ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እየተገባደደ ባለው የኢትዮጵያዊያን የ2005 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ማለትም ከሐምሌ 1/ 2004 እስከ መጋቢት 30/ 2005 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ዋናዎቹ የወጪ ንግድ ምርቶች በዓለም ገበያ ገቢያቸው ማሽቆልቆሉን ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተገኘ መረጃ ጠቁሟል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜያት 2 ነጥብ 2 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህ ገንዘብ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ5 በመቶ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢህአዴግ የዲያስፖራ ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴውን ቀጥሎአል
ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሕአዴግ መንግስት ዲያስፖራውን የስርዓቱ ደጋፊ ለማድረግ የቀየሰውን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ በቅርቡ ከተለያዩ አህጉራት ከሄዱ የዲያስፖራ አባላት ጋር እየመከረ ሲሆን፣ ዲያስፖራው በአገር ውስጥ ስለሚያገኛቸው ጥቅሞች ገለጻ እየተደረገለት ነው። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በሚልንየም አዳራሽ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ነዋሪነታቸው በውጭ አገር የሆኑ የስርዓቱ ደጋፊዎች መገኘታቸው የታወቀ ሲሆን ጠቅላላ ...
Read More »የኢትዮጵያ እና የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተወያዩ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያና የግብጽ ፍጥጫ እያየለ መምጣቱን ተከትሎ የግብጽ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ሞሀመድ ካሚል በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ጋር ተነጋግረዋል። ሬዲዮ ፋና ባቀረበው የቀን ዘገባ ላይ የሁለቱ አገራት ባለስልጣናት ባደረጉት የማለዳው ውይይት ከስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸውን ገልጿል። ሬዲዮ ፋናም ሁለቱ ባለስልጣኖች ስምምነት ላይ አልደረሱም የሚል ዜና ይፋ ካደረገ ...
Read More »በአፋር የገዋኔ ነዋሪዎችና በፌደራል ፖሊሶች መካከል ያለው ውዝግብ እንደቀጠለ ነው
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ትናንት ገዋኔ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አንድ ሾፌር መገደሉን ተከትሎ በፖሊሶች እና በነዋሪዎች መካከል አዲስ ውዝግብ ተከስቷል። በአካባቢው የተሰማሩት የፌደራል ፖሊስ አባላት ለሹፌሩ መገደል የገዋኔ ነዋሪዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። ነዋሪዎቹ በበኩላቸው ግድያውን የፈጸሙት እነሱ አለመሆናቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ሀይሰማ ወልዶ እና ሌሎች ሁለት የፌደራል ፖሊስ አዛዦች በተገኙበት ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ “የፌደራል ፖሊስ አባላት ሶስት ጊዜ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት የሚገኙበት የተቃውሞ ሰልፍ በብራሰልስ ይካሄዳል
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በተለያዩ የአውርጳ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ ያቋቋሙት “በአውሮጳ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ታስክ ፎርስ” የኢህአደግ መንግሥት በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲያቆምና የዜጎችን መብት እንዲያከብር ለመጠየቅ የፊታችን ረቡዕ ጁን 19 ቀን 2013 የአውሮጳ ህብረት መቀመጫ በሆነው ብራስልስ የህብረቱ ካውንስል ጽ/ቤት ፊት ለፊት ታላቅ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ መዘጋጀታችውን ለኢሳት ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሎአል። ...
Read More »የሁለት የቤንሻንጉል ጉምዝ ምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት ተነሳ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረዋል ያላቸውን ሁለት የምክር ቤት አባላት የሕግ ከለላ ማንሳቱን አስታወቀ። የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ የሆኑት አቶ አቡሽ ሙስጠፋ እንደገለጹት ከሆነ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ያቋቋመው አጣሪ ቡድን ባሰባሰበው መረጃ መሠረት በካማሽ ዞን በያሶ ወረዳ የሚኖሩ በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ...
Read More »በደብረ ታቦር ከተማ 2 ወጣቶች በደህንነት ሀይሎች ተይዘዉ ተወሰዱ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፋርጣ ወረዳ በመንገድ ትራንስፓርት ውስጥ የሚሰሩ ምስጋናዉ መልካም እና በሪሁን ዉበቴ የተባሉ ወጣቶች ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ እና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች። ገልጸዋል። በደብረታቦር ባለፈው ሳምንት 6 ወጣቶች በተመሳሳይ ምክንያት መታሰራቸው ይታወቃል። በፈቀደ እግዚ ኮሌጅ መምህር የሆኑት ታደሰ መንግስቴ እና ፍቃዱ ጌትነት እንዲሁም በደብረ ታቦር የ2ኛ ደረጃ መምህር ...
Read More »ኮከብ አርማ የሌለው ሰንደቅ ዓላማ ተጠቅማችኃል በሚል የእግር ኳስ ደጋፊ ወጣቶች ተደበደቡ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢትዮጵያ ትናንት ደቡብ አፍሪካን ማሸነፉዋን ተከትሎ ምሽት ላይ በነቂስ ወደ አደባባይ ወጥተው ድጋፍ ካደረጉት የባህር ዳር ነዋሪዎች መካከል በዛ ያለ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች “የኮከብ ዓርማ የሌለውን ሰንደቅ ዓላማ በመልበሳቸው፣ እንዲሁም ‹‹ሰማያዊ ፤ሰማያዊ ደገመው ዋልያዊ››፣ “ኢትዮጵያዊው ለሰንደቅ አላማው ፤ለሰማያዊው ” እያሉ ደስታቸውን በመግለጻቸው፣ ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው አምሽተዋል። ፖሊሶች ሰንደቅ ዓላማውን ...
Read More »በአባይ ግድብ ዙሪያ ከፍተኛ ጥበቃ ማድረግ ተጀመረ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው የደህንነት መረጃ እንዳመለከተው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ቻይና እና ሩሲያ ሰራሽ ራዳሮች ሰሞኑን በአካባቢው ተተክለዋል። መንግስት ማንኛውንም አይነት ድንገተኛ የአየር ወይም የሰርጎ ገቦች ጥቃት ለመከላከል ዘመናዊ ራዳሮችን ከመትከል በተጨማሪ የተወሰኑ የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት በአስችኳይ ወደ አካባቢው እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል። በፌደራል ፖሊስ ሲደረግ የነበረው ጥበቃ በመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲጠናከር ያደረገው መንግስት ፣ በሻለቃ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ <<በአባይ ወንዝ ላይ የተጀመረው ግድብ ከሐገራዊ ጠቀሜታው ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የስልጣን እድሜ ለማራዘም የታለመና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚደለቅ ከበሮ ነው>> አለ።
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ ፦<<እነሱ ከ አባቶቻቸው አይበልጡም፤ እኛም ከ አባቶቻችን አናንስም>> በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ወረራና ደባ መፈፀም የጀመረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ከመነሳቷ እጅግ በርካታ አመታት በፊት ጀምሮ መሆኑን በመጥቀስ ሀገራችን ከግብፅም ሆነ ከሌሎች የተቃጣባትን ተደጋጋሚ ወረራዎች በመመከትና ጠላቶቿንም ድባቅ በመምታት ነፃነቷን ጠብቃ መኖሯ ለጠላቶቿ መራር የሆነ እውነት ነው ...
Read More »