ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰደድ እሳቱ ከተነሳ 3ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን የደባርቅ አካባቢ ሕዝብ ያደረገው ጥረት እሳቱን ሊያጠፋው አልቻለም። ዛሬ ኢሳት ያናገራቸው የደባርቅ አካባቢ ነዋሪ እንደገለጡልን ብርቅና ድንቅ አዕዋፍ፣ እንስሳትና ዕፅዋትን ያቀፈው የስሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ ከክልልና ከፌዴራል እሳት አደጋ መከላከያ እገዛ ካልተደረገ ከፍተኛ አደጋ ላይ ይገኛል። በሳንቃ በር አካባቢ በሚገኘው የፓርኩ ክፍል የተነሳው እሳት በኢትዮጵያ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በጋምቤላ ክልል የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላትን ጨምሮ በ23 ሰዎች ግድያ የተከሰሱ ሞት ተፈረደባቸው
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ በ23 ሰዎች ግድያ የከሰሳቸው ዘጠኝ ሰዎች ሲሆኑ ሶስቱ በተገኙበት ስድስቱ ላይ ደግሞ ባልተገኙበት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል:: በሌሎቹ ላይ ደግሞ ከ21 እስከ 9 ዓመት የሚደርስ እስር ወስኖባቸዋል። የዐቃቤ ሕግ የክስ ማመልከቻ እንደሚያብራራው ኡመድ ኡከት የተባለው ፍርደኛ ከግብረ አበሮቹ ጋር በአኙዋክ ዞን አበቦ ወረዳ ድቦንግ ቀበሌ ...
Read More »የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አባል ድርጅቶች በአስቸኳይ እንዲዋሃዱ ተጠየቀ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት አምስት ወራቶች የመድረክን የሥራ አፈፃፀም ሁኔታ በቅርብ ሲገመግም የነበረው የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክ እንዲዋሃድ ብሏል ሲል ፍኖተ ነፃነት ዘግቧል። ድርጅቱ ላለፉት አራት ዓመታት አሳሳቢ በሆኑና በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ የቆየ ቢሆንም ሀገራችን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር በተደረገው ትግል ውስጥ ...
Read More »የቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለባቡር መስመር ሥራ በሚል (የፊታችን) ሐሙስ ከቦታው ሊነሳ መሆኑ ተገለፀ።
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሕወሓት ንብረት የሆነው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደዘገበው በ1930ዎቹ ለቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያነት የተሰራውና(አራዳ) ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ የሚገኘው ሐውልት በዚህ ሳምንት ተነስቶ ወደ ጊዜያዊ መቆያ ቦታ ይዛወራል። በአዲስ አበባ በስሜን-ደቡብ አቅጣጫ ለሚሰራው የ650 ሜትር የመሬት ውስጥ የባቡር መተላለፊያ ግንባታ ምክንያት ሐውልቱ በጊዜያዊነት መነሳት አስፈልጎናል ያለው ዋልታ ሐውልቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ቅጥር ግቢ ...
Read More »በተለያዩ የአለም ክፍሎች መንግስት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው
ሚያዚያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለባይ ግድብ መዋጪ ለማሰባሰብ በኖርዌይ ኦስሎ የተጠራው ስብሰባ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቷ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲቋረጥ ተደርጓል። በተመሳሳይ ሁኔታም በካልፎሪኒያ ሳንዲያጎ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ተብሎ የተጠራው ስብሰባ በአካባቢው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ሰብሰባው እንዲቋረጥ ተደርጓል። በሌላ በኩል ደግሞ በኔዘርላንድስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን የማፈናቀል ዘመቻ አውግዘዋል። ። የኢትዮጵያውያን ማህበር በሆላንድ ትናንት በአምስተርዳም ...
Read More »የታዋቂው ፖለቲከኛ እና ጸሀፊ አስገደ ገብረስላሴ ልጅ ታፍኖ መወሰዱ ታወቀ
ሚያዚያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያን ሀርነት ትግራይ ነባር አባል፣ በአሁኑ ጊዜ የአረና ትግራይ ከፍተኛ የአመራር አባል እና ጸሀፊ የአቶ አስገደ ገብረስላሴ ልጅ የሆነው አክህፎም አስገደ የታሰረው ባለፈው አርብ ነው። ሚያዚያ 16 ቀን 2005 ዓም ቀዳማዊ ወያኔ ፖሊስ ጣቢያ ተብሎ በሚጠራ እስር ቤት መታሰሩን እሁድ ሚያዚያ 20 ደግሞ በመቀሌ ውስጥ በሚገኝ ህጋዊ እውቅና በሌለው ድብቅ እስር ...
Read More »በመተማ ወረዳ አርሶ አደሮች ከመፈናቀላቸውም፡በላይ ድረንበር ጥሰዋል ተብለው ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ
ሚያዚያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጐንደር ዞን በመተማ ወረዳ ከዮሐንስ ከተማ በስተሰሜን <<ደለሎ>> ተብሎ በሚጠራው አካባቢ፣ ለረዥም ዓመታት መሬት ወስደው በሕጋዊ መንገድ ግብር ሲከፍሉ፡የቆዩ አርሶ አደሮች፣ አካባቢውን ጥለው እንዲሄዱ በወረዳው ውሳኔ መተላለፉን የሪፖርተር ዘገበ፡፡ ጋዜጣው ምንጮቹን በመጥቀስ እንደዘገበው፤ድንበር አልፈዋል በሚል ሦስት አርሶ አደሮችም በሱዳን ታጣቂዎች ተገድለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን በፓርላማ ሪፖርት ሲያቀርቡ በቤንሻንጉል ክልል ...
Read More »የህወሀት ጄኔራሎች በአለም ላይ ውድ የሆነውን የታንታለም ማእድንን በህገወጥ መንገድ እየዘረፉ ለውጭ ገበያ እያቀረቡ ነው
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኬንቲቻ ቦረና የኢትዮጵያ ማእድን ልማት አክሲዮን ማህበር የተባለ መንግስታዊ ድርጅት ከአመታት በፊት በጉጂ ዞን በሻኪሶና አናሶራ ወረዳዎች 2ሺ 500 ቶን የሚጠጋ ንጹህ የታንታለም ማእድን ማግኘቱ የመገናኛ ብዙህንን ትኩረት ስቦ ነበር። ኩባንያው ምንም አይነት የማጣሪያ ስራ ሳይሰራ ይህን ውድና ስትራቴጂክ ማእድን በርካሽ ዋጋ መሸጡ አገሪቱን እንደሚጎዳ የዘርፉ ባለሙያዎች ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ...
Read More »በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስ መንግስት የሚፈጽመውን የማፈናቀል እርምጃ አወገዘ
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በውጭ የሚገኘው እና በ ብጹእ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የኢሕአዴግ መንግሥት አገራችንን ኢትዮጵያን በጠመንጃ ኃይል ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንሥቶ የኢትዮጵያ አንድነት ከባድ አደጋ ውስጥ ጥሎታል” ብሎአል። ኢህአዴግ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን መልኩን በመቀያየር በቦረናና በአርባ ጉጉ፥ በጋምቤላና በኦጋዴን፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በአፋር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በቤኒሻንጉል በሚኖሩት ወገኖቻችን ...
Read More »በዚህ አመት 30 ሺ ኢትዮጵያን የመን መግባታቸው ታወቀ
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር እንዳስታወቀው በያዝነው አመት ብቻ 30 ሺ ስደተኞች ባህር አቋርጠው የመን የገቡ ሲሆን፣ ባለፉት 7 አመታት ወደ የመን ከገቡት ግማሸ ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ወደ የመን የገቡ ሶማሊዎች ወዲያውኑ የስደተኝነት መታወቂያ የሚያገኙ ሲሆን፣ ኢትዮጵያኖች ግን ይህን ወረቀት በቀላሉ አያገኙም። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ወደ ሌሎች የአረብ ...
Read More »