ህዝባዊ አመጹ ሊደገም ይችላል የሚል ስጋት አለ

ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር እና ጎንደር ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴው ይጀመራል የሚል ስጋት መኖሩን የገለጸው ዘጋቢያችን፣ ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች በሸማቾች ተጣበው ታይተዋል።
ዘጋቢያችን ከስፍራው በላከው መረጃ በቅርብ ቀናት አገዛዙ በወልቃይት ዙሪያ ለአመታት ምላሽ ሳይሰጥ የንፁሐንን ደም አፈስሶ በዜጎች ቤት ሀዘን ካስቀመጠ አመታት ሊደፍን ወራት በቀሩት በዚህ ጊዜ፣ አገዛዙ ላይ አጣነው ባሉት እምነት የባህር ዳር እና ጎንደር ከተማ የህዝባዊ አመፅ አመራሮች፣ በህቡዕ አስተላለፉት የተባለውን መልዕክት ተከትሎ የባህር ዳር እና ጎንደር ገበያዎች በእለታዊ ምግብ ፍጆታዎች ግዥ ተጣበው ተስተውለዋል፡፡
በባህር ዳር እና ጎንደር መንግስትን በማገዝ የወልቃይትን የማንነት ጥያቄ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በመንግስት ወታደሮች የሞቱበት ህዝባዊ አመጾች የተካሄዱበት አመት ሊሆን ቀናት ቀርተውታል፡፡
በአማራና ኦሮምያ ተደርጎ በነበረው ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ከ1 ሺ በላይ ዜጎች ተገድለዋል። በአስር ሺ የሚቆጠሩት ታስረዋል። ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ፣ ፕ/ር መረራ፣ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ታስረዋል።
ለሁለት ተከታታይ ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢታወጅም፣ አሁንም ሙሉ በሙለ መረጋጋት ማስፈን አልቻለም።
በተለይ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በመሳሪያ የተደረገ የትጥቅ ትግል በመካሄዱ ህዝቡ ለከፍተኛ ችግር ተደርጓል። የመጀመሪያውን የህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ የመሩት ሰዎች በእስር እየማቀቁ ቢሆንም፣ አዳዲስ ወጣቶች አሁንም ህዝባዊ አመጽ ለማካሄድ እየሰሩ ነው።