የኦጋዴን በህራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ከመንግስት ጋር ድርድር ጀመረ

ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ በኬንያው ፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ አነሳሽነት በኢህአዴግ መራሹ መንግስትና በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር መካከል እኤአ ከመስከረም 6 እስከ 7፣ 2012 ባሉት ቀናት ውስጥ ድርድር ተካሂዷል።

ውይይቱ የተመራው በኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር የውጭ ጉዳይ ሀላፊ በሆኑት አቶ አብዱራህማን ማሀዲ እና በመከላከያ ሚኒስትሩ ሀሰን ፈርጌሳ መካከል ነው።

ውይይቱን የመሩት ደግሞ የኬንያው የእርሻ ሚኒስትር እና የአገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትሩ ናቸው።

ሁለቱም ወገኖች በድርደሩ ሞዳሊቲ ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒሰትሩ አቶ በረከት ስምኦን ገልጠዋል።

ኢሳት ከወራት በፊት በመንግስትና በኦብነግ መካከል ድርድር እንደሚጀመር የኦብነግን አመራሮች በመጥቀስ መዘገቡ ይታወሳል።

በወቅቱ የኦብነግ አመራሮች ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ ቀድም ብሎ ተይዞ የነበረው ድርድር መልኩን ሊለውጥ ይችላል በማለት ተናግረው ነበር ።

የፖለቲካ ምሁራን እንደሚሉት በስልጣን ሽኩቻ ውስጥ የሚገኘው ኢህአዴግ ድርድሩን የህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥ እንደተጠቀመበት ይገልጣሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide