ኢሳትና የአሜሪካ ድምጽን በፍርድ ቤት ለመክሰስ በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ማህበር ውሳኔ አሳለፈ (ኢሳት ዜና የካቲት 7 ቀን 2010ዓ/ም) የትግራይ ተወላጆች ማኅበር በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ እኤአ ጃንዋሪ 27 ቀን 2018 ባደረጉት ስብሰባ፣ ኢሳትና ቪኦኤ አማርኛ ዝግጅት ክፍል በቀጥታና በተዘዋዋሪ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም የሚያደርጉ በመሆናቸው ሕጋዊና ዲፕሎማሲዊ ዘመቻ እንዲደረግባቸው ሲል ውሳኔ አሳልፏል። የማኅበሩ አባላት በመላው ኢትዮጵያ በሚኖሩ የትግራይ ...
Read More »Amsterdam
በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ለሁለተኛ ቀን በመካሄድ ላይ ያለው የስራ ማቆም አድማ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎአል
(ኢሳት ዜና የካቲት 6ቀን 2010ዓ/ም) በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ለሁለተኛ ቀን በመካሄድ ላይ ያለው የስራ ማቆም አድማ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎአል በአንዳንድ አካባቢዎች ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል። ከዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ተነስተው ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚጓዙ መንገደኞች በትራንስፖርት እጥረት መጓዝ ሳይችሉ ቀርተዋል። የንግድ እቃዎችን የጫኑ መኪኖች በየቦታው ቆመዋል። በአዲስ አበባ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል ወታደሮች በተጠንቀቅ ቆመው ማንኛውንም እንቅስቃሴ ...
Read More »አቶ በቀለ ገርባና 6 ጓደኞቻቸው ከእስር ተለቀቁ
(ኢሳት ዜና የካቲት 6ቀን 2010ዓ/ም) አቶ በቀለ ገርባና 6 ጓደኞቻቸው ከእስር ተለቀቁ ባለፉት 2 ቀናት በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች የተደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ የኦፌኮ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባ ፣ ጉርሜሳ አያና፣ አዲሱ ቡላላ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ ጌቱ ጋሩማ፣ ተስፋዬ ሊበን እና በየነ ሩዳ ከእስር ተፈተዋል። ሰሞኑን ችሎት በመድፈር የአንድ አመት እስር የተፈረደባቸው እነ አቶ በቀለ ገርባ፣ ፍርዳቸውን ሳይጨርሱ መፈታታቸው ውሳኔውን ላስተላለፉት ዳኞች ...
Read More »በማላዊ 50 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተያዙ
(ኢሳት ዜና የካቲት 6ቀን 2010ዓ/ም) በማላዊ 50 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተያዙ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ወደ ግዛቴ ገብተዋል ያለቻቸውን 50 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የማላዊ የስደተኞች ጉዳይ አስታወቀ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችን ሳያሟሉ ሰኞ እለት በሰሜናዊ የማላዊ ግዛት ሲገቡ መያዛቸውን የስደተኞች ጉዳይ ቃል አቀባይ የሆኑት ፍራንሲስ ቺቲንቡሊ ገልጸዋል። ስደተኞቹ እድሜያቸው በአማካኝ ከ15 እስከ 40 ዓመት የሚገመቱ ሲሆን ሚቢያ ከሚባለው የታንዛኒያ ...
Read More »ገዢው ፓርቲ በነጋዴዎች እየቀረበ ያለውን ጥያቄ ወደ ጎን በማለት “የበቀል እርምጃ” እየወሰደ ነው ሲሉ ነጋዴዎች ተናገሩ
ሐምሌ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት 2 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየውን የነጋዴዎች አድማ ተከትሎ፣ ገዢው ፓርቲ “ችግሩን በውይይት እፈታለሁ” በማለት በየስብሰባዎች ቃል እየገባ ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን እንዲከፍቱ ለማግባባት ሲሞክር ከቆየ በሁዋላ ወደ በቀል እርምጃ መግባቱን ነጋዴዎች ይገልጻሉ። የሞጣ ከተማ ባለስልጣናት ሰሞኑን በተከታታይ ባደረጉት ስብሰባዎች ለነጋዴዎች ጥያቄ አጥጋቢ መልስ እንደሚሰጡ ሲገልጹ ቢቆዩም፣ ዛሬ ለነጋዴዎች ያላቸውን ንቀትና ...
Read More »ደም አፋሳሽ ሆኖ የቀጠለውን የጉጂ ዞን ግጭት የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስነሱት ነዋሪዎች ተናገሩ
ሐምሌ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና እስከ 1 ሺ የሚጠጉ ቤቶች መቃጠላቸውን የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱን የጉጂ ዞን ባለስልጣናት እንዳስነሱት ይገልጻሉ። ኢሳት በተከታታይ ያቀረባቸው ዜናዎች የአንድን ወገን መረጃ ብቻ ማእከል ያደረገ ነው በማለት ቅሬታቸውንም አቅርበዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ግጭቱ የጉጂ ዞን ባለስልጣናት በደቡብ ክልል ...
Read More »አቶ ዳንኤል ሺበሺ ነጻ ተባሉ ሐምሌ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከተፈቱ በሁዋላ ይግባኝ የተጠየቀባቸው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ም/ል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና የደቡብ ክልል ተወካይ በመሆን ሲያገልግሉ የነበሩት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ፍርድ ቤት ዛሬ ነጻ ያላቸው ሲሆን፣ ሌላው ይግባኝ የተጠየቀባቸው የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ “ ...
Read More »ከእለታዊ ግብር ጋር በተያያዘ የተጀመረው የነጋዴዎች አድማ በምስራቅ ጎጃምና በምስራቅ ሃረርጌ ቀጥሎ ዋለ
ሐምሌ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገቢያችንንና ኑሮአችንን ያላገናዘበ የግምት ግብር ይቀየርልን በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ነጋዴዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ላለፉት 2 ሳምንት ድርጅቶቻቸውን በመዝጋት ሲያደርጉ የነበረውን አድማ ዛሬም ቀጥለዋል። ለተከታታይ አምስት ቀናት አድማውን እያደረጉ ካሉት ከተሞች መካከል የምስራቅ ጎጃሟ ሞጣ አንዷ ስትሆን፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን እንዲከፍቱ ጉልበትን ጨምሮ የተለያዩ ማስፈፋሪያዎችን ተግባራዊ ቢያደርጉም ነጋዴዎች ...
Read More »በመከላከያ ላይ ሲደረግ የነበረው የሙስና ምርምራ መታፈኑ ታወቀ
ሐምሌ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት ውስጥ በመከላከያና በደህንነት ሃይሉ መካከል የተነሳውን የቆየ ልዩነት ተከትሎ የደህንነት ሃይሉ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በመከላከያ ውስጥ የተፈጸመውን ሙስና በማጣራት፣ የተወሰኑ ቡድኖችን ለመምታት የተደረገው ሙከራ ፣ ምርምራው እንዲታፈን መደረጉን ምንጮች ገለጹ። መረጃ የሰጡ የተለያዩ ሰዎች መታሰራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ የሚመራው መከላከያና በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት መስሪያ ...
Read More »በአገር ሽማግሌ ስም መቀሌ ከሄዱት መካከል 4ቱ የተባረሩ የአርበኞች ግንቦት አባላት የነበሩ ናቸው
ሐምሌ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የአማራ እና የትግራይን ህዝብ እናስታርቃለን በማለት ወደ መቀሌ ከተጓዙ፣ የአገር ሽማግሌ ስም ከተሰጣቸው ሰዎች መካከል አራቱ በአርበኞች ግንቦት7 ስር ተደራጅተው ሲሰሩ የነበሩና በሁዋላ ላይ ህወሃት በሰላይነት እንዲያገለግሉት እንደመለመላቸው ሲታወቅ የተባረሩ ናቸው። አቶ ታያቸው ጥሩነህ፣ አቶ ሞላ መኮንን፣ አሰማራው መኮንን እና ሻንቆ ሽባባው የተባሉትን በመድረክ ላይ ...
Read More »