(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በቂሊንጦ እስር ቤት የእሳት ቃጠሎ መድረሱ ተነገረ። በእስር ቤቱ የእንፈታ ጥያቄ ያቀረቡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጋዝ ሲተኮስ እንደነበርና የቦምብ ፍንዳታም መሰማቱ ተነግሯል። እስረኞቹን ለመጠየቅ የመጡ ሰዎች በፖሊስ እንደተደበደቡ ለማወቅ ተችሏል። በቂሊንጦ እስር ቤት እስረኞች የእንፈታ ጥያቄ አቅርበው ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል። እስረኞቹ የኦነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት በሚል ታስረው ከነበሩት መካከል መሆናቸውም ታውቋል። ድሃ በመሆናችንና ታዋቂ ባለመሆናችን ከእስር ...
Read More »ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ነገ ወደ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ነገ አዲስ አበባ እንደሚገቡ መንግስት ይፋ አደረገ። የአዲስ አበባና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ለኤርትራው መሪ አቀባበል እንዲያደርጉላቸውም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ከቅዳሜ ሐምሌ 7/2008 ጀምሮ እስከ ሰኞ ሐምሌ 9/2010 ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ቆይታ እንደሚያደርጉም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦርነት ከፈነዳበት ግዜ ጀምሮ እንዲሁም ...
Read More »የውጭው ሲኖዶስ ለሰላሙ ድርድር ዝግጁ ነኝ አለ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 6/2010) በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የሚመራው በውጭ ሃገር የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰላሙ ድርድር ዝግጁ መሆኑን ገለጸ። በእርቅ መድረኩ ላይ የሚገኙ ሶስት ሊቃነጳጳሳት መሰየማቸውንም ይፋ አድርጓል። የጥላቻና የመከራው ዘመን ያብቃ ሲልም ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥሪውን አቅርቧል። በሚቀጥለው ሳምንት ሐሙስ በሚጀመረውና ከሐምሌ 12 እስከ 21 እንዲቀጥል መርሃ ግብር በተያዘለት የእርቅ ፕሮግራም እንዲሳካ ቅዱስ ሲኖዶሱ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት ይፋ አድርጓል። በፓትሪያርክ አቡነ ...
Read More »የለውጥ ጸር የሆኑ ሃይሎች በኦሮምያ ላይ ጦርነት መክፈታቸውን አቶ አዲሱ አረጋ ተናገሩ
የለውጥ ጸር የሆኑ ሃይሎች በኦሮምያ ላይ ጦርነት መክፈታቸውን አቶ አዲሱ አረጋ ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኦሮምያ ክልል የገጠር የፖለቲካና ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባወጡት ጽሁፍ፣ የለውት ጸር የሆኑ ሃይሎች ኦሮሞ ከባድ መስዋትነት ከፍሎ ያስመዘገበውን ድል ለማኮላሸትና ለመቀልበስ ከምንጊዜውም በላይ እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል። እነዚህ ሃይሎች ድላችንን ዋጋ ቢስ ለማድረግና ...
Read More »በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ
በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከአርበኞች ግንቦት7 እና ከሌሎችም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በተያያዘ እስረኞች ፍትህ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ከትናንት ሃሙስ ምሽት ጀምሮ ተቃውሞውዋቸውን እያሰሙ ነው። እስረኞቹ፣ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ተፈተው እያለ እንዲሁም በስማቸው የተከሰሱባቸው የፖለቲካ ድርጅቶች አሸባሪዎች እንዳልሆኑ በፓርላማ ውሳኔ ተላልፎ በሚገኝበት ሰዓት እነሱ አሸባሪ ተብለው መከሰሳቸው ፍትሃዊ እንዳልሆነ ...
Read More »የኤርትራው መሪ ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚገቡ መንግስት አስታወቀ
የኤርትራው መሪ ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚገቡ መንግስት አስታወቀ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት ቅዳሜ የሚገቡት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባና በሃዋሳ የስራ ጉብኝት ያካሂዳሉ። የሁለቱ አገራት መሪዎች በሚሊኒየም አዳራሽ ተገኝተው የሁለቱን አገራት ሰላም እንደሚያበስሩ ሃላፊው ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሃዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዶ/ር አብይ አህመድ ኤርትራን ...
Read More »በቅርቡ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነት ስልጣናቸውን የለቀቁት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ
በቅርቡ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነት ስልጣናቸውን የለቀቁት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ) የህወሃት የደቡብ ክንፍ ቀኝ እጅ ተደርገው የሚቆጠሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከግርብና እና የእንስሳት ሃብት ሚኒስትር ቦታቸው ለቀው በአምባሳደርነት ተሹመዋል። የግለሰቡ ከማእከላዊ ስልጣን መልቀቅ ህወሃት በደቡብ ክልል ያላትን ስልጣን እንደሚያሳጣት ዘጋቢያችን ገልጿል። ከሽፈራው ሽጉጤ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ...
Read More »የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በለንደን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በለንደን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ) እንግሊዝን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የህጻን ምስላቸውን ከፍ አድርገው በያዙ ተቃዋሚዎች ሲወገዙ ውለዋል። አብዛኞቹ ሰልፈኞች ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስደተኞችን በተመለከተ የሚከተሉትን ፖሊሲዎች አውግዘዋል። እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ህብረት ማቋረጡዋን በተመለከተ ፕሬዚዳንቱ በአንድ ቀን ልዩነት እርስ በርስ የሚጣረስ ንግግር መናገራቸው የመገናኛ ብዙሃን የትኩረት አቅጣጫ ...
Read More »በደብረማርቆስ ከተማ ውጥረቱ ዛሬም ቀጥሎ ዋለ
በደብረማርቆስ ከተማ ውጥረቱ ዛሬም ቀጥሎ ዋለ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 5 ቀን 2010 ዓ/ም ) አቶ በረከት ስምኦን ደብረማርቆስ ከተማ ላይ ታይተዋል በሚል ከሁለት ቀናት በፊት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን ዘጋቢያችን ከስፍራው ገልጿል። ትናንት በዚሁ ሳቢያ በነበረው ተቃውሞ ቤቶችና ተሽከርካሪዎች መውደማቸው ተመልክቷል። በዛሬው ዕለትም ህዝቡ የህውሃት ተላላኪዎች ወደ ከተማዋ በመግባት ጥፋት ሊፈጽሙ ይችላሉ በሚል በደብረማርቆስ መግቢያና መውጫ ላይ ከፍተኛ ...
Read More »አብዲ ኢሌ የፓርላማ አባሉን አሰሩ
አብዲ ኢሌ የፓርላማ አባሉን አሰሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 5 ቀን 2010 ዓ/ም ) ትናንት በክልሉ ለተፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት የቀድሞውን የደህንነት ሚኒስትር ተጠያቂ ያደረጉት የሶማሌው ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ኢሌ፣ አቶ ጌታቸውን በተመለከተ ከአጀንዳ ውጭ በፓርላማ መናገራቸውን በመንቀፍ ለአፈ ጉባኤውና ለሶማሊ ክልል አመራሮች ደብዳቤ የጻፉትን አቶ አብዲ ዴሬን “የጌታቸው ደጋፊ” በሚል ዛሬ አስረዋቸዋል። የፓርላማ አባሉ አቶ አብዲ ዴሬን ...
Read More »