የኮሪያ ዘማቾች፤ በኮሪያ መንግስት የጡረታ ክፍያ ሊታሰብላቸው ነው

ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ60 ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ የዘመቱ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ከኮሪያ መንግሰት ጡረታ ሊቆረጥላቸው እንደሆነ ተገለጸ። በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ጊዮን ኪም እንዳሉት ፥ የጡረታውን አበል የደቡብ ኮሪያ መንግስት ለመቁረጥ የፈለገው ለሀገሪቱ ነጻነት ኢትዮጵያውያን አርበኞች ያደረጉትን ትልቅ ተጋድሎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው። በዚሀም መሰረት አርበኞቹ በየወሩ ሰባት መቶ ብር እንደሚከፈላቸው አምባሳደሩ ጠቁመዋል። ...

Read More »

በእስር ላይ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ድበደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ታወቀ

ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢሳት የፖሊስ ምንጮች እንደተናገሩት ባለፈው ሳምንት በሙስሊሙና በመንግስት መካካል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በተለያዩ እስርቤቶች በሚገኙ አማንያንና አመራሮች ላይ የሚፈጸመው ዘግናኝ ድርጊት እየጨመረ መምጣቱ ፣ አንዳንድ እስረኞች ስቃዩን መቋቋም ተስኖአቸው መንግስት የሚፈልገውን ሁሉ እንዳሉና ከስቃይ ለመገላገል ችለዋል። ሰውነታቸው ተገልብጦ የውስጥ እግራቸው የተገረፈ፣ ብልታቸው የተቀጠቀጠ፣ ጭናቸው መሀል ላይ መቆንጠጫ ብረት  የገባላቸው፣ እጃቸው የፊጥኝ ...

Read More »

የፍትህ ጋዜጣ እግድ ጸደቀ

ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣን እግድ እንዲያፀድቅ በዐቃቤ ህግ ጥያቄ የቀረበለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት  ልደታ ምድብ ችሎት፤ ዛሬ ከሰዓት በሁዋላ  ጉዳዩን በዝግ ችሎት በማየት  የእግዱን ውሳኔ ተቀብሎ  ማፅደቁን አሳውቋል። ይሁንና ችሎቱ መቼ እንደተካሄደ እና ልደታ ስንተኛው ችሎት ውስጥ እንደተካሄደ ሌላው ቀርቶ የጋዜጣው አዘጋጆች እንኳ እንደማያውቁ፤ ወኪላችን ከአዲስ አበባ ያጠናቀረው መረጃ ያመለክታል። ፍትህ፤ጠንካራ ትችቶችን በምክንያታዊ ትንታኔ ...

Read More »

ጋና አዲስ ፕሬዚዳንት ሾመች

ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የ68 አመቱ ጆን አታሚልስ ትናንት ካረፉ በሁዋላ፣ ጆን ማሀማ ፕሬዚዳንት በመሆን ዛሬ ቃለመሀላ ፈጽመዋል። ተቃዋሚዎች ሰላማዊውን የስልጣን ሽግግር ያደነቁ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንቱም ሁሉንም ጋናውያንን በእኩል እንደሚያገለግሉ እና ሁሉም ነገር ሰላም መሆኑን ተናግረዋል። የአለም መሪዎች ለሟቹ ፕሬዚዳንት ያላቸውን አድናቆት እየገለጡ ነው። የላይቤሪያዋ መሪ፣ ፕሬዚዳንቱ የተለየ ስእብና ባለቤት መሆናቸውን ሲናገሩ፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ...

Read More »

በመልጋ ወረዳ በተነሳ ግጭት ከ19 በላይ ፖሊሶች በጽኑ ቆሰሉ

ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት ከአዋሳ ከተማ  በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ  በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ መቁሰላቸውን የዘገብን ቢሆንም፣ ዛሬ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያጠናከረው መረጃ እንደሚያመለክተው ከ19 በላይ ፖሊሶች እና ከ20 በላይ ነዋሪዎች በጽኑ ቆስለዋል። አናታቸው የተፈነከተ ፣ እግራቸው የተሰበረ፣ እንዲሁም በጥይት የቆሰሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገድ ላይ ወድቀው ይታዩ ነበር። ...

Read More »

ሲፒጄ በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተጣለውን እገዳ ኮነነ

ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቀማጭነቱ ኒውዮርክ የሆነው አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት ( ሲፒጄ) በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተጣለው እገዳ በኢትዮጵያው ውስጥ የሚታየው አፈና የደረሰበትን ደረጃ ያሳያል ብሎአል። የሲፒጄ የምስራቅ አፍሪካ ዋና አማካሪ የሆኑት ቶም ሮድስ እንደተናገሩት ” የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የጠቅላይ ሚኒሰትሩን ህመም በተመለከተ ምን ነገር እንዲነገርባቸው አይፈልጉም፣ ይህም በአገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋውን የአፈና መጠን በገሀድ የሚያሳይ ...

Read More »

የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕርትርክና 20ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በሼራተን አዲስ ተከበረ

ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደጀ-ሰላም እንደዘገበው፤የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና ራእይ ለትውልድ ፤  በእንግሊዝኛው አጠራር ፦/Vision for Generation/ የተባለው አካል የጥቅም ትስስር የፈጠሩበት የሼራተኑ በዓለ ሢመት ዝግጅት የተከናወነው፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ይኹን አለያም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት፤ እስካሁን  አልታወቀም። በዚሁ  የአቡነ ጳውሎስ  20ኛ ዓመት  በዓለ-ሢመት ላይ፤ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የአብያተ እምነት መሪዎችን፣ አምባሳደሮችንና ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ  በሺህ ...

Read More »

በኢትዮጵያ 6 የሳዑዲ ዜጎች ታሠሩ

ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ  ባለፈው እሁድ ስድስት የሳኡዲ ዜጎች በሽብርተኝነት ተጠርጥረው መታሰራቸው ተዘገበ። “ ሳዑዲ ጋዜጣ” እንደዘገበው የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ስድስት የ ሳዑዲ ዜጎችን ያሰሩት፦” ሽብርተኝነትን በገንዘብ ትደግፋላችሁ” በማለት ነው። ጋዜጣው እንዳለው የታሰሩት ስድስቱ የሳዑዲት ዓረቢያ ዜጎች  በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ሙስሊሞች ያሉባቸውን ችግር ለመቅረፍ በአዲስ አበባ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ በጎ አድ ራጊዎች ነበሩ። በ አዲስ አበባ የሳኡዲ ...

Read More »

የጋና ፕሬዚዳንት ጆን አታ ሚልስ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፕሬዚዳንቱን ጽህፈት ቤት በመጥቀስ ቢቢሲ እንደዘገበው፤ የ 68 ዓመቱ  ፕሬዚዳንት ጆን አታ   ዛሬ ከቀትር በሁዋላ  ሀመም በተሰማቸው በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ነው  ህይወታቸው ያለፈው። ይሁንና  ፅህፈት ቤቱ ዝርዝር ሁኔታውን ከመግለጽ ተቆጥቧል። “የጋና ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንትን ድንገተኛና ያልተጠበቀ  ሞት ስንገልጽ በጥልቅ ልባዊ ሀዘን ነው” በማለት ነው ፅህፈት ቤቱ የፕሬዚዳንት ሚልስን  ሞት ይፋ ያደረገው። የአፍሪካ የዲሞክራሲ ...

Read More »

የመልጋ ወረዳ ህዝብ ከ ፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ሲጋጭ ዋለ

ሐምሌ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአዋሳ ከተማ  በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ ዛሬ በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ ሲቆስሉ ከህዝቡም በተመሳሳይ ሰዎች ቆስለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ለእረፍት ወደ አካባቢው ከሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር በመሆን፣ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተከሰተውን ችግር እየተወያዩ በነበረት ጊዜ የፌደራል ፖሊስ አባላት  ለመበትን ጥረት በማድረጋቸው ግጭቱ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል ” ...

Read More »