በሽንሌ ዞን እስርና ድብደባው እንደቀጠለ ነው

በሽንሌ ዞን እስርና ድብደባው እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 22 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮ-ሶማሊ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የክልሉ የልዩ ሃይል አባላት በርካታ ወጣቶችን እየያዙ አስረዋል። ብዙዎችም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ብዙዎቹ ወደ ጅግጅጋ ተወስደው የታሰሩ ሲሆን፣ በእስር ቤት ውስጥም ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።
በሽንሌ ከተማ በእስር ላይ የሚገኘው የወጣት አብዲ ሙሚን ሃሰን ቤተሰቦች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። ካለፉት አርብ ጀምሮ ድሬደዋን ጨምሮ በተለያዩ የክልሎ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄደዋል።