በማላዊ 50 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተያዙ

(ኢሳት ዜና የካቲት 6ቀን 2010ዓ/ም) በማላዊ 50 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተያዙ
ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ወደ ግዛቴ ገብተዋል ያለቻቸውን 50 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የማላዊ የስደተኞች ጉዳይ አስታወቀ።
ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችን ሳያሟሉ ሰኞ እለት በሰሜናዊ የማላዊ ግዛት ሲገቡ መያዛቸውን የስደተኞች ጉዳይ ቃል አቀባይ የሆኑት ፍራንሲስ ቺቲንቡሊ ገልጸዋል። ስደተኞቹ እድሜያቸው በአማካኝ ከ15 እስከ 40 ዓመት የሚገመቱ ሲሆን ሚቢያ ከሚባለው የታንዛኒያ ግዛት ጀልባ ተከራይተው ወደ ማላዊ ኒካታ አውራጃ የባህር ዳርቻ ይጓዙ ነበር።
”ማንነታቸው የማይታወቅ ሕገወጥ ስደተኞች በሃይቅ ላይ በጀልባ ተጭነው እየሄዱ መሆኑን