ግንቦት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢትዮጵያ ሆቴልና ከጎኑ የሚገኘው የበጎ አድራጎት ሕንፃ ፈርሰው፣ በቦታው ላይ 60 ፎቅ ያለው ሆቴል እንዲገነባ የተወሰነው ውሳኔ ተቃውሞ ገጥሞታል ሲል የዘገበው ሪፖርተር ነው። ተቃውሞውን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያቀረቡት ከ 81 ዓመት በፊት በተገነባውና አሁን ከ ኢትኦጵያ ሆቴል ጋር እንዲፈርስ በተወሰነበት በፖላስሪያቴሪ በጎ አድራጎት ሕንፃ ላይ የሚኖሩ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ ነጋዴዎቹ ተቃውሟቸውን ለከንቲባ ኩማ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የመንግስት ባለስልጣናት በፈጠሩት ችግር በአፋርና በአማራ ድንበሮች ከፍተኛ ግጭት ተፈጥሮ ሰዎች ተገደሉ
ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሰሜን ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ በአፋር እና በአማራ ተወላጆች መካከል በመንግስት ባለስልጣናት በተቀሰቀሰ ችግር ባለፉት 2 ወራት ብቻ ከ15 ያላነሱ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል፣ ከብቶችም ተዘርፈዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ባለፈው ሀሙስ እና አርብ በተፈጠረው ግጭት አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ቆስሏል። ግጭቱን የፈጠሩት የታጠቁ የአፋር ...
Read More »በጎንደር የተቃውሞ ሰልፍ አደራጅተዋል የተባሉ 14 ወጣቶች ታሰሩ
ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ባለፈው ሳምንት የጎንደር ቀበሌ 6 እና 7 ወጣቶች ያደረጉትን ተቃውሞ ተከትሎ ከ14 በላይ ወጣቶች በዜኖ 1 እና ዜሮ 2 ጣቢያዎች መታሰራቸውን የአካባቢው ወኪሎች ገልጸዋል። ሰልፉን አስተባብረዋል የተባሉት ወጣቶች በየቤታቸው እየታደኑ መያዛቸውን የገለጹት ወኪሎች፣ ፍርድ ቤት ይቀርቡ አይቅረቡ ለማወቅ አለመቻሉን ተናግረዋል። ከቀናት በፊት በጎንደር የቀበሌ6 እና 7 ነዋሪዎች የመብራት፣ ውሀ እና ሌሎችንም ...
Read More »የባለራይ ወጣቶች ህዝብ ግንኙነት ከሌሎች 5 ሰዎች ጋር በግንቦት7 አባልነት ተከሰሰ
ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የባለራእይ ወጣቶች ማህበር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ በደህንነቶች ከተወሰደ በሁዋላ በማእከላዊ እስር ቤት መታሰሩን ወንድሙ ሙሉጌታ ተክለያሬድ ለኢሳት ገልጿል። ሀሙስ እለት ፍርድ ቤት የቀረበው ወጣት ብርሀኑ ከእርሱ ጋር ሌሎች በተመሳሳይ መንገድ የታሰሩ 5 ወጣቶች ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል። አምስቱ ወጣቶች እርስ በርስ የማይተዋወቁ እና ...
Read More »የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ኮሚቴ መንግስት ለሱዳን አሳልፎ የሰጠው እጅግ ሰፊ መሬት ህገወጥ ነው አለ
ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የድንበሩ ኮሚቴ ከፍተኛ አካል የሆነው ምክር ቤት ግንቦት 10 እና 11 ቀን 2005 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጠበብቶች የተሳተፉበት ታላቅ ጉባዔ በሲሊቨር ስፕሪንግ ከተማ፣ ሜሪላንድ፣ አሜሪካ አካሂዶ ባወጣው መግለጫ የሻለቃ ቻርልስ ጉዊን ድንበር ከለላ መሥመር ሕገወጥ መሆኑን በተጨባጭ ውድቅ አድርጓል። መንግስት ለሱዳን በስጦታ ያስረከበው ዳር- ድንበራችን የኢትዮጵያ መሬት መሆኑን የገለጸው ኮሚቴው ፣ ...
Read More »ጆን ኬሪ ለአፍሪካ ህብረት 50ኛ አመት በአል ለመገኘት አዲስ አበባ ገቡ
ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒሰትር ሀይለማርያም ጋር ተወያይተዋል። ኬሪ በኢትዮጵያ በሚታየው ሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዙሪአ ከአቶ ሀይለማርያም ጋር ስለመነጋገራቸው የተገለጸ ነገር ይለም። ባለስልጣኑ የኢህአዴግ መንግስት የህዝብን መብቶች እንዲያከብር ግፊት እንዲያደርጉ የተለያዩ አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ሲወተውቱ ከርመዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ 50ኛው አመት የአፍሪካ ህብረት በአል በሚከበርበት ...
Read More »በደሴ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በፌደራል ፖሊሶች ተደበደቡ
ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘወትር አርብ የጁመዓን ስግደት ተከትሎ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ” ድምጻችን ይሰማ” በማለት የሚያቀርቡት ተቃውሞ ከአዲስ አበባ ውጭ የተካሄደ ሲሆን በደሴ ሸዋ በር መስጂድ የተካሄደው ተቃውሞ በጸጥታ ሀይሎች እንዲበተን ተደርጓል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተደብድበዋል። አንዳንድ ወጣቶች በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶችም ታፍሰው በመኪና ...
Read More »ኢህአዴግ ግንቦት 20ን የአባይን ወንዝ አቅጣጫ በማስቀየር ሊያከብር ነው
ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢህአዴግ አዲስአበባን የተቆጣጠረበትን 22ኛ ዓመት ክብረበአል የአባይን ግድብ አቅጣጫ በማስቀየር ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ስነስርዓቱ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በጉባ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሚገኙበት እንደሚካሄድ ታውቋል። ኢህአዴግ የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር የኢትዮጵያን ህዝብ በእለቱ ለማስደመም ማቀዱን ለማወቅ ተችሎአል። የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየር ሥራ ክንውን አስመልክቶም የፊታችን ሰኞ ግንቦት 19/2005 ...
Read More »የኡራዔል አካባቢ ነጋዴዎች ሱቆቻቸው ከታሸጉ አራት ወራት መቁጠሩን ተናገሩ
ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በተለምዶ ኡራኤል ተብሎ በሚጠራው ቂርቆስ ክፍለከተማ በአሁኑ አጠራር ወረዳ 8 የንግድ ክልል ውስጥ የሚገኙ ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታቸውን ሕይወት ብርሃን ለተባለ ቤተክርስቲያን በአስቸኳይ ለቀው እንዲያስረክቡ መገደዳቸውን ባለመቀበላቸው ሱቆቻቸው በክፍለከተማው ከታሸጉ አራት ወራት እንደሞላው በምሬት ገለጹ፡፡ በአካባቢው የኮንስትራክሽን የፋብሪካ ውጤቶች በችርቻሮና በጅምላ የሚቀርብበትና ከፍተኛ ግብር ከፋይ የንግዱ ኀብረተሰብ አባላትን ያቀፈ አካባቢ ነው። ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ በማንኛውም መልኩ ሰልፉን ለማካሄድ መወሰኑን አስታወቀ
ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጀነር ይልቃል ጌትነት ትናንት ለኢሳት ሬዲዮ እንደገለጹት የፓርቲው አመራሮች የፈቃድ ደብዳቤ ለማስገባት ወደ አዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት የሰላማዊ ሰልፍና የህዝባዊ ስብሰባ ማስታወቂያ ቢሮ ቢሄዱም ሃላፊዎቹ ደብዳቤውን ለመቀበል ፈቀደኛ አልሆኑም። ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቢሮ ሀላፊ ደብዳቤ አልቀበልም በማለታቸው የፓርቲው አመራሮች ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ከከንቲባው ጽህፈት ቤት ሀላፊ እሰከ ...
Read More »