ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በ10 ቀናት ውስጥ ወደ ስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ ከሶስት ሳምንታት በፊት ስህተት እንደነበር አቶ ስብሃት ነጋ ከኢሳት ጋር ባደርጉት ቃለ ምልልስ ገለጹ:: አቶ በረከት ስምኦን ከአዲሱ ዓመት በፊት አቶ መለስ ወደስራ ገበታቸው እንደሚመለሱ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተ ይህንን የሚያረጋግጥም ሆነ የሚአስተባብል መረጃ እንደሌላቸው አመልክተዋል። አንጋፋው ሕወሀት ታጋይ አቶ ስብሀት ነጋ ለስርአቱ ቅርበት ያላቸው ጋዜጦች ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ወደ ሀገር ቤት ...
Read More »የአዜብ መስፍን እህት ሰርግ ተሰረዘ
የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተሰቦች ለመስከረም 10 ታቅዶ የነበረ ሰርግ እንዲሰረዝ ማድረጋቸውን ታማኝ የኢሳት ምንጮች ጠቁመዋል። ከጠቅላ ሚኒስትሩ ደብዛ መጥፋት ጋር በተያያዘ በቤተመንግስት አከባቢ በተፈጠረው ቀውስና ትርምስ የተጨነቁት እነዚሁ የቤተሰብ አባላት የወ/ሮ አዜብ ታናሽ እህት ሶሻል ይልማ ሰርግ ለመሰረዝ መገደዳቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኢሳት ምንጮት ጠቁመዋል። ምንም እንኳ ለዚህ ሰርግ ከፍተኛ ወጪ ተደርጎ ከአሜሪካና ከአውሮፓ ሳይቀር ...
Read More »ሰራዊቱ አሁንም በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ ላይ ነው
የአቶ መለስ ዜናዊን መሰወር ተከትሎ በኢትዮጵያ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ሲሆን፤ ጦር ሰራዊቱ በአንደኛ ደረጃ ተጠንቀቅ እንዲቆም የታዘዘው፤ በቅርቡ በተመሰረተውና በጦር ሰራዊቱ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ውይይት በጫረው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ (ነኢሰን) መግለጫ ጭምርም እንደሆነ አስተማማኝ የውስጥ ምንጭ ገለጸ። ለመከላከያ ሚኒስቴር ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በቅርቡ የተመሰረተበትን መግለጫ የበተነው ነጻ የኢትዮጵያ ሰራዊት ንቅናቄ፤ ከተመሰረተ ግዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ውስጥ ...
Read More »በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ተከስቷል
በኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዝሬ ዕጥረት መፈጠሩን፤ በዚህም ሳቢያ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት መቸገራቸውን፤ ሪፖርተር ጋዜጣ ከአዲስ አበባ ዘገበ:: አሁን ለተከሰተው የውጭ ምንዛሬ እጥረት፤ በሕገ-ወጥ መንገድ ገንዘብ ከሐገር በመውጣቱ እንደሆነ ሪፖርተር ባለሞያዎችን ጠቅሶ አመልክቷል። ኢሳት ያነጋገራቸው የኢኮኖሚክስ ባለሞያ፤ ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻውም፤ ለምንዛሬ እጥረቱ ምክንያት፤ ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ እየወጣ በመሆኑ ነው ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል። በሐገሪቱ የተከሰተውን የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ተከትሎ፤ ዕቃ ወደ ሐገር ...
Read More »የደሴ ሙስሊሞችና መስጅዶች በፌደራል ፖሊሶች እየታመሱ ነው
በደሴ የሚገኙ መስኪዶች በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት እየተበረበሩ መሆኑ ታወቀ። እማኞች መስኪድ ሄዶ ሰግዶ መመለስ የማይታሰብና አሸማቃቂ ተግባር መሆኑንም ዘግበዋል።ምንጯቻችን ከደሴ እንደዘገቡት፤ ካለፈው አርብ ጀምሮ፤ ከ300 የሚልቁ የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት እየተደበደቡ በየእስር ቤቱ ታጉረዋል። ከደሴ ከተማ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉ የደሴ ነዋሪዎች እንደገለጡት፤ የፌደራል ፖሊሶችና የመከላከያ ሰራዊት አባላት፤ ወደ መስጅድ ገብተው ብርበራ ከማድለጋቸውም በላይ፤ ብዙ በመስኪድ የተገኙ ሰዎች ተደብድበው ወደ ...
Read More »የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአረብሳት ላይ እንዲወርድ ተደረገ
ቴሌቭዝን የሳተላይት ስርጭት በኢትዮጵያ መንግስት መታወኩ ታወቀ። ይሄንን ተከትሎም፤ የአረብ ሳት የኤትዮጵያ ቴሌቭዥንን ከሳተላይት ስርጭት አግዷል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሜኒሳቴር ባለስልጣናት፤ አረብ ሳት በኤርትራ ቴሌቭዥን ላይ የሚያካሂደውን የማወክ ተግባር የማስቆም ህጋዊና ተቆማዊ ሀላፊነት እንዳለበት አሳስቧል። አረብ ሳት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ከአየር ከማውረድ ባሻገር የሄደበት ቀጣይ እርምጃ ስለመኖሩ አልታወቀም። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከኧረብ ሳት ከመውለዱ በፊት የኤርትራ ቴሌቭን በሚታወክበት ወቅት ኢቲቪም እብሮ ሲታወክ ቆይቶል። ...
Read More »ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ የሚታየው ገንዘብ የማሸሽ እንቅስቃሴ ንግዱን እየጎዳ የኑሮውን ውድነትም እያባበሰው ነው ተባለ
ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአንድ የግል ባንክ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኛ ለኢሳት እንደገለጡት፣ የተለያዩ የውጭ እና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ባለፉት ሁለት ወራት ከዚህ በፊት ታይቶ ባልታወቀ ሁኔታ ገንዘባቸውን አሽሽተዋል። ይህንኑ ተከትሎም ንግድ ባንክ ለመድሀኒትና መሰረታዊ ለሚባሉት የፍጆታ እቃዎች መግዢያ ካልሆነ በስተቀር ፣ ማንኛውም ነጋዴ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዳይከፍት መመሪያ አስተላልፎአል። እገዳው በአገሪቱ የሚታየው የዶላር እጥረት እስከሚቀረፍ ድረስ ላልተወሰነ ...
Read More »የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በአርማጭሆ ወታደራዊ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ
ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሕአግ በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ልዩ ስሙ አዋሳ በተሰኘ አካባቢ ከመንግስት ልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር ሐምሌ 28-2004 ዓ∙ም ባካሄደው ውጊያ 11 የመንግስት ቡድን ቅጥረኞችን በመግደልና 19 በማቁሰል አንፀባራቂ ድል ማግኘቱን ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል። በእለቱ የግንባሩ ሰራዊት የተለመደውን ታሪካዊ ጀብድ ሲያከናውን የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍና አቀባበልም እንዳደረገለት ገልጧል። ማህበረሰቡ የአርበኛ ግንባር ደጋፊ ነህ በሚል ...
Read More »በማሌዥያ ጫት ይዛ የተገኘችው ኢትዮጵያዊ ተከሰሰች
ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተከለከለ ዕጽ በማዘዋወር የተጠረጠረችው ኢትዮጵያዊቷ የቤት እመቤት ጫት ይዛ በመገኘቷ ትናንትና በፍርድ ቤት ክስ እንደተመሰረተባት የተለያዩ የማሌዥያ የዜና አውታሮች ዘገቡ። የ36 ዓመቷ ሙና መሃመድ ኢብራሂም፣ እ.ኤ.አ ሃሙስ ኦገስት 2/ 2012 የማሌዥያው ኬ.ኤል ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ውስጥ 90 ኪሎግራም የሚመዝን ካቲኖን የተሰኘ እፅ ወይንም ጫት ይዛ በመገኘቷ በቁጥጥር ስር እንደዋለች ታውቋል። ነዋሪነቷ ካናዳ እንደሆነ የተገለፀው ወ/ሮ ...
Read More »በለንድን ኦሎምፒክ የሴቶች 5000 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ የበላይነታቸውን አሳዩ
ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠያይሞቹ ንግስቶች ለንደን ላይ አክሊላቸውን ደፉ።አረንጓዴው ጎርፍ በለንደን ኦሎምፒክ ስታዲየም ፈሰሰ። በሴቶች 5ሺህ ሜትር የ ኦሎምፒክ ውድድር ድንቅ ታሪክ ተሠራ። 1 ኛ ኢትዮጵያ 3ኛ ኢትዮጵያ 5 ኛ ኢትዮጵያ። የ2004 የ ኦሎምፒክ ሻምፒዮን የሆነችው ጀግናዋ መሰረት ደፋር እንደ ልማዷ በመጨረሻው መቶ ሜትር ላይ ፍጥነቷን በመጨመር እና የኢትዮጵያውያን ተቀናቃኝ የሆነችውን- ኬንያዊቷን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ቪቪያን ...
Read More »