የኢድ አልፈጥር በአል ተከበረ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 8 /2010) 1 ሺህ 439ኛው የኢድ አልፈጥር በዛሬው እለት በመላ ዓለም ተከበረ ።


የእስልምና ዕምነት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያወያን በዓሉን በአዲሰ አበባ ስታዲየም እና በክልል ከተሞች በድምቀት አክብረዋል።
በውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በተመሳሳይ በየሚገኙበት ሃገር በአሉን እንዳከበሩም ታውቋል። ።
በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት ከሚከበሩት በዓላት አንዱ የሆነው የኢድ አልፈጥር በዓል ከአንድ ወር የጾም ጊዜያት በኋላ የሚመጣ ዓመታዊ በዓል ነው።