.የኢሳት አማርኛ ዜና

ገዢው ፓርቲ ያልጠበቀውን የምርጫ ውጤት አገኘ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ያለምንም ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ባደረገው ምርጫ ያልጠበቀውን ውጤት ማግኘቱን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሰባሰብናቸው መረጃዎች አመለከቱ። ምንም እንኳ ኢህአዴግ ምርጫውን ከ99 እስከ 100 ፐርሰንት እንደሚያሸንፍ ቢጠበቅም ህዝቡ በምርጫ ካርዶች ላይ ያሰፈረው መልእክት ግን ገዢው ፓርቲ ያልጠበቀውና ያለሰበው ነበር እንደ ታዛቢዎች አገላለጽ። በአንዳንድ አካባቢዎች የቀበሌ እና የወረዳ ሹሞች የምርጫ ታዛቢዎች እና ...

Read More »

መንግስታዊ ተቋማት በሕዝብ ላይ የሚያደርሱት አስተዳደራዊ በደሎች ከዓመት ዓመት እያደገ ነው

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ከሕዝብ ከሚቀርቡለት አስተዳደራዊ በደሎች መካከል በመንግስት ላይ በተለይ በፍትህ ተቋማት ላይ የሚቀርበው የአስተዳደራዊ ቅሬታ ብዛት ከፍተኛ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታት ወደተቋሙ የመጡ ቅሬታዎች መካከል አንድ ሶስተኛ ወይም 31 በመቶ ያህል ከፍተኛ ድርሻ የያዙት የመንግስት ተቋማት ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ማለትም ከቀበሌ መዋቅር አንስቶ አስከ ፌዴራል ባሉ ...

Read More »

የእርዳታ ድርጅቶች በዝቅተኛው የኦሞ ሸለቆ የደረሰውን የህዝብ መፈናቀል ከቁም ነገር አለመቁጠራቸውን አንድ ድርጅት አስታወቀ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ለኢሳት በላከው ዘገባ በኦሞ ሸለቆ ላይ የሚገነባው ግልገል ጊቤ 3 እና ለስኳር እርሻ በሚል የሚካሄደው የመሬት ወረራ በአካባቢው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ቢያስከትልም፣ መንግስትን በገንዘብ የሚደጉሙት ለጋሽ አገራት ለችግሩ ተገቢውን ትኩረት አልሰጡትም። በቦዲ. ክዌጎ እና ሙርሲ ህዝቦች ኩራዝ እየተባለ ለሚጠራው የስኳር ፕሮጀክት መሬቱ ይፈለጋል በሚል ከቦታቸው እንዲፈናቀሉ ተደርጓል። ነዋሪዎቹ አብዛኛውን ከብቶቻቸውን ...

Read More »

ከሰሀራ በታች ያሉ አገሮች በመጪዎቹ 3 አመታት ፈጣን እድገት ያስመዘግባሉ

ሚያዚያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ቢቢሲ የአለም ባንክን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሰሀራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮች በመጪዎቹ ሶስት አመታት ከሌላው አለም አማካኝ የእድገት መጠን ጋር ሲተያይ የተሻለ እድገት ያሳያሉ። የአብዛኞቹ አገራት እድገት ጥሬ እቃዎችን ወደ ውጭ አገራት በመላክ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው፣ የስራ አጥ ቁጥር መጨመር እና ከጥሬ እቃዎች ባሻገር ገቢን ለመጨመር የሚያስቸሉ ሌሎች የስራ መስኮች ባለመፈጠራቸው ...

Read More »

የከማሺ ዞን ተፈናቃይ አርሶ አደሮች ወደ ቤታችው ሲገቡ የተደበላለቀ ስሜት እንደተሰማቸው ገለጹ

ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ያለፉትን ሳምንታት በከፍተኛ ጭንቅ ውስጥ ሆነው ያሳለፉት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን የተፈናቀሉ አርሶአደሮች ወደ ቤታቸው ሲገቡ የተደበላለቀ ስሜት እንደፈጠረባቸው ለኢሳት ገልጸዋል። “ንብረት ቢወድም ይተካል፣ በህይወት ተርፈን ወደ ቤታችን በመግባታችን እግዝአብሄርን እና የተባበሩንን ሁሉ እናመሰግናለን፣ ደስ ብሎናል” በማለት አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ ይፈለጉ ተፈናቃይ ተናግረዋል። ሌላ ተፈናቃይም እንዲሁ ወደ ቤቱ ሲመለስ ደስታ እንደፈጠረበት ገልጾ፣ ሁኔታው ...

Read More »

የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና የሲቪክ ተቋማት መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል እያወገዙ ነው

ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል ” የአማራ ህዝብ ስቃይ እንዲያበቃ ወያኔን መቅበር ይኖርብናል ” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” ወያኔ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ያፈናቀላቸው አማሮች የመጀመሪያዎቹ የወያኔዎች የጥቃት ሰለባዎች አይደሉም። የመጨረሻዎቹም አይሆኑም። ወያኔ  ከነ ጸረ አማራ ፖሊሲው በስልጣን እስካለ ድረስና በአማራ ስም አማራውን እያፈኑ፣ እየሰለሉ ከወያኔ ፍርፋሪ እየለቀሙ ለመኖር የቆረጡ  ከአማራው መሃል የወጡ ከሃዲዎች አማራውን መቆጠጠር ...

Read More »

የአፋር ከፍተኛ ባለስልጣናት ሽኩቻ ቀጥሎአል

ሚያዚያ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከክልሉ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የአብዴፓ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ከፕሬዚዳንቱ ከአቶ አሊ ሴሮ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ውዝግብ ከስልጣን እንዲወርዱ  ከተደረጉ በሁዋላ ከእርሳቸው ጀርባ በመሆን ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ ይሰራሉ የተባሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊው  አቶ አወል ወግሪስ ከስልጣን ተባረዋል። በግምገማው ወቅት አቶ አባይ ጸሀየ በስፍራው ተገኝተው  ከአቶ አሊሴሮ ጋር በመቆም ፕሬዚዳንቱን ይቃወማሉ የተባሉትን ...

Read More »

ከከማሺ ዞን የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ወደ ቀበሌያቸው ተመለሱ

ሚያዚያ ፬  (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ከከማሺ ዞን ተፈናቅለው በፍኖሰላም ከተማ ሰፍረው የቆዩት የአማራ ተወላጆች ያሶ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ አንድ ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ ከተደረጉ በሁዋላ ዛሬ አርብ ከሰአት በሁዋላ ወደ የቀበሌያቸው እንዲመለሱ መደረጉን ኢሳት ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች ገልጸዋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አብዛኛው ተፈናቃይ ወደ የቀበሌው የተጓዘ ሲሆን ቀሪዎቹም ወደ ቦታቸው ለመመለስ መኪና በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፍትህ ይሰጠን በማለት ተቃውሞ ሲያሰሙ ዋሉ

ሚያዚያ ፬  (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአርብ ስግደትን በማስከተል ከአንድ አመት በላይ ሲካሄድ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የመብታችን ይከበር ጥያቄ፣ በዚህ ሳምንት ” ፍትህ ፍትህ” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በአዲስ አበባ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች “ፍትህ ” የሚል ጽሁፍ የያዙ ወረቀቶችን በመያዝ ፍትህን ሲጠይቁ የዋሉ ሲሆን፣ ፍትህ አጥተው በእስር ቤት የሚሰቃዩ  መሪዎቻቸውን እጃቸውን በማጣመር በድጋሜ አስበዋቸዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ...

Read More »

ኢህአዴግ “ሕዝቡ ለመምረጥ ላይወጣ ይችላል” በሚል ስጋት ውስጥ ገብቷል

ሚያዚያ ፬  (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢህአዴግ በመጪው እሁድ ብቻውን በሚወዳደርበት የአዲስአበባ እና የአካባቢ ምርጫ ላይ ለመምረጥ የተመዘገበው ሕዝብ ወጥቶ ላይመርጥ ይችላል በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቁን ምንጮቻንን ጠቆሙ፡፡ ከምርጫ በፊት ባሉት ችግሮች ላይ ውይይት እንዲቀድም በይፋ ያቀረቡት ጥያቄ በኢህአዴግና በኢህአዴግ መራሹ ምርጫ ቦርድ በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱን ተከትሎ ከ28 በላይ ፓርቲዎች ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን፣ የኢህአዴግ አጋር እንደሆነ የሚነገርለት ...

Read More »