ ውስጥ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ለኢሳት የደረሰው ጥቆማ እንደሚያመለክተው የዶ/ር አብይ አህመድን ጠ/ሚኒስትር ሆኖ መመረጥ በመቃወም ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/አረጋዊ ስልጣናቸውን ከለቀቁ በሁዋላ መስሪያ ቤቱ ትርምስ ውስጥ መግባቱን ምንጮች ገልጸዋል። የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲው በአቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዲመራ መደረጉ ያበሳጫው የህወሃት ባለስልጣናት፣ የህወሃት የስለላ አባላት ዋና ዋና የሚባሉ የስለላ መሳሪያዎችን ...

Read More »

ከአርባ ምንጭ ከተማ በምህረት የተለቀቁት ወጣት ባንተወሰን አበበና ጓደኞቹ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ

ከአርባ ምንጭ ከተማ በምህረት የተለቀቁት ወጣት ባንተወሰን አበበና ጓደኞቹ እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ገዥው ህወሃት/ኢህአዴግ የፖለቲካና የሕሊና እስረኞችን በምህረትና በይቅርታ አለመልቀቅ የገባውን ቃል ተከትሎ በነጻ የተለቀቁት የአርባ ምንጭ ወጣቶች ዳግም ለእስራት ተዳርገዋል። ወጣት ባንተወሰን አበበን ጨምሮ አብረውት የነበሩት ሶስት ወጣቶች በባጃጅ ተጭነው ሲጓዙ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል። እስካሁን 14 ቀናት ታስረው ፍርድ ...

Read More »