መጋቢት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞ ማስታወቂያ ሚኒስቴርን መፍረስ ተከትሎ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት እንዲፈርስ የተደረገው የቀድሞ መንግስታዊ ዜና አገልግሎት በአሁኑ ወቅት በአቶ በረከት ስምኦን በሚመራው የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት በአንድ መምሪያ ስር በሕግ ባልተሰጠው ስም “የኢትዮጽያ ዜና አገልግሎት-ኢዜአ” በሚል ዜናዎችን በመስራት ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በመሸጥ ላይ መገኘቱ ብዙዎችን ግራ የሚያጋባ ሆኗል፡፡ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት እያካሄደ ባለው የሪፎርም ስራ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአፋር ህጻነት በርሀብ እየረገፉ ነው
መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክልሉ ካለፉት አራት ወራት ጀምሮ የተከሰተው ከፍተኛ ረሀብና የውሀ እጥረት የበርካታ ህጻናትን ህይወት መቅጠፉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ምንም እንኳ 60 በመቶ በሚሆነው የአፋር አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሀ እጥረት ቢከሰተም ፣ ችግሩ ከሁሉም ወረዳዎች አስከፊ ሆኖ በቀጠለበት የእዳ ወረዳ 6 ህጻናት በአንድ ወር ውስጥ ሞተዋል። ይህ አሀዝ በአንድ ሰፈር ብቻ የተጠናከረ እንጅ ...
Read More »የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በአብዛኛው ነባር አመራሮቻቸው በስራ አስፈጻሚነት ቀጠሉ
መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ሰሞኑን በተከታታይ ባካሄዱዋቸውና በመተካካት ረገድ እምብዛም ለውጥ ያልታየባቸው ጉባዔዎች በአብዛኛው ነባር አመራሩን ይዘው ሲያስቀጥሉ መጠነኛ የሆነ እርምጃም ወስደዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ኦህዴድ አቶ አባዱላ ገመዳን፣ ግርማ ብሩን እና ኩማ ደመቅሳን ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ሲያሰናብት፤ ብአዴን በበኩሉ የፍትህ ሚኒስትር የሆኑትን አቶ ብርሃን ኃይሉን፣ደኢህዴን ደግሞ አቶ ተሾመ ቶጋን አሰናብቷል፡፡ ብአዴን በጤና ...
Read More »ኢትዮጵያውያን በጄኔቭ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ትናንት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ገዢው ፓርቲ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ዙሪያ የየዘውን አቋም ከማውገዝ ባለፈ፣ በአገረቱ ውስጥ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተባባሰ መምጣቱን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች የተለያዩ ክፍሎች አስታውቀዋል። የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ ፣ የቢላል ኮሚቴ መስራችና ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ኤልያስ ረሺድ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አንደገለጡት ሰላማዊ ሰልፉ ሙስሊም ኢትዮጵያን የሚያደርጉትን ትግል ...
Read More »በአባይ ግድብ ከሳሊኒ በመቀጠል ከፍተኛው ተጠቃሚ የወ/ሮ አዜብ መስፍን ቤተሰብ ድርጅት ነው ተባለ
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሁለት ዓመት በፊት ኢሳት በወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ በወ/ሮ አቲኮ ስዩም አምባየ የተመሰረተው ኦርቺድ ቢዝነስ ግሩፕ በጣሊያኑ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን አማካኝነት በሚገነቡት ግልገል ጊቤ አንድ እና ግልገል ጊቢ ሁለት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክቶች ስሚንቶ እና የግንባታ እቃዎችን እንዲሁም ከፍተኛ ማሺነሪዎችን በማቅረብ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማጋበሱን ዘግቦ ነበር። በአባይ ወንዝ ላይ የሚሰራውን የህዳሴውን ግድብ ...
Read More »የኢህአዴግ የመተካካት ዕቅድ በተግባር እየከሸፈ ነው ተባለ
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ ያወጣው የአመራር መተካካት ከመፈክር ባለፈ እየተተገበረ አለመሆኑን ለግንባሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች ከ17 ዓመታት በላይ በጫካ ትግል ላይ ዕድሜያቸውን ያሳለፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአሁኑ ወቅት በተለይ ከዕድሜና ሕመም ጋር ተያይዞ ብዙዎቹ የያዙትን ከፍተኛ ኃላፊነት መወጣት የማይችሉበት ደረጃ ላይ እየደረሱ በመሆናቸው በሌላ አመራር የመተካታቸው ጉዳይ ታምኖበት የአፈጻጸም ፕሮግራም ወጥቶለት ...
Read More »የአፍሪካ መዲና-አዲስ አበባ የውሀ እና የመብራት ያለህ እያለች ነው
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውኃና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ ይሻሻላል በሚል በትዕግስት ቢጠባበቁም፣ እየባሰበት እንደመጣና መፍትሔ በማጣታቸው ግራ መጋባታቸውን በርካታ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መግለፃቸውን ሪፖርተር ዘገበ። እንደ ጋዜጣው ዘገባ ውኃና ኤሌክትሪክ ከዓመት እስከ ዓመት ተቋርጦባቸው እንደማያውቅ ሲነገርላቸው የነበሩ በተለይ በቤተ መንግሥት አቅራቢያ ያሉ ነዋሪዎች ሳይቀሩ አሁን ውኃ እያገኑ ያሉት በሳምንት ለሦስትና አራት ቀናት ብቻ ...
Read More »ፕሬዚዳንት ኦባማ እስራኤልን እየጎበኙ ነው
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እስራኤል ሲገቡ ፣ አገራቸው ለእስራኤል ጠንካራ ወዳጅ አገር መሆኑዋን ገልጸዋል። እስራኤል እንደ አሜሪካ ጠንካራ ወዳጅ የላትም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ለቅድስቲቱ አገር ሰላም መምጣት እንዳለበትም ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ሀሙስ ወደ ዌስት ባንኩዋ ራማላህ ከተማ ተጉዘው ከፍልስጤም ባለስልጣናት ጋር ይነጋገራሉ። የፕሬዚዳንት ኦባማ ዋና የጉብኝት አላማ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ማደስ ...
Read More »በባህርዳር ጊዮን ሆቴል ጉዳይ የተነሳ የአማራ ክልል ባለስልጣናትና ህወሀት ተፋጠዋል
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዛሬ 21 አመት ህወሀት/ ኢህአዴግ አሸንፎ አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ በፊት ለህወሀት በመሰለል ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው የሚታወቁት በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአድዋው ተወላጅ እና የአቶ መለስ ዜናዊ የቅርብ ዘመድ አቶ ወልዱ፣ ለህወሀት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ፣ አቶ መለስ ዜናዊ የመንግስት ንብረት የሆነውን ጊዮን ሄቴልን በ5 ሺ ብር ኪራይ እንዲሰሩበት በገጸ በረከት ስጥተዋቸው ነበር። አቶ ወልዱ ...
Read More »የህዝቡ የፖለቲካ ተሳትፎ ካልጎለበተ በኢትዮጵያ ጠንካራ ለውጥ አይመጣም ሲሉ የለጋሽ አገራት ቡድን አስታወቀ
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የለጋሽ አገራት ቡድን ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው የኢትዮጵያ መንግስት አገሪቱን ወደ መካከለኛ ገቢ አገር ለመቀየር ማቀዱ በአወንታዊነት የሚመዘገብ ቢሆንም፣ ይህን አላማ እውን ለማድረግ መንግስት የህዝቡን ተሳትፎ ለመጨመር፣ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ለማድረግ፣ የዲሞክራሲ ተቋማት እንዲገነቡና እንዲጠናከሩ ለማድረግ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ አለበት ብሎአል። ሪፖርቱ አክሎም መንግስት የመቻቻል ባህል እንዲጎለብትን ልዩነቶችን ለማስተናገድ ካልቻለ ...
Read More »