.የኢሳት አማርኛ ዜና

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሊኒየሙ የልማት ግብ ሲጠናቀቅ በህገወጥ የገንዝብ ዝውውር ላይ እንደሚዘምት አስታወቀ

ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለማቀፍ እውቅና ያላቸውን ሰዎች ያካተተው የተመድ ከፍተኛ ፓናል ፣ የሚሊኒየም የልማት ግቦች መርሀግብር ከሁለት አመት በሁዋላ ሲጠናቀቀር ፣ በህገወጥ መንገድ ከደሀ አገሮች እየተዘረፈ በውጭ ባንኮች  በሚቀመጠው ገንዘብ ላይ ፊቱን እንደሚያዞር  አስታውቋል። ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ከላከው ዜና ለመረዳት እንደተቻለው ፣ በአለፉት 30 አመታት ከአፍሪካ 1 ትሪሊዮን 300 ቢሊዮን ዶላር ተዘርፎ በውጭ ባንኮች ተቀምጧል። ...

Read More »

በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱት ሀይሎች ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ የታች አርማጭሆ አንድነት ሰብሳቢ እና ሌሎች 15 ሰዎች ቶርቸር ተፈጸመባቸው

ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር የታች አርማጭሆ ሰብሳቢ የሆኑት   ሚያዚያ 17 ፣ 2005 ዓም በቁጥጥር ስር በዋሉበት እለት ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ቤተሰባቸው ለኢሳት ገልጸዋል። እህታቸው ወ/ሮ የንጉሴ ሲሳይ  ወንድማቸው ተዘቅዝቆ ለረጅም ሰአታት እንዲቆይ መደረጉን፣ በእጆቹ ጣቶች  መካከል ብረት እንዲገባ በመደረጉ ጣቶቹ ሽባ መሆናቸውን እንዲሁም እግሮቹ በድበዳ መመለጣቸውን  እያለቀሱ ተናግረዋል። አቶ ተገኝ በድብደባ ብዛት ለመሞት ሲቃረቡ ...

Read More »

በባህርዳር ከ17 ሰዎች ሞት ጋር በተያያዘ ከታሰሩት 22 ፖሊሶች መካከል 4ቱ ተፈቱ

ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በባህርዳር ከተማ 17 ንጹሀን ዜጎችን በግፍ ከገደለው የፌደራል ፖሊስ አባሉ ፈቃዱ ናሻ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት መካከል 4ቱ ዛሬ ሲለቀቁ፣ 5ቱ ደግሞ ከስራ ተባረዋል። ከዚህ ሌላ  2ቱ ፖሊሶች በከፍተኛ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ሲደረግ፣ 9ኙ ደግሞ በህዳር 11 ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው። ሥለ ጉዲዩ  ምስክርነት የሰጠችው የፖሊስ ...

Read More »

የተለያዩ የግል ተቋማት የህክምና ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ እና የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ14 የግል ኮሌጆች የተሰባሰቡ 5 ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች ትናንት ሰኔ 27፣ 2005 ዓም የትምህርት ማቆም አድማ በማድረግ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር አምርተዋል። የትምህርት ሚ/ር ባለስልጣናትም ተማሪዎቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ጠይቀው ፣ ተማሪዎቹ የትምህርት ሚኒስቴርን ግቢ ለቀው ካልወጡ በፖሊስ ተገደው እንደሚወጡ ሲነገራቸው ተወካዮችን ወክለው መሄዳቸው ታውቋል። የትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናትም ተማሪዎች ላቀረቡት ጥያቄ ለዛሬ ...

Read More »

በእስር ላይ የሚገኘው የባለራእይ ወጣቶች አመራር በህግ አማካሪውና በቤተሰቦቹ እንዳይጎበኝ ተከለከለ

ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ማህበሩ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የባለራእይ ወጣቶች የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ” ግንቦት27 ፣ 2005 ኣም ከጧቱ ሶስት ሰአት ላይ ሜክሲኮ በሚገኘው ፍርድ ቤት ለ3ኛ ጊዜ ቢቀርብም፣ ጉዳዩ ሳይታይ ቀጠሮ ተጠይቆበት እንደገና ወደ እስር ቤት ተመልሷል። ማህበሩ አያይዞም ከግንቦት 27 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ ወጣት ብርሀኑ በቤተሰቡም ሆነ በጓደኞቹ ...

Read More »

የዜና እርማት

ግንቦት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተመልካቾቻችን እና አድማጮቻችን፣ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዕለት በስዊዘርላንድ-ጄኔቫ ስለተካሄደው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ባስተላለፍነው ዜና ላይ፤ ተቃውሞ ባሰሙት ኢትዮጵያውያን ሳቢያ ዝግጅቱ እንደከሸፈ  መዘገባችን ይታወሳል። ይሁንና ዜናው ስህተት እንዳለበት የደረሰንን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረግነው ማጣራት መሰረት የኢትዮጵያውያኑ ተቃውሞ እስከ ምሽቱ 6፡00፣  ዝግጅቱ ደግሞ ከሌሊቱ 6፡00 ጀምሮ  እንደተካሄደ ተገንዝበናል። በመሆኑም  በስዊዘርላንድ-ጄኔቭ የተካሄደውን የዓባይ ቦንድ ሽያጭ ...

Read More »

ከተቃውሞ ሰልፉ በሁዋላ በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አመራሮች እየተገመገሙ ነው

ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ ያካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በማግስቱ የኢህአዴግ ባለስልጣናት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ አመራሮችን እንዲሁም በፕሮፓጋንዳ መስክ ላይ የተሰማሩትን በመጥራት ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ግምገማ እያካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። አብዛኞቹ አመራሮች ሂስና ግለሂሳቸውን እንዲያወርዱ የተጠየቁ ሲሆን፣ የድርጅቱ አባሎች በጸረ ህዝቦች ፕሮፓጋንዳ በመወናበድ እና ለግንባሩ ርእዮተ አለም ትኩረት ባለመስጠት ድርጅቱን ከውስጥ እያዳከሙት ...

Read More »

በአርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ የሚመራ የአርቲስቶች እና ጋዜጠኞች ቡድን የሶማሊ ክልልን ጎብኝቶ ምስክርነት ሊሰጥ ነው

ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደሬሽን ምክር ቤት በአርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ የሚመራ  የአርቲስቶች ቡድንን እና ጋዜጠኞችን በማሰባሰብ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የጎብኝት መረሀ ግብር በጅጅጋ እና በሌሎች የሶማሊ ዞኖች አዘጋጅቷል። አርቲስቶቹና ጋዜጠኞች ከትናንት ሰኞ ጀምሮ ወደ ጂጂጋ ይጓዛሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ጉብኝታቸውም ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ታውቋል። የጉዞው ዋና አላማ በክልሉ የሚገኙ የጸጥታ ችግር አለባቸው የሚባሉ ቦታዎችን በመጎብኘት ልማቱ ...

Read More »

የግብጽ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ላይ ሲመክሩ የሚያሳይ ቪዲዮ የፋ ወጣ

ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግብጹ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ የተለያዩ  የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን በመሰብሰብ በመሰራት ላይ ባለው የአባይ ግድብ ዙሪያ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ ወይይቱ ለተቃዋሚዎች ሳይነገር በቀጥታ በቴሌቪዥን እንዲተላለፍ በመደረጉ ተቃዋሚዎች ቅሬታቸውን ሲገልጹ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ደግሞ ይቅርታ ጠይቋል። አሶሽየትድ ፕሬስ እንደዘገበው በውይይቱ ላይ የተለያዩ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች አስገራሚ አስተያየቶችን ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንት ሙርሲ በቅርቡ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ...

Read More »

ኢህአግ በሁመራ አካባቢ ጥቃት መፈጸሙን ገለጸ

ግንቦት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሉግዲና በበረከት ተከታታይ ወታደራዊ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል። በግንቦት 25-2005 ዓ.ም በሁመራ ልዩ ስሙ በረከት በተሰኘ ስፍራ ከመከላከያ ሰራዊት  35ኛ ክፍለጦር እና ከሚሊሻ ሰራዊት ጋር በተከታታይ በስምንት/8/ ዙር ፋታ የለሽና እልህ አስጨራሽ ውጊያ 148 ሙት፣ 374 ቁስለኛ፣ 31 ክላሽንኮፍ ጠመንጃ፣  47 የእጅ ቦንብ ፣2 ስናይፐር፣ 3 መትረየስና የተለያዩ ...

Read More »