Amsterdam

በሽንሌ ዞን እስርና ድብደባው እንደቀጠለ ነው

በሽንሌ ዞን እስርና ድብደባው እንደቀጠለ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮ-ሶማሊ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የክልሉ የልዩ ሃይል አባላት በርካታ ወጣቶችን እየያዙ አስረዋል። ብዙዎችም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ብዙዎቹ ወደ ጅግጅጋ ተወስደው የታሰሩ ሲሆን፣ በእስር ቤት ውስጥም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። በሽንሌ ከተማ በእስር ላይ የሚገኘው የወጣት አብዲ ሙሚን ሃሰን ቤተሰቦች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ካለፉት አርብ ጀምሮ ድሬደዋን ጨምሮ በተለያዩ የክልሎ ...

Read More »

ኢንሳ አሁንም ትርምስ ላይ ነው

ኢንሳ አሁንም ትርምስ ላይ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) ኢንሳን ለረጅም ጊዜ ሲመሩ የነበሩት ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/አረጋዊ ከለቀቁ በሁዋላ ስልጣናቸውን በሚለቁ የህወሃት ባለስልጣናት ቦታ ሌሎች አዳዲስ ሰዎች እየተተኩ ነው። የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሰዎችን እየሾሙ መሆኑን የደረሱን የሹመት ደብዳቤዎች ያመለክታሉ። ህወሃቶች በርካታ የስለላ መሳሪያዎችን ወደ መቀሌ የወሰዱ ሲሆን፣ ከ10 ያላነሱ ...

Read More »

በአማራ ክልል በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ንብረት መባከኑን ተጋለጠ፡፡

በአማራ ክልል በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ንብረት መባከኑን ተጋለጠ፡፡ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) የምክር ቤቱን አባላት ያነጋገረና ከፍተኛ ጥያቄ ያስነሣ የ2010 ዓ.ም የክዋኔ ኦዲት የስድስት የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የኦዲት ግኝት ይፋ ተደርጓል፡፡ ዋና ኦዲተሩ ረዳት ፕሮፌሠር ገረመው ወርቁ ለምክር ቤቱ ዘጠነኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ጥሬ ገንዘብና ንብረት መባከኑን ተናግረዋል፡፡ ዋና ኦዲተር ...

Read More »

በኢትዮ ሶማሊ ለሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ህዝቡ ድጋፉን እንዲሰጥ ተጠየቀ

በኢትዮ ሶማሊ ለሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ ህዝቡ ድጋፉን እንዲሰጥ ተጠየቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ተወላጆች እንደገለጹት በክልሉ የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ እየቀጠለ በመሆኑ ከክልሉ ተወላጆች ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጠይቀዋል። ህዝባዊ እንቅስቃሴው ከተጀመረ በሁዋላ በርካታ የክልሉ ተወላጆች ተይዘው ታስረዋል። የአብዲ ኢሌን ጭካኔ የተሞላበት አገዛዝ ለመቃወም በውጭ አገር የተቋቋመው ዱል ሚዲድ አባላት ናቸው የተባሉ ወላጆች እና ቤተሰቦች እየተያዙ ...

Read More »

የአምቦ ተማሪዎች ባነሱት ተቃውሞ ተማሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ

የአምቦ ተማሪዎች ባነሱት ተቃውሞ ተማሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ/ም)ተማሪዎቹ በእስር ላይ የሚገኙ ጓደኞቻቸው እንዲፈቱ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ወታደሮች አስለቃሽ ጥይት በመተኮስ በትነዋቸዋል። በተኩሱ አንድ የጎንደር እና ሁለት የአምቦ ተወላጆች ተጎድተዋል። አንደኛው ተማሪ ከሆስፒታል የወጣ ሲሆን፣ ሁለቱ ግን አሁንም በህክምና ላይ ናቸው። ተማሪዎች ጥያቄያቸው ካልተመሰለ በስተቀር ተቃውሞአቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። አምቦ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የለውጥ እንቅስቃሴ ...

Read More »

የዳባት ከተማ ነዋሪዎች የወልቃይት ጉዳይ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ጭምር ነው አሉ

የዳባት ከተማ ነዋሪዎች የወልቃይት ጉዳይ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ጭምር ነው አሉ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ/ም) “የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት የአማራ ድንበር ተከዜ ነው። የድንበሩ ጉዳይ ፖለቲካዊ ውሳኔ ሊሰጠው ይገባል” ብለዋል። የዳባት ህዝብ ከመንግስት አንዳች ጥቅም አግኝቶ አያውቅም፡፡ለሃያ ሰባት ዓመታት ያለአንዳች እገዛ ህብረተሰቡ እርስ በእርሱ እየተረዳዳና በአካባው ካሉ ህዝቦች ጋር እየተሸማገለ የሚኖር እንጅ በገዥው መንግስት ፍትህ አግኝቶ እንደማያውቅ ነዋሪዎች ...

Read More »

በባቡር ፕሮጀክት ሥም የመስኖ መሬታቸውን ካለተመጣጣኝ ክፍያ መነጠቃቸውን የተሁለደሬ ወረዳ የጎበያ 012 ቀበሌ አርሶ አደሮች ተቃወሙ

በባቡር ፕሮጀክት ሥም የመስኖ መሬታቸውን ካለተመጣጣኝ ክፍያ መነጠቃቸውን የተሁለደሬ ወረዳ የጎበያ 012 ቀበሌ አርሶ አደሮች ተቃወሙ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 18 ቀን 2010 ዓ/ም) ነዋሪነታቸው በደቡብ ወሎ ዞን በተውለደሬ ወረዳ 012 ቀበሌ ልዩ ቦታው ጎበያ ገ/ማኅበር በመባል በሚጠራው ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች በመስኖ የሚለማ መሬታቸውን በባቡር መንገድ ዝርጋታ ምክንያት በርካሽ ዋጋ እንዲለቁ መደረጋቸውን 34 አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ተቃውሞ አሰምተዋል። አርሶ አደሮቹ ...

Read More »

የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከእስር ከተፈቱት ታዋቂ ሰዎችና ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተነጋገሩ

የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ከእስር ከተፈቱት ታዋቂ ሰዎችና ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋር ተነጋገሩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጓቾችና ጋዜጠኞች ጋር ተወያይተዋል። ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉት ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ዙሪያ እና አገሪቱ መውሰድ ስለሚገባት እርምጃ አስተያቶችን ሰብስበዋል። በገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት ወደ ...

Read More »

በሺኒሌ ዞን ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎች በገፍ እየታሰሩ ነው

በሺኒሌ ዞን ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎች በገፍ እየታሰሩ ነው (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) በረባራት እየተባሉ የሚጠሩ ወጣቶች በአቶ አብዲ ኢሌ አገዛዝ በመማረር የጀመሩትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። በርካታ ወጣቶች በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የገለጹት ምንጮች፣ የእስር ዘመቻው ተጠናክሮ በመቀጠሉ አካባቢው በውጥረት እንደሚሞላ አድርጎታል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በአካባባቢው በማሰማራት ተቃውሞውን ለማፈን ጥረት መደረጉን የአካባቢው ...

Read More »

“አገራችን በጥሩ እጅ ላይ ወድቃለች” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ

“አገራችን በጥሩ እጅ ላይ ወድቃለች” ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ይህን የተናገሩት በቤተመንግስት የመሸኛ ዝግጅት በተደረገላቸው ወቅት ነው። አቶ ሃይለማርያም ለአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ያላቸውን አድናቆት ከገለጹ በሁዋላ በአገሪቱ እየነፈሰ ያለው የለውጥ ንፋስ ህዝቡ በሚፈልገው መሰረት እንዲከናወን ከፍተኛ ትግል ያስፈልጋል ብለዋል። “በአሁኑ ወቅት የለውጥ ንፋስ እየነፈሰ ነው፡፡ ለውጡ የሁላችንንም ፍላጎት ያማከለ እንዲሆን ልንረባረብ ...

Read More »