.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአባይ ግድብ መዋጮ አሁንም ሰራተኛውን እያስመረረ ነው

መስከረም ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የሞግዚት አስተዳደር ሰሞኑን ማንኛውም ሰራተኛ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በድጋሚ የወር ደሞዙን በአመት እንዲከፍል ያወጡት ትእዛዝ የመንግስት ሰራተኛውን እያስመረረ ነው። የኑሮ ውድነቱ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት የአቶ መለስን ራእይ ለማሳካት በሚል የተጣለው አዲስ የመዋጮ ኮታ ፣ የህዝቡን ስቃይ ማባባሱን ነው ዘጋቢያችን ከባህርዳር የገለጠው። በሌላ በኩል ደግሞ የግብርና ሚኒስቴር በእርሻ ስራ ...

Read More »

ናዝሬት በንጹህ ውሃ እጦጥ ችግር ላይ ነች

ላለፉት 22 ቀናት በውሃ እጦት የሚሰቃዩት የናዝሬት ከተማ ነዋሪዎች: አሁንም የውሃ አቅርቦታቸው እንዳልተመለሰ ታወቀ:: ከስፍራው ያገኘነው ዜና እንደሚያመለክተው፤ ትላንት እሁድ ውሃ ይኖራል ተብሎ ተስፋ ቢደረግም እስከ ዛሬ ድረስ ውሃ እንዳልመጣ ታውቋል:: ከአዲስ አበባ 100 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኘው የናዝሬት ከተማ፤ 500 ሺህ አካባቢ ነዋሪዎች ያላት፤ ከኢትዮጵያ 2ኛዋ ትልቅ ከተማ ስትሆን፤ ባለፈው ነሐሴ 20 በቆቃ ግድብ ውሃ የሚያስተላልፈው ቧንቧ በጎርፍ ተጠርጎ ...

Read More »

ተስፋ የወጣቶች ድርጅት በኢትዮጵያ በራሪ ወረቀቶ በተነ

(Sept. 17) የኢትዮጵያ ተስፋ ወጣቶች ድርጅት የተሰኘ አገር በቀል ስብስብ፤ በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች ከ25 ሺህ በላይ ቀስቃሽና ኢህአዴግ ሰራቸው የሚላቸውን ጥፋቶች የሚዘረዝሩ በራሪ ወረቀቶችን በተነ። በተለይ ለኢሳት የደረሰው ዜና እንደሚያመለከተው፤ ድርጅቱ በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነ መልኩ፤ በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች፤ የኢትዮጵያ ህዝብን ለትግል የሚቀሰቅሱ ወረቀቶችን መበተኑን አስታወቋል። ከሌሎች ምንጮቻችን ማረጋገጥ እንደቻልነው በአዲስ አበባ በላፍቶ ክ/ከ በአዲሱ ገበያ፤ በኮልፌ፤ ፒያሳና፤ ሽሮ ...

Read More »

ሀይለማሪያም ደሳለኝ ሳይጠበቅ ሶማሊያ ሄዱ

አዲሱ የኢህአዴግ ሊ/መንበርና የወደፊቱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ፤ ትናነት ወደሶማሊያ ማቅናታቸው ታወቀ። አቶ ሀይለማሪያም በኢህአዴግ ሊ/መንበርንት ከተመረጡ የመጀመሪያቸው በሆነው የውጭ አገር ጉብኝታቸው ወደሞቃዲሾ ያመሩት፤ በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት በዓለ-ሲመት ላይ ለመገኘት መሆኑ ታውቋል። የሶማሊያ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት፤ ባለፈው ጳሁሜ 5 ቀን ሀሰን ሼክ መሀመድን ፕሬዚዳንት አድርጎ መምረጡ የሚታወቅ ሲሆን፤ በአዲሱ ፕሬዚዳንት ቃለመሀላ ስነስርት ላይ አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ፤ ሌሎች የጎረቤት አገሮች ...

Read More »

እስክንድር ነጋ የታሰረበት ፩ኛ አመት ታሰቦ ዋለ

(Sept. 17) ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች የህሊና እስረኞች የታሰሩበትን አንደኛ አመት የሚያስብ ዝግጅት ባለፈው ቅዳሜ መስከረም 4 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ። በዚህ የዋሽንግተን ዲሲ አምነስቲ አለማቀፍ ቅርንጫፍ ደጋፊዎችና ፍሪ እስክንድር ነጋ ባዘጋጁት ዝግጅት ላይ፤ የእስክንድር ነጋን ቤተሰቦች ጨምሮ አያሌ ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው የሻማ ማብራት ስነ-ስርአት አካሂደዋል። የዝግጅቱ አስተባባሪ፤ ወ/ት አዜብ የዝግጅቱን ዓላማ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩ አያሌ የህሊና እስረኞችን ...

Read More »

በሶማሊ ክልል በሚሊሺያዎች እና በህዝቡ መካከል በተፈጠረ ግጭት 11 ሰዎችና ቁጥራቸው ያልታወቁ ፖሊሶች ተገደሉ

መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክልሉ መንግስት እየተደገፈ የተለያዩ የስብአዊ መብቶችን በመጣስ የሚታወቀው የሶማሊያ ሚሊሺያ ታጣቂ ሀይል ሰሞኑን ከሀሺ ወረዳ ህዝብ ጋር በፈጠረው ግጭት 11 ሰዎችን ሲገድል፣ ከሚሊሺያዎች ወገን ደግሞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ይሁን እንጅ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ታጣቂዎች ተገድለዋል። በኦጋዴን አካባቢ ብቻ ሳይሆን ወደ አፋር አካባቢዎች በመንቀሰቃስ በመንቀሳቀስ የተለያዩ ግጭ  ቶችን እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚፈጽመው ይህ ...

Read More »

ኢህአዴግ ቀጣዩን ምርጫ ካሸነፈ አዲስ ተሿሚዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በስልጣናቸው ይቀጥላሉ ሢሉ አቶ በረከት ስምዖን ተናገሩ

መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ይህን ያሉት፤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ቅዳሜ ዕለት ሊቀ-መንበሩን እና ምክትል ሊቀ-መንበሩን መምረጡን ተከትሎ ከኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሀላፊው ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር በሂልተን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ቀደም ሲል የህወሀቱን አቶ ስብሀት ነጋን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ የሚመረጠው ሰው ሹመቱ የሚቆየው እስከ ቀጣዩ ምርጫ እንደሆነ እና ...

Read More »

የኢትዮጵያ ተስፋ ወጣቶች ድርጅት የተለያዩ ወረቀቶችን በአዲስ አበባ መበተኑን አስታወቀ

መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ የተለያዩ ቀስቃሽ ጽሁፎችን እና መግለጫዎችን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች መበተኑ ታውቋል።   ድርጅቱ  ” የአንባገነኑ ስርአት በየቤተ እምነቱ ውስጥ ጣልቃ እየገባ የአማኞቹን ሰላም እየነሳ እንደሚገኝ፣  ዘረኛው ስርአት ሀገሪቷን በዘር ከፋፍሎ አንዱን ብሄር ከሌላኛው ጋር በማጋጨት የህዝቡን የመኖር ህልውና አስጊ ደረጃ ላይ ማድረሱን ፣ በአገዛዙ ቅጥረኞች የአማራውን ህዝብ ከደቡብ ክልል ማባረሩን፣የኦሮሞን፣የአፋርን፣ የጋንቤላን፣ የሱማሌን ...

Read More »

የቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ሊያፈርስ የሄደውን የፖሊስ ሀይል ተባብረው በመመከት ወደ መጣበት መለሱት

መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፖሊስና በነዋሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ፤”መብታችንን አናስነካም!”ባሉ ነዋሪዎች ድል አድራጊነት ተጠናቋል። የአስተዳደሩ ግብረ ኃይል  ባለፈው ሐሙስ በዶዘር በመታገዝ መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ ያደረገው ሙከራ፤ በአካባቢው ነዋሪዎች ብርቱ ተቃውሞ ተቋርጧል፡፡ እንደ ሪፖርተር ዘገበ፤ በወቅቱ በነዋሪዎቹና በፖሊስ መካከል የጥይት ተኩስና የድንጋይ ውርወራ ተካሂዶ ነበር፡፡ ባንዲራ በማውለብለብ ባካሄዱት ተቃውሞ መኖሪያ ቤታቸውን ከመፍረስ የታገዱት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ መንግሥት እንዲያነጋግራቸው ...

Read More »

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ከግድያ አመለጡ

መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሦስት አጥፍቶ ጠፊዎች ባለፈው ረቡዕ በሞቃዲሾ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በፈፀሙት የቦንብ ጥቃት አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሁሴን ሼክ መሀመድ ለጥቂት ተረፉ። ጥቃቱ የተፈፀመው አዲሱ ፕሬዚዳንት ከኬንያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዑካን ጋር ስብሰባ እያደረጉ በነበረበት ሰዓት ነው። በጥቃቱ ሦስቱን አጥፍቶ ጠፊዎች እና አንድ የ አፍሪካ ህብረት ሰላም አስጠባቂ ወታደርን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ዓለማቀፍ መገናኛ ...

Read More »