ሶስት ግዙፍ የስኳር ፕሮጀክቶች የግንባታ ውሎች ተቋረጡ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 28/2010) የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ለዓመታት ሊያጠናቅቃቸው ያልቻላቸው ሦስት ግዙፍ የስኳር ፕሮጀክቶች የግንባታ ውሎች እንዲቋረጡ ተወሰነ። ውሳኔውን ያሳለፈው የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ቦርድ መሆኑ ታወቋል። ይሕ በእንዲህ እንዳለም ሜቴክ ከፍተኛ ብክነት እንዳሳየ የታወቀበት የፌደራል ኦዲት ሪፖርት ተይዞ ከቆየ በኋላ ይፋ ተደርጓል። በፓርላማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስኳር ኮርፖሬሽኑን ሥራ አፈጻጸም ሰኔ 25 ...

Read More »

በተለያዩ ድርጅቶች ላይ የተጣለው የሽብርተኝነት ስያሜ ተነሳ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 28/2010) በኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣በኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባርና በአርበኞች ግንቦት ሰባት ላይ የተጣለው የሽብርተኝነት ስያሜ በይፋ ተነሳ። በሳምንቱ መጨረሻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሶስቱ ድርጅቶች ከአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ እንዲወጡ ያሳለፈውን ውሳኔ ፓርላማው ዛሬ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ስብሰባው ከሰባት አመት በፊት በአንድ ተቃውሞ ብቻ የሳለፈውን የአሸባሪነት ስያሜ ዛሬ ላይ በሙሉ ድምጽ ሽሮታል። ሰኔ 7 ቀን ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲመረመር ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 28/2010) በሶማሌ ክልል የሚፈጸመውን መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በአስቸኳይ እንዲመረመር እንዲያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተጠየቁ። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄውን ያቀረበው ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች የተሰኘው ድርጅት ነው። ድርጅቱ በሶማሌ ክልል ስለሚፈጸሙ ሰቆቃዎች የሚያሳይ ጠለቅ ያለ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል። በተለይም ጄይል ኦጋዴን በተሰኘው አሰቃቂ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ የሚፈጸምበት መሆኑን ምስክሮችን እማኝ ...

Read More »

በሱዳን ታጣቂዎች የተገደሉ ኢትዮጵያውያን የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 28/2010) ሰሞኑን በድንበር ላይ በሱዳን ታጣቂዎች የተገደሉ ኢትዮጵያውያን የቀብር ስነስርዓታቸው ተፈጸመ። በመተማ ወረዳ ገንዳውሃ ከተማ በተፈጸመው የቀብር ስነስርዓት በብዙ ሺህ የሚቆጠር የአካባቢው ነዋሪ በተኩስ እሩምታ በማጀብ ማከናወኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በተለይም የአርበኛ ገብሬ አውለው የቀብር ስነስርዓት በልዩ ስሜት የተከናወነ ሲሆን ህዝቡ ድንበር ጥሶ ጥቃት የፈጸመውን የሱዳን ጦር ለመፋለም መዘጋጀቱን አስታውቋል። በቀብር ስነስርዓቱ ላይ በቀረርቶና ሽለላ ጀግኖቻቸውን የሸኙት የመተማ ...

Read More »

ዶ/ር አብይ አህመድ በሶማሌው ርዕሰ መስተዳድር በአቶ አብዲ ኢሌ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ይሰጡ ዘንድ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ

ዶ/ር አብይ አህመድ በሶማሌው ርዕሰ መስተዳድር በአቶ አብዲ ኢሌ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ይሰጡ ዘንድ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ባወጣው መግለጫ በክልሉ በሚገኘው የኦጋዴን እስር ቤት ውስጥ በተፈጸሙት አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ምርምራ ማካሄዱን በመጥቀስ፣ የደህንነት ሰራተኞችና ባለስልጣናት ተጠያቂ እንዲሆኑ ያደርጉ ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቋል። “የሞቱትን እንመስላለን” በሚል ርዕስ ...

Read More »

ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7ን በሽብርተኝነት የፈረጀው ፓርላማ ፍረጃውን አነሳ

ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7ን በሽብርተኝነት የፈረጀው ፓርላማ ፍረጃውን አነሳ (ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በፓርላማው በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ያስደረጓቸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች የሆኑት፣ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባርና አርበኞች ግንቦት7፣ ዛሬ በዚያው ፓርላማ ፍረጃው እንዲነሳላቸው ተደርጓል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ቃል በገቡት መሰረት የተላለፈው ይህ ውሳኔ ፣ የሃይል ...

Read More »

በመልካ ጀብዱ በተነሳ ብሄር ተኮር ግጭት ሰዎች ተጎዱ

በመልካ ጀብዱ በተነሳ ብሄር ተኮር ግጭት ሰዎች ተጎዱ (ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) በድሬዳዋ ከተማ ዙሪያ በምትገኘው መልካ ጀብዱ ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓም በኢሳ የሶማሊ ጎሳዎችና በጉርጉራ የኦሮሞ ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ሰው ሲገደል ፣በርካታ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። ግጭቱን የድሬዳዋና የአካባቢውን ስልጣን ለመቆጣጠር ያለሙ የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስነሱት ነዋሪዎች ተናግረዋል። ግጭቱን ተከትሎ በተነሳው አመጽ አህመድ አብዱልሀኪም ...

Read More »

ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት መልዕክት መላካቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘገበ።

ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት መልዕክት መላካቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘገበ። (ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በሁለቱ ሀገራት በሚዋሰኑባቸው የድንበር አካባቢዎች ግጭት ተቀስቅሶ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መጎዳታቸው ይታወቃል። የሱዳን ታጣቂዎች ድንበር አሳብረው በመግባት ” የእርሻ መሬት ይገባኛል” በሚል በፈጸሙት ጥቃት የተቀሰቀሰው ግጭት በሚቆምበት እና በሀገራቱ ድንበሮች አካባቢ ዘላቂ ...

Read More »

አዳዲስ ፕሬዝዳንቶች ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 27/2010) ለኢትዮያ ንግድ ባንክና ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳዲስ ፕሬዝዳንቶች ተሾሙ። አቶ ባጫ ጊና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት ሲደርጉ አቶ ሃይለማርያም በቀለ ደግሞ የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸው ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ካለፉት ሶስት ወራት ጀምሮ በሃገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ የሚካሄደው ብወዛ የሃገሪቱ ብሔራዊ ባንክ ገዢን በማንሳት ተጀምሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው ለረጅም አመታት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያዩ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 27/2010) የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አስፈላጊ ኮሚቴ አባላት በተጨማሪ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሃላፊዎችንም አነጋገረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለቱንም ወገኖች በተናጠልና በጋራ ማወያየታቸውን ተከትሎ ሁለቱም ወገኖች ችግሮቻቸውን የእስልምና አስተምህሮቶቻቸውን መሰረት ...

Read More »