በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነኝ በሚል ስም የጦርነት አዋጅ እያወጀ ያለው አካል ፣ እያደረገ ያለው ነገር እንዲያስብበት እና ወደትክክለኛው መንገድ እንዲመለስ ኦቦ ለማ መገርሳ አስጠነቀቁ።

በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነኝ በሚል ስም የጦርነት አዋጅ እያወጀ ያለው አካል ፣ እያደረገ ያለው ነገር እንዲያስብበት እና ወደትክክለኛው መንገድ እንዲመለስ ኦቦ ለማ መገርሳ አስጠነቀቁ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 4 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦቦ ለማ መገርሳ የጦርነት አዋጅ ያወጀውን ቡድን ያስጠነቀቁት፣ ትናንት በኦሮሚያ ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ነው። “ከዚህ በፊት ቀጥታ ሲዋጉን የነበሩ አካላት ...

Read More »

511 የሚሆኑ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ብሄር ተወላጆች እስካሁን መፍትሄ አላገኙም ፡፡

511 የሚሆኑ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ብሄር ተወላጆች እስካሁን መፍትሄ አላገኙም ፡፡ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 4 ቀን 2010 ዓ/ም ) ተፈናቃዮቹ የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ስብሰባን ምክንያት በማድረግ ወደ ስብሰባ ቦታው በመሄድ ችግራቸው እንዲታይላቸው የጠየቁ ሲሆን፣ የክልሉ አመራሮች ለአጭር ጊዜ አግኝተው አነጋግረዋቸዋል። ባለስልጣናቱ እስከ መጪው ቅዳሜ ስብሰባ ላይ መሆናቸውንና እሁድ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተፈናቃዮችን እንደሚያናግሩዋቸው ...

Read More »

የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት በሌሉበት መሻራቸውን ተቃወሙ

የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት በሌሉበት መሻራቸውን ተቃወሙ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 4 ቀን 2010 ዓ/ም ) የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙራድ አብዱላሂድ እርሳቸው ባልተገኙበት ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓም የተደረገው የማእከላዊ ስብሰባ እና የፕሬዚዳንት ምርጫ እንደማይቀበሉትና አሁንም ክልሉን እሳቸው እንደሚመሩት አስታውቀዋል። ምክር ቤቱ አቶ ኦድሪን በድሪን ሊቀመንበር ፣ አቶ ነቢል ማሃዲን ደግሞ ምክትል ሊ/መንበር አድርጎ መርጦ ነበር። አቶ ሙራድ ከአዲስ አበባ ከተመለሱ ...

Read More »

ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደረገው በረራ በቀጣዩ ሳምንት ይጀመራል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደርገውን በረራ በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ እንደሚጀምር አስታወቀ። ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ እንዲሁም ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞች ያለ ቪዛ በፓስፖርት ብቻ መጓዝ እንደሚችሉም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻንም ወደ 114 ከፍ ያደርገዋል ተብሏል። ወደ አስመራ የሚደረገው በረራም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ማክሰኞ ሐምሌ 10/2010 በቦይንግ 787 አውሮፕላን እንደሚጀምርም ተመልክቷል። አንድ ሰአት ከ10 ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የተፈጸሙት በህወሃት መሪዎች አስገዳጅነት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) በሶማሌ ክልል ሲፈጸሙ የነበሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ግድያዎች በህወሃት መሪዎች ተገደን የፈጸምነው ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ አብዲ ዒሌ ይህን የተናገሩት ዛሬ በተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው። አብዲ ኢሌ የቀድሞ የደህንነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋን በስም በመጥቀስ እያስገደዱን ወንጀል እንድንፈጽም ያደረጉን ናቸው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድንና አቶ ለማ መገርሳን በማወደስ ለኢትዮጵያ ...

Read More »

የአቶ በረከት ስምኦን ተሽከርካሪ በእሳት ጋየ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) አቶ በረከት ስምኦን በደብረማርቆስ ታዩ በመባሉ በተካሄደ ተቃውሞ ቪ ኤይት ተሽከርካሪያቸው መቃጠሉ ተነገረ። በጎዛምን ሆቴል ታይተዋል የተባሉት አቶ በረከት ስምኦን ሹፌር መታወቂያም ተገኝቷል። በደብረማርቆስ ሕዝቡ አቶ በረከትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ያደረገው ተቃውሞን ተከትሎ በአካባቢው የስልክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉም ታውቋል። አቶ በረከት ስምኦን ከአምባገነኑ መሪ መለስ ዜናዊ ጋር የኢትዮጵያን መንግስት በተንኮልና በአሻጥር በመምራት የሕወሃት ተላላኪ ሆነው ላለፉት 27 ...

Read More »

የኦሮሚያን ክልል ሰላም ለማደፍረስ የሚጥሩ አካላት አሉ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) በውጭ የሚገኙ በኦሮሞ ስም የተደራጁ ድርጅቶች  ወደ ሃገር ቤት ገብተው በሰላም እንዲንቀሳቀሱ  እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት  በኦሮሞ ስም የተደራጁ ሌሎች አካላት የኦሮሚያን ክልል ሰላም  ለማደፍረስ   በመስራት ላይ  መሆናቸውን አቶ ለማ መገርሳ ገለጹ። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ይህንን የተናገሩት እየተካሄደ ባለው የኦሮሚያ ክልላዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው። አቶ ለማ መገርሳ ለኦሮሚያ ክልላዊ ምክር ቤት ...

Read More »

ሲኖዶስን ወክለው ሶስት ጳጳሳት ወደ አሜሪካ ሊጓዙ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በሽምግልና ለመፍታት ሶስት ጳጳሳት የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ ወክለው ወደ አሜሪካ እንደሚጓዙ ተገለጸ። ፓትሪያሪክ ብጹዕ አቡነ ማትያስ አባቶቹ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን ጉዞ በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስ ከሐገር በመውጣታቸው ላለፉት 26 ዓመታት የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ማዘናቸውንና ቤተክርስተያኒቱ በሰላም እጦት ውስጥ ማለፏን ገልጸዋል። ከሐምሌ 11/2010 ጀምሮ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ...

Read More »

ሜ/ጄ ተክለብርሃን ወ/አረጋይ ይመሩት የነበረው ኢንሳ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ በሙስና ማባከኑ ታወቀ

ሜ/ጄ ተክለብርሃን ወ/አረጋይ ይመሩት የነበረው ኢንሳ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ በሙስና ማባከኑ ታወቀ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 3 ቀን 2010 ዓ/ም ) የዶ/ር አብይ አህመድን ጠ/ሚኒስትር ሆኖ መመረጥ አጥብቀው ሲቃወሙ፣ ጠ/ሚኒስትሩን “ጠላት” ብለው በመፈረጅ የለውጥ ሂደቱን ለመቀልበስ ጥረት እያደረጉ የሚገኙት የቀድሞው የኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሜ/ጄኔራል ተክለብርሃን ወልዳረጋይ እና በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ የሚገኘው ምክትሉ ቢኒያም ተወልደ ...

Read More »

ኢትዮጵያና ኤርትራ ታሪካቸውን መቀየራቸውን ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ

ኢትዮጵያና ኤርትራ ታሪካቸውን መቀየራቸውን ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 3 ቀን 2010 ዓ/ም ) ጠ/ሚኒስትሩ ለኤርትራው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ በጻፉት ደብዳቤ ፣ ሁለቱ አገራት መራርና አውዳሜ ጊዜ ማሳለፋቸውን ጠቅሰዋል። አሁን ያ የታሪክ ምዕራፍ ተዘግቶ ሁለቱ አገራት አዲስ የሰላም ግንኙነት መጀመራቸውም ጠ/ሚኒስተሩ ገልጸዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያ ዝግጁ ናት ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፣ በኤርትራ በነበረው ቆይታቸው ...

Read More »