በቅርቡ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነት ስልጣናቸውን የለቀቁት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

በቅርቡ ከደኢህዴን ሊቀመንበርነት ስልጣናቸውን የለቀቁት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ) የህወሃት የደቡብ ክንፍ ቀኝ እጅ ተደርገው የሚቆጠሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከግርብና እና የእንስሳት ሃብት ሚኒስትር ቦታቸው ለቀው በአምባሳደርነት ተሹመዋል። የግለሰቡ ከማእከላዊ ስልጣን መልቀቅ ህወሃት በደቡብ ክልል ያላትን ስልጣን እንደሚያሳጣት ዘጋቢያችን ገልጿል።
ከሽፈራው ሽጉጤ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማም አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል። አለማየሁ ተገኑ፣ እሸቱ ደሴ፣ አዛናው ታደሰ፣ ዮናስ ዮሴፍ፣ ያለው አባተ እና አብዱልፈታ አብዱላሂም እንዲሁ አምባሰደር ሆነው ተሹመዋል። የቀድመው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ የነበሩት አቶ ያለው አባተም እንዲሁ የህወሃት ቀኝ እጅ መሆናቸውን እርሳቸውን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች ይገልጻሉ።