Amsterdam

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር በጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ ላይ የወሰደውን እርምጃ አወገዘ።

ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬዲዮ ጣቢያ ውስጥ ስፖርት አዘጋጅ በመሆን የሚሰራውን ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒን የመስራት ነጻነት በሚጋፋ መልኩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር የጻፈውን ደብዳቤ ተከትሎ ማህበሩ በአባላቱ ሥም የተቃውሞ መልስ ጽፏል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ማህበር ሰኔ 16 ቀን 2009 ዓ.ም በብስራት ሬዲዮ ጣቢያ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን የሚኮንኑ እና ሚዛናዊነት ...

Read More »

አዲሱ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለአራት አገራት 639 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ዕርዳታ ለመስጠት ወሳኔ አሳለፈ:: ልገሳው ኢትዮጵያን አያካትትም።

ሐምሌ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካ መንግስት ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የ639 ሚሊዮን ዶላር በጀት አጽድቋል። ይህም አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አራት አገራት እንደሚውል የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (USAID) አስታውቋል። ከአራቱ አገራት አገራት ውስጥ በዘንድሮው ዓመት ኢትዮጵያ አልተካተተችም። ናይጀሪያ121 ሚሊዮን፣ ደቡብ ሱዳን 199፣ ሶማሊያ 126 ሚሊዮን እና የመን 191 ሚሊዮን ዶላር እያንዳንዳቸው እንደሚያገኙ ...

Read More »

በመላ አገሪቱ ያሉ ነጋዴዎች የእለታዊ ገቢ ግብርን እየተቃወሙ ነው

ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ፣ በባህርዳር፣ በወልድያ፣ በሻሸመኔና በደቡብ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በግምት ላይ የሚጣለውን ግብር በመቃወም ላይ ሲሆኑ፣ በምስራቅ ሃረርጌ በጨለንቆና በጭሮ ከተማ ደግሞ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን አሰምቷል። ነጋዴዎቹ ከገቢያቸው ጋር ያልተመጣጠነ ግብር እንዲከፍሉ መደረጋቸውን የግብር መከፈያ ጽ/ቤትን በመክበብ ሲቃወሙ ውለዋል። ስቱዲዮ በገባንበት ሰአት ወኪላችን ባደረሰን ዘገባ ...

Read More »

ብአዴንን ደግፈን በመታገላቸው እንደሚጸጸቱ የሰቆጣ ነዋሪዎች ተናገሩ

ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዋግ ነዋሪዎች በከተሞች ዙሪያ በተጠራ ስብሰባ ላይ ፣ ድርጅቱ በአካባቢያቸው ተመስርቶ አስፈላጊውን ድጋፍ አድርገውለት ለስልጣን ቢያበቁትም፣ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ግን እንደጠላቸውና እንደረሳቸው ተናግረዋል። “አንዳንድ ጊዜ የትግል ታሪካችንን ለመናገር ስንፈልግ፣ የታላላቅ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ታሪክ እንኳን ለመናገር ስንፈልግ፣ የሚያሸማቅቅ ሁኔታ ነው ያለው” በማለት በድርጅቱ እንደሚያፍሩበት ገልጸዋል። ይህ ህዝብ “ይህንን ድርጅት ደግፎ ...

Read More »

ከሰራዊቱ የተገለሉ ወታደሮች በከፍተኛ ጉስቁልና ውስጥ እንገኛለን በማለት ምሬታቸውን ገለጹ

ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላፉት አስር እና 20 ዓመታት በመላከያ ግንባሮች በትግል ያሳለፉ እና አካላቸውን አጠው የተመለሱ የኢትዮጵያ መከላከያ አባላት፣ በከፈሉት መስዋዕትነት ምንም አይነት ድጋፍ እያገኙ እንዳልሆኑ ባህር ዳር በተካሄደው የመከላከያ ተመላሽ አባላት ውይይት ላይ ተናግረዋል። ከ3 አመታት በፊት ከመከላከያ የተሰናበተ ወታደር፣ “ስንሄድ በከብሮ ተሸኝተን ነበር፣ አሁን ግን ተረስተን በጉስቁልና እየኖርን ነው” በማለት ...

Read More »

በኢትዮጵያ 780 ሰዎች በኮሌራ በሽታ መሞታቸው ታወቀ

ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሌራ ወረረሽኝ በኢትዮጵያ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱንና በበሽታውም 780 ኢትዮጵያዊያንን መግደሉን ወርልድ ቪዥን በጥናታዊ ሪፖርቱ አስታውቋል። ከሚያዝያ አጋማሽ እስከ ግንቦት አጋማሽ 2017 እ.ኤ.አ. በተደረገ ጥናት በኢትዮጵያ የኮሌራ ወረሽኝ አድማሱን እያሰፋ ነው። በግንቦት ወር መጨረሻ ላይ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሊያ ክልሎች በአጠቃላይ 567 የነበረው የኮሌራ ተጠቂዎች ቁጥር፣ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ...

Read More »

39 የአውሮፓ የፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በገለልተኛ አካል ምርመራ እንዲደረግበት ጠየቁ

ሐምሌ ፬ ( አራት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ሲሉ፣ 39 የአውሮፓ ፓርላማ አባላት በፊርማቸው ለህብረቱ ፓርላማ ጥሪ አቅርበዋል። በገዥው ፓርቲ የሚመራው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ ያወጣው የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ግልጽነት እና ተአማኒነት የጎደለው ነው ሲሉ የፓርላማ አባላቱ ተችተዋል። የፓርላማ አባላቱ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በኦሮሞ ...

Read More »

ህዝባዊ አመጹ ሊደገም ይችላል የሚል ስጋት አለ

ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር እና ጎንደር ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴው ይጀመራል የሚል ስጋት መኖሩን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች በሸማቾች ተጣበው ታይተዋል። ዘጋቢያችን ከስፍራው በላከው መረጃ በቅርብ ቀናት አገዛዙ በወልቃይት ዙሪያ ለአመታት ምላሽ ሳይሰጥ የንፁሐንን ደም አፈስሶ በዜጎች ቤት ሀዘን ካስቀመጠ አመታት ሊደፍን ወራት በቀሩት በዚህ ጊዜ፣ አገዛዙ ላይ አጣነው ባሉት ...

Read More »

በትግራይ ድንበር የሚገኙ አርሶ አደሮች የባቡር መሬት ካሳ ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ፡፡

ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጅቡቲ ወደ መቀሌ በሚዘረጋው የባቡር መስመር እርሻ ቦታቸውን የተነጠቁ አርሶ አደሮች “ተገቢውን የመሬት ካሳ እንከፍላችኋለን” ቢባሉም ለሶስት አመታት ምንም ዓይነት የካሳ ክፍያ ባለማግኘታቸው ከነቤተሰቦቻቸው ችግር ላይ መውደቃቸውን ገለጹ፡፡ በአማራ ክልል ቆቦ አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች በተለይ ለሪፖርተራችን እንደገለጹት፤ከመቀሌ እስከ ትግራይ ድንበር ድረስ ለሚገኘው አካባቢ ደረቅ መሬት በማለት የመሬት ካሳ ...

Read More »

የወልድያ ህዝብ የእለት ገቢ የግብር ተመንን ተቃወመ

ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወልድያ ትናንት የእለት ገቢን ምክንያት አድርጎ የተጣለውን ግብር ለመቃወም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በወልድያ የስብሰባ አዳራሽ የተገኘ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይም ተቃውሞውን በከፍተኛ ስሜት አቅርቧል። ወኪላችን እንደገለጸው ህዝቡ ስብሰባ እንዳለ በማወቁ በብዛት የወጣ ሲሆን፣ አዳራሽ በመሙላቱ ስብሰባውን በውጭ ሆኖ እስከ መከታተል ደርሷል። ህዝቡ “ እኛን ገድላችሁ፣ ማንን ልትገዙ ነው? ዜጎችን ...

Read More »