.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአንድ አመት ውስጥ 19 የዳንግላ ከተማ ፖሊሶች መሳሪያቸውን እንደያዙ የገቡበት አልታወቀም

ግንቦት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአማራ ክልል ፖሊስ  በ9 ወሩ የግምገማ ሪፖርት ላይ እንደገለጸው 19 የዳንጋላ ፖሊሶች እስከነ መሳሪያቸው ተሰውረዋል። ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደገለጹት ፖሊሶቹ ራሱን ይፋ ያላደረገውን እና በ አዊ ዞን በጃዊ በረሀ በስፋት የሚንቀሳቀሰውን አዲስ ወታደራዊ ሀይል ተቀላቅለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወታደሮቹ እንቅስቃሴያቸውን በማስፋት አንዳንድ መጠነኛ የሚባሉ ጥቃቶችን እየፈጸሙ ነው። የፖሊስ የጸጥታ ሃይሎችን መጥፋት ተከትሎ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት ድህረ ገጾችን ለማፈን 26 ቢሊዮን ብር ክፍያ ለቻይና መንግስት ፈጸመ

ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከአስተማማኝ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ የደህንነት ሰራተኛ ባገኘው መረጃ መንግስት ለስርአቱ አደጋ ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን የመገናኝ ብዙሀን ወደ አገር ቤት ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር ወይም ወደ 26 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መክፈሉን ለማወቅ ተችሎአል። በቁጥር አንድ እንዲታፈን ትእዛዝ የተላለፈበት ኢሳት ሲሆን ድህረገጹ ራዲዮው እና ቴሌቪዥኑን ሙሉ በሙሉ  እንዲታፈን ስምምነት ላይ ተደርሷል። ...

Read More »

የብአዴን ወጣቶች ሊግ አባላት ከኢህአዴግ ጎን ተሰልፈን ለመታገል እምነትም ጽናትም የለንም አሉ

ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ይህን የተናገሩት በባህርዳር በመካሄድ ላይ ባለው የብአዴን ወጣቶች 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ በክልሉ ካለው 20 ሚልዮን ህዝብ መካከል 429 ሺ 520 የሚሆኑ ወጣቶችን አባል አለኝ የሚለው ብአዴን ከአደገኛ ቦዘኔነት እስከ ልማት አርበኛ ስም የሚነግድበት ወጣት ከገዥው ፓርቲ ያተረፈው ኪሳራ መሆኑን ተሰብሳቢዎች በአስተያየት አመልከተዋል፡፡ ከመላው የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ ከ3000 በላይ ወጣቶች ...

Read More »

መንግስት በጉምሩክ ባለስልጣናት ላይ የወሰደውን እርምጃ ወደ ሌሎች ባለስልጣናት ማዞር ፈርቷል ተባለ

ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በቅርቡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሥራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች ላይ የወሰደውን እርምጃ ወደሌሎች በሙስና የሚጠረጠሩ ባለስልጣናት ለማስፋት ፍርሃት እየታየበት መሆኑን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ከኢትዮምህዳር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልለስ ገልጸዋል፡፡ ዶክተሩ ግንቦት 20 ለወጣው ኢትዮምህዳር ጋዜጣ እንደተናገሩት “በሙስና ተከስሰው ወደወህኒ የወረዱት የአንድ መ/ቤት ሠራተኞችና ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሐብታሞች ...

Read More »

መኢአድ እሁድ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፍና እንደሚያስተባብር አስታወቀ

ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ በሚቀጥለው እሁድ በጠራው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ እንደሚሳተፍ አስታወቀ።  የፓርቲው ተቀዳሚ ም/ል ሊቀመንበር አቶ ወንድማገኝ ደነቀ  ከኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጋር  ባደረጉት ቃለምልልስ ሰልፉ መደረጉን መደገፍና ማበረታታት ብቻ ሳይሆን ተከታታይነት እንዲኖረው ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።=    የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ህዝቡ ለሰላማዊ ሰልፉ በነቂስ እንዲወጣ መልእክት ...

Read More »

የአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ታመው በጀርመን ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው

ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ባለስልጣናት ከፍተኛ ቀረቤታ በማሳየት በአፋር ተወላጆች ዘንድ ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባቸው አቶ ኢስማኤል አሊሰሮ በጀርመን ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው።  በህወሀት የደህንነት ሰዎች ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግላቸው አቶ እስማኤል ጤናቸው እየተሻሻለ መምጣቱን ለኢሳት ተናግረዋል። ” ተሽሎኛል፣ ጥሩ ህክምናም እያገኘሁ ነው፣ አላህ ከፈቀደ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ልመለስ እችላለሁ በማለት” ፕሬዚዳንቱ አክለዋል።  ፕሬዚዳንቱን ...

Read More »

ኢህአዴግ በአማራ ክልል ሹሞች ላይ ጥብቅ ግምገማ እያካሄደ ነው

ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከብአዴን ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የመገናኛ ብዙሀን ሽፋን እንዳይሰጡት በተደረገበት ሁኔታ ከግንቦት19 ጀምሮ ግምገማ እየተካሄደ ነው። የግምገማው ዋና አላማ ኢህአዲግ በትጥቅ ትግል እንዲወድቅ አልመው ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ የሚጠረጠሩ ባለስልጣናትን ሰበብ በመፍጠር ለማውረድና ለመምታት ያቀደ ነው ተብሎአል። በአብዛኞቹ ግምገማዎች ላይ ከፍተኛ ውጥረት መኖሩንም የደረሰን ...

Read More »

የኢትዮጵያ ማአድን ልማት አክሲዮን ማህበር የተቋረጠውን የታንታለም ምርት ለመጀመር ፈቃድ ጠየቀ

ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው የኢትዮጵያ ማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበር ከአንድ ዓመት በፊት ያቋረጠውን የታንታለም ኮንሰንትሬት የማምረት ሒደት ለመቀጠል የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲን ፈቃድ ጠይቋል። በኦሮሚያ  ጉጂ ዞን ሰባቦሩ ወረዳ ቀንጢጫ በተባለ አካባቢ ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ የታንታለም ኮንሰንትሬት ሲመረት ቢቆይም፣  ጥሬ ምርት ከመላክ እሴት በመጨመር የተለያዩ የታንታለም ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ የተሻለ የውጪ ...

Read More »

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አዲስ ክብረ-ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈች

ግንቦት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው እሁድ እንግሊዝ ውስጥ ማንችስተር ከተማ ላይ በተደረገው ዓመታዊ የሩጫ ውድድር፤ ዝነኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በአስደናቂ ብቃት የዓለምን የ10 ኪሎ ሜትር ክብረወሰን በማሻሻል ማሸነፏ ታወቀ።   እስከ አምስት ኪሎሜትር ድረስ ያለውን ርቀት ከኋላ ሆና ስትሮጥ የነበረችው ጥሩነሽ፣ ከዚህ በኋላ ግን ድንገት አፈትልካ በመውጣት ቀሪውን አምስት ኪሎሜትር ውድድሩን በመምራት ነበር ያጠናቀቀችው። አትሌት ...

Read More »

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በገንዘብ የአለማችን ሀብታም ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የበቁ መሆናቸው ተዘገበ

ግንቦት  ፲፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ዘ ሪቸስት ዳት ኦርግ” የተሰኘው ድረ-ገፅ ይፋ እንዳደረገው፤ የቀድሞው ጠ/ ሚ/ር መለስ ዜናዊ የ3 ቢሊዮን ዶላር ባለቤት በመሆን ነው ከዓለማችን ፖለቲከኞች የሁለተኛ ደረጃን የያዙት። “ዘ ሪቸስት” የተሰኘው ይህ ድረ-ገፅ፤ በአንደኛ ደረጃ ባለፀጋ ሲል ያሰፈራቸው የቀድሞውን የጣሊያን ጠ/ሚ/ር ሲልቪዮ በርሎስኮኒን ሲሆን አንደኛ ደረጃ ያስቀመጣቸውን የ5.9 ቢሊዮን ዶላር ያፈሩት ከፖለቲካው መድረክ ሳይሆን በሜዲያው መስክ ከተሰማሩበት ...

Read More »