በአማሮ ወረዳ እና በጉጂ መካከል እንደገና ግጭት በማገርሸቱ የሰዎች ሕይወት አለፈ (ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) በድንበር በማካለል ስም የተነሳውና ለአንድ አመት ያክል የዘለቀው በአማሮ ወረዳ በሚኖሩ የኮሬ ብሄረሰብና በጉጂ ኦሮሞ መካከል የተከሰተው ግጭት ዛሬ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን፣ ዛሬ ከዲላ ወደ አማሮ ኤፍ.ኤስ.አር የጭነት መኪና ሲያሽከረክር የነበረ፣ በጀሎ ቀበሌ ቅዱስ ዮሃንስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት የታጠቁ ሃይሎች ተኩስ ...
Read More »Amsterdam
በሃረር ወጣቶችን እርስ በርስ ለማጋጨት የተደረገው ሴራ ከሸፈ
በሃረር ወጣቶችን እርስ በርስ ለማጋጨት የተደረገው ሴራ ከሸፈ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወኪላችን እንደገለጸው ጠ/ሚ አብይ አህመድን ለመደገፍ፣ በኢንጂኒየር ስመኛው ሞት ሃዘናቸውን ለመግልጽ እንዲሁም የአሟሟታቸው ሁኔታ በፍጥነት ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ለመጠየቅና ጄ/ል አብርሃ የምስራቅ እዥ አዛዥ በነበሩበት ወቅት ታፍነው የተወሰዱትን የአቤል ፈቃዱ ወይም አቤል ኩባ እና የደረጀ ሙሉጌታ ሁኔታ ለህዝብ እንዲገለጽ ለመጠየቅ የወጡ ፋኖና ...
Read More »ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሲፈፀምባቸው የነበሩት አራት የፌደራል ማረሚያ ቤት አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደረገ
ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሲፈፀምባቸው የነበሩት አራት የፌደራል ማረሚያ ቤት አመራሮች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደረገ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) በህግ ጥላ ስር ያሉ ፍርደኛ እስረኞችን በመቀበል የቅጣት ጊዜያቸውን እስኪፈፅሙ ድረስ በማቆያነት የተቋቋሙት ማረሚያ ቤቶች ከፍተኛ የመብት ጥሰት ሲፈፀምባቸው ቆይቷል። ከማእከላዊ ምርመራ ሰቆቃ የተረፍትን ታራሚዎች በመቀበል ኢሰብዓዊ የመብት ጥሰቶች በመፈፀም የሚታወቁት የቂሊንጦ፣ የድሬዳዋ፣ የሸዋሮቢትና የቃልቲ ማረሚያ ቤት ...
Read More »ላለፉት 12 አመታት በህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ በኃይል ተዘግተው ከነበሩት የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ።
ላለፉት 12 አመታት በህወሀት ኢህአዴግ አገዛዝ በኃይል ተዘግተው ከነበሩት የነፃው ፕሬስ ቢሮዎች መካከል አንዱ የነበረው የእነ እስክንድር ቢሮ ዳግም ተከፈተ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ካለፉት ስድስት ዓመታት እስር በኋላ በቅርቡ ከእስር የተፈታው ጋዜጠኛ እስክንድር በአጭር ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የሚዲያ ውጤቶች ከህዝቡ ጋር ለመገናኘት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል.። የእስክንድ ቢሮ ከ12 ዓመታት በኋላ ሲከፈት ጋዜጠኞች እና ...
Read More »‹ከእኔ ክስና እስራት በስተጀርባ በመንግሥት ውስጥ ጡንቻቸው የጠነከረ ማፊያዎች ነበሩ›› ሲሉ የቀድሞው የገቢዎች ሚኒስትር ገለጹ።
‹ከእኔ ክስና እስራት በስተጀርባ በመንግሥት ውስጥ ጡንቻቸው የጠነከረ ማፊያዎች ነበሩ›› ሲሉ የቀድሞው የገቢዎች ሚኒስትር ገለጹ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) የቀድሞ ሚኒስትር አቶ መላኩ ፋንታ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሙስና ሰበብ ለእስር የተዳረጉት የአሠራር ስህተቶችን ሲያዩ በመቃወማቸውና ሹመኞችን ሙስና አላስበላም በማለታቸው እንደሆነ በስፋት ዘርዝረዋል። በአቶ በረከት ስምኦን ባለቤት ስም ከውጭ አገር የገባ የፊልም ካሜራ እንዲወረስ ...
Read More »በቶሪኖ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን የመደመር ቀንን በጋራ አከበሩ
በቶሪኖ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን የመደመር ቀንን በጋራ አከበሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) ነዋሪነታቸውን በጣሊያኗ ቶሪኖ ከተማ ያደረጉ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን በጋራ በመሆን የመደመር ቀንን በአዳራሽ ውስጥ በማክበር ለሰላም ጥሪው አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ላለፍት ሃያ ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ አገራት ግንኙነት በሰላም እንዲፈታ በተሾሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድንና አጋሮቻቸውን ...
Read More »ጠ/ሚ አብይ አህመድና ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአጭር ጊዜ ተገናኝተው ተነጋገሩ
ጠ/ሚ አብይ አህመድና ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለአጭር ጊዜ ተገናኝተው ተነጋገሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ) አሜሪካ የሚገኙት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። ለአንድ ሰዓት ያክል የነበራቸው ግንኙነት የትውውቅ እንደነበረና ተጨማሪ ውይይቶችን እንደሚያካሂዱ ታውቋል። አርበኞች ግንቦት7 መሰረታዊ የሆኑ የዲሞክራሲ ተቋማት እንዲገነቡ ላለፉት 10 አመታት ትግል ሲያካሂድ ቆይቷል። ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ...
Read More »ኢትዮጵያውያን በኢንጂነር ስመኛው በቀለ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን እየገለጹ ነው
ኢትዮጵያውያን በኢንጂነር ስመኛው በቀለ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን እየገለጹ ነው ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ዜጎች በአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስ በኢንጂነር ስመኛው ሞት የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ፣ የኢንጂኒሩ አሟሟት ሁኔታ በፍጥነት ተጣርቶ ለህዝብ እንዲገለጽ እየጠየቁ ነው። በጎንደር ከተማ ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጥተው ተቃውሞአቸውን የገለጹ ቢሆንም፣ የከተማው የአገር ሽማግሌዎች ወጣቶችን በመምከር አረጋግተዋቸዋል። በባህርዳርና በደሴ እንዲሁ ...
Read More »በአወዳይ አንድ ታጣቂ የነበረ ግለሰብ 3 ሰዎችን ገደሎ 5 ሰዎችን ደግሞ አቆሰለ::
በአወዳይ አንድ ታጣቂ የነበረ ግለሰብ 3 ሰዎችን ገደሎ 5 ሰዎችን ደግሞ አቆሰለ:: ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም )ሃሙስ እለት ከአስተዳደር ጥበቃ ስራ የተባረረው ከድር ኢብራሂም የተባለው ታጣቂ በህዝቡ ላይ ጥይት በመተኮስ 3 ሰዎችን ወዲያውኑ ሲገድል 5 ሰዎች ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። ህዝቡ በወሰደው እርምጃም ሰውዬው በአሰቃቂ ሁኔታ መገደሉ ታውቋል። ግለሰቡ ከስራ ከተሰናበተ በሁዋላ ታጥቆት የነበረውን የጦር ...
Read More »የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ከነገ ጀምሮ ኤርትራን ይጎበኛሉ።
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ከነገ ጀምሮ ኤርትራን ይጎበኛሉ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 20 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአፍሪቃ ቀንድ በቅርቡ እየተስተዋሉ ያሉ የፖለቲካ አሰላለፍና የዲፕሎማሲ ለውጦችን ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ ከነገ ጀምሮ በኤርትራ የሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ያደርጋሉ። የኤርታራው ማስታወቂያ ሚኒስትር በትዊተር ገጻቸው እንደገለጹት የሶማሊያ ሪፐብሊክ መሪ የሆኑት ፕሬዚዳንት ፎርማጆ ኤርትራን የሚጎበኙት፣ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብዣ መሰረት ነው። በዚህም መሰረት ...
Read More »