የአትዮጵያ መንግስት ሁለቱን የስዊድን ጋዜጠኞች፤ ማርቲን ሽብዬና ዮሀን ፐርሶንን ጨምሮ፤ ለ1900 እስረኞች ምህረት ማድረጉን የተለያዩ አለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ። እስረኞቹ የተለቀቁት የኢትዮጵያን አዲሱን አመት በማስመልከት ባስገቡት የይቅርታ ጥያቄ መሰረት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሞታቸው በፊት፤ በተለይም ለሁለቱ የሰውዊድን ዜጎች ምህርት አድርገው ለአዲስ አመት ሊፈቷቸው እንደነበር ባለስልጣናቱ ገልጸው፤ 1900 እስረኞች በዚህ ሳምንት በሚደረግ የምህረት ስነስርአት እንደሚለቀቁ ...
Read More »ሳውዲ አረቢያ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አገደች
(Sep. 10) የሳኡዲ አረቢያ መንግስት፤ ዜጎቹ ወደኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲገቱ ማስጠንቀቂያ ማስጠንቀቂያ ሰጠ። በአገሪቱ ውስጥ በሙስሊሞችና በፖሊስ መካከከል በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት፤ ግጭቱ እስኪበርድና አገሪቱ ውስጥ ያለው ውጥረት እስኪረግብ ድረስ፤ የሳኡዲ መንግስት፤ ዜጎቹ ወደኢትዮጵያ እንዳይጓዙ እንዳስጠነቀቀ እለታዊው የአረብኛ ጋዜጣ፤ አካዝ ጽፏል። በኢትዮጵያ የሳኡዲአረቢያ አምባሳደር፤ አብዱል በቂ አህመድ አጅላን፤ ከአዲስ አበባ በጻፉት ማስጠንቀቂያ፤ “በረመዳን ወር፤ 7 የሳኡዲ ዜጎች በተለያዩ ስፍራዎች ሲዘዋወሩና የበጎ ...
Read More »በጄነራል ሳሞራ ዩኑስ የሚመሩ የህወሀት አባላት ጀነራሎች የመለስ ቦታ የሚገባው ለኛ ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰማ
ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ሾልከው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ እና በሥራቸው ያሉ የህወሀት ጀነራሎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ብቁ የሆነ ሰው ከነሱ መካከል ስላለ በመለስ ቦታ ምንም ዓይነት ሹመት እንዳይሰጥ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጀነራሎቹ፦“መለስን መተካት የሚችል ብቁ ሰው አለን። ከኛ ፈቃድና ዕውቅና ውጪ ማንም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሾም አይችልም!”ነው ያሉት። የጀነራሎቹ መልዕክትና አቋም መሰማቱን ተከትሎ በኢህአዴግ ...
Read More »ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለ17 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ለዩኒቨርስቲ መምህራን ይሰጣል
ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ድንገተኛ ሞት ተከትሎ በስልጣን ሽኩቻ ውስጥ የሚገኘው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችንና የመንግስት ሰራተኞችን በመጋበዝ፣ ለግንባሩ ያላቸውን ተአማኒነት በይፋ እንዲያረጋገጡ የነደፈው ስትራቴጂ በዩኒቨርስቲ መምህራን ይጀመራል። የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ ዲንሳ በአገሪቱ ለሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በቀጥር 259/2311/04 በቀን 10/12/2004ዓም በላኩት ደብዳቤ ከመስከረም 3 እስከ መስከረም 20 ...
Read More »የኦጋዴን በህራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ከመንግስት ጋር ድርድር ጀመረ
ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ በኬንያው ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ አነሳሽነት በኢህአዴግ መራሹ መንግስትና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር መካከል እኤአ ከመስከረም 6 እስከ 7፣ 2012 ባሉት ቀናት ውስጥ ድርድር ተካሂዷል። ውይይቱ የተመራው በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር የውጭ ጉዳይ ሀላፊ በሆኑት አቶ አብዱራህማን ማሀዲ እና በመከላከያ ሚኒስትሩ ሀሰን ፈርጌሳ መካከል ነው። ውይይቱን የመሩት ደግሞ የኬንያው የእርሻ ሚኒስትር ...
Read More »በ አፍሪካ ቀንድ ከ17 ሚሊዮን በላይ ህዝቦች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ
ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ በአፍሪካ ቀንድ 17 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልጉ ኧስታውቃል። ከፍተኛ እርዳታ ከሚፈልጉት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ይገኙበታል። የአለማቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ4 ሚሊዮን በላይ ህዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚፈልግ በቅርቡ ገልጠዋል። ይህ አሀዝ ከ12 ሚሊዮን በላይ በሴፍቲኔት ...
Read More »የጋንቤላው ተወላጅ እንግሊዝን ሊከሱ ነው
(Sept. 8) ከእንግሊዝ መንግስት በተገኘ ድጋፍ የሰብአዊ መብቴ ተጥሶብኛል ያሉ አንድ የጋምቤላ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ፤ የእንግሊዝ መንግስትን ሊከሱ እንደሆነ ቢቢሲ ዘገበ። ስማቸው ያልተጠቀሰውና በስደተኝነት በኬንያ የሚገኙት ከሳሽ በጠበቆቻቸው በኩል እንደተናገሩት፤ በጋምቤላ አካባቢ በሚካሄድ የሰፈራ መርሀግብር የተነሳ፤ ከመሬታቸው እንደተፈናቀሉና እንደተደበደቡ፤ እንዲሁም ሴቶች ሲደፈሩ እንደተመለከቱ ተናግረዋል። በጋምቤላ አካባቢ የሚደረገው የሰፈራ መርሀግብር፤ የእንግሊዝ አለምአቀፍ የዴቭሎፕመንት ድርጅት መምሪያ የገንዝብ ድጋፍ እንዳለበት ቢነገርም፤ ይህ መምሪያ ግን ...
Read More »የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣን ለማስቀጠል ዘመቻ ተከፈት
(Sept. 8) የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ፤ አቶ ብዙአየሁ ወንድሙ፤ የግድያ ዛቻ እንደደረሰበት ሲናገር፤ እንዳትታም የተከለከለችውን ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ሕትመትና ህልውና ለመቀጠል፤ “ዘመቻ ነፃነት” የተሰኘ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን በአዲስ አበባ የሚገኙት የጋዜጣዋ ዋና አዘጋጆች ገለፀ። ምክትል ዋና አዘጋጁ አቶ ብዙአየሁ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ፤ በብርሃንና ሰላም እምቢታ ላለፉት ሁለት ሣምንታት እንዳትታተም የተከለከለችውን ጋዜጣ ህልውና ለመቀጠል፤ ፍትህ ሚኒስትርን ጨምሮ፤ ለተለያዩ ...
Read More »3.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል
(Sept. 8) ድርቅ አሁንም ለኢትዮጵያ ፈተና ሆኖ እንደሚቀጥልና፤ ከነሀሴ እስከ መጪው ታህሳስ ድረስ፤ 3.7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው፤ የግብርና ሚኒስቴር አቶ ምትኩ ካሳ ገለጡ። ከነሀሴ በፊት በነበሩት ስድስት ወራት ውስጥ፤ የምግብ ተረጂዎች ቁጥር 3.2 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን፤ በቀጣዮቹ 4 ወራት ግን የተረጂዎች ቁጥር 16 በመቶ ጨምሮ፤ በአሁኑ ሰዓትና እስከሚቀጥለው ታህሳስ መጨረሻ፤ የተረጂዎች ቁጥር 3.7 ሚሊዮን እንደሚደርስ፤ የግብርና ሚኒስትሩ መናገራቸውን ...
Read More »በኢህአዴግ ውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ቀጥሏል
(Sept. 9) አቶ መለስ ዜናዊን ለመተካት፤ በኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት መካከል የተፈጠረው ሽኩቻ እንደቀጠለ ሲሆን፤ በመጪው የኢትዮጲያ አዲስ አመት የመጀመሪያ ሳምንት፤ 180 የኢህአዴግ ማእከላዊ ምክር ቤት አባላት፤ ጉዳዩን እልባት ለመስጠት እንደሚሰበሰቡ ለማወቅ ተችሏል። የ4 ፓርቲዎች ግንባር የሆነው ኢህአዴግ፤ ከያንዳንዱ ፓርቲ የተውጣጡ 45 የማእከላዊ ም/ቤት ዓባላት፤ በድምሩ 180 የምክር ቤት አባላት ተሰብስበው ላለፉት ሁለት ሳምንታት ሲያከራክር የቆየውን፤ የኢህአዴግ ሊ/መንበርና፤ የጠ/ሚ/ርነት ቦታን ...
Read More »