በጎንደር የተቃውሞ ሰልፍ አደራጅተዋል የተባሉ 14 ወጣቶች ታሰሩ

ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ባለፈው ሳምንት የጎንደር ቀበሌ 6 እና 7 ወጣቶች  ያደረጉትን ተቃውሞ ተከትሎ ከ14 በላይ ወጣቶች በዜኖ 1 እና ዜሮ 2 ጣቢያዎች መታሰራቸውን የአካባቢው ወኪሎች ገልጸዋል።

ሰልፉን አስተባብረዋል የተባሉት ወጣቶች በየቤታቸው እየታደኑ መያዛቸውን የገለጹት ወኪሎች፣ ፍርድ ቤት ይቀርቡ አይቅረቡ ለማወቅ አለመቻሉን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት በጎንደር የቀበሌ6 እና 7 ነዋሪዎች የመብራት፣ ውሀ እና ሌሎችንም ማህበራዊ አገልግሎቶች ለመጠየቅ በራሳቸው ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።