(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8/2010) በጋምቤላ ክልል በ2008 ተካሂዶ ለነበረው 10ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የምግብ መስተንግዶ ወይዘሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ ለተባሉ የሆቴል ባለቤት ከክልሉ የመጠባበቂያ በጀት 12 ሚሊዮን ብር መከፈሉ ተገለጸ ። ገንዘቡ በበአሉ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት አቶ ማትዮስ ገለታ ስም ወጭ ተድርጎ ለወይዘሮ ትልቅ ሰው ገዳሙ እንዲከፈል ትእዛዝ የሰጡት የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉክ ቱት ናቸው። የጋምቤላ ምክር ቤት ታመው ...
Read More »በየአካባቢው የተፈጠረው ግጭት የለውጥ ሂደቱ ባልተዋጠላቸው አካላት ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8/2010) በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በየአካባቢው የተፈጠረው ግጭት በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ባልተዋጠላቸው አካላት ጠንሳሽነት እየተመራ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ። የፌዴራል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የመንግስትን አቋም በሚያመለክተው መግለጫው እንዳለው አካባቢያዊ ወሰንና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን መነሻ በማድረግ ለግጭት የሚያነሳሱ ሴራዎች እየተስተዋሉ ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለምበአዋሳ የተጀመረው ግጭት ግድያን ዘረፋን ጨምሮ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በወላይታ ሶዶ ግድያውን በማውገዝ በተካሄደ ትዕይንተ ...
Read More »የኢድ አልፈጥር በአል ተከበረ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8 /2010) 1 ሺህ 439ኛው የኢድ አልፈጥር በዛሬው እለት በመላ ዓለም ተከበረ ። የእስልምና ዕምነት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያወያን በዓሉን በአዲሰ አበባ ስታዲየም እና በክልል ከተሞች በድምቀት አክብረዋል። በውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በተመሳሳይ በየሚገኙበት ሃገር በአሉን እንዳከበሩም ታውቋል። ። በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት ከሚከበሩት በዓላት አንዱ የሆነው የኢድ አልፈጥር በዓል ከአንድ ወር የጾም ጊዜያት በኋላ የሚመጣ ዓመታዊ ...
Read More »የአለም ዋንጫ በሩሲያ ሞስኮ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) 21ኛው የአለም ዋንጫ ዛሬ በሩሲያ ሞስኮ ከተማ ተጀመረ። በአለም ዙሪያ በቢሊየን የሚቆጠሩ ተመልካቾችን በመሳብ ግንባር ቀደም ሆኖ የተገኘው የአለም የእግር ኳስ ዋንጫ ከአፍሪካ የሚሳተፉ 5 ቡድኖችን ጨምሮ 32 ሀገራት ተሳታፊ ሆነውበታል። ከዛሬ ሰኔ 7/2010 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2010 የሚቆየው የአለም ዋንጫ በሩሲያ ሞስኮና ፒትስበርግን ጨምሮ በ11 ከተሞች የሚካሄድ ነው። ሩሲያም ይህንን እድል ስታገኝ የመጀመሪያዋ ነው ተብሏል። በዚህ ...
Read More »የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ቅሬታውን አቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር ላይ ቅሬታውን አቀረበ። የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ባድመን በተመለከተ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሁም ግዙፍ የመንግስት ተቋማት በከፊል ወደ ግል እንዲዞሩ የተደረሰበትን ስምምነት ግን እንደሚቀበለው አረጋግጧል። የእስከዛሬው ድላችንም ሆነ የነገው ስኬታችን በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ መስመር ብቻ ነው ብሏል የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ። ይህ ተግባራዊ መስመር በኢሕአዴግ አመራር እየተሸረሸረ ነው ሲልም ማዕከላዊ ኮሚቴው ...
Read More »የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው ወጡ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው በመውጣት ላይ መሆናቸው ተገለጸ። የአማራ ተወላጆች የሚደርስባቸው ጥቃት እንዲቆም በመጠየቅ ባለፉት አራት ቀናት የተጀመረው ተቃውሞ በክልሉ ልዩ ሃይል የሃይል ርምጃ መወሰዱን ተከትሎ ተማሪዎቹ ሻንጣቸውን ይዘው ከግቢ መውጣታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ትላንት ግቢው ድረስ ዘልቆ የገባው ልዩ ሃይል በተማሪዎች ላይ ድብደባ በመፈጸም ከባድ ጉዳት ማድረሱም ታውቋል። መንገድ ላይ የተገኘ ነዋሪም ሲደብደብ መዋሉን በቪዲዮ ...
Read More »በጌዲዮ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል ቀጥሏል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጅ በጌዲዮ ብሔረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል መቀጠሉ እንዳሳሰበው በሰሜን አሜሪካና አውሮፓ የጌዲዮ ማህበረሰብ ማህበር አስታወቀ። ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ለሚመለከታቸው የሃገር ውስጥና የውጭ ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ባለፈው 10 ቀናት ብቻ ከ2 መቶ በላይ የጌዲዮ ማህበረሰብ አባላት ሲገደሉ ከ3መቶ ሺህ በላይ ደግሞ ከሚኖሩበት አካባቢ ተፈናቅለዋል። ማህበሩ ከ137 የሚበልጡና በግፍ የተገደሉ ...
Read More »በወልቂጤ ህዝባዊ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 7/2010) በወልቂጤ ህዝቡ ተቃውሞ በማድረግ ላይ መሆኑ ታወቀ። የመከላከያ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ ወጣቱን በማፈስ እያሰሩ ቢሆንም ነዋሪው ቁጣውን በመግለጽ ላይ ነው። በእስከሁኑ ተቃውሞም ሶስት ሰዎች ተገድለዋል። ከ100 በላይ ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ የህክምና ማዕከላት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። ከ30 በላይ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን አራት የመንግስት ተሽከርካሪዎችም በእሳት መጋየታቸው ታውቋል። በሌላ በኩል በሀዋሳ በተነሳው ግጭት ከ30 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ...
Read More »በሃዋሳ በድጋሜ ግጭት ተነሳ
በሃዋሳ በድጋሜ ግጭት ተነሳ (ኢሳት ዜና ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም) በአመታዊው የሲዳማ የዘመን መለወጫ በአል -ጨምበለላ ቀን የተጀመረው ግጭት ዛሬ በድጋሜ ማገርሸቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የዛሬው ግጭት-ሁለት ሰዎች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ መገደላቸውን ተከትሎ የተነሳ ነው። የጨምበለላን በአል ወደ ብሄር ግጭት ለመቀየር የሚደረገውን ሙከራ ለማስቆም የአገር ሽማግሌዎች አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል። ደኢህዴን ከህወሃት ጋር ሆኖ ያቀናበረው ግጭት ነው የሚሉ ነዋሪዎች፣ ግጭቱን ...
Read More »ህወሃት- የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በባድመና የመንግስት ኢኮኖሚ ተቋማት ዙሪያ የወሰናቸውን ውሳኔዎች እንደሚቀበል አስታወቀ
ህወሃት- የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ በባድመና የመንግስት ኢኮኖሚ ተቋማት ዙሪያ የወሰናቸውን ውሳኔዎች እንደሚቀበል አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 7 ቀን 2010 ዓ/ም) በቅርቡ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባድመን ለኤርትራ የወሰነውን የአልጀርሱን ስምምነት እንደሚቀበል እንዲሁም ዋና ዋና የሚባሉትን የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም በሙሉ ወደ ግል ለማዞር የወሰነውን ውሳኔ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ እንደሚቀበለው ሲያስታውቅ፣ አፈጻጸሙ ላይ ግን ጥንቃቄ ይደረግ ብሎአል። ህወሃት ትናንት ባወጣው ...
Read More »