.የኢሳት አማርኛ ዜና

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ከናይጀሪያ ለቀቁ

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ህብረት በጤና ጉዳይ ላይ ለመመካከር በናይጀሪያ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ሰብሰባቸውን ሳይጨርሱ ወደ አገራቸው የተመለሱት ፣ አለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የናይጀሪያ መንግስት ይዞ እንዲያስራቸው አቤቱታውን ለፍርድ ቤት ካቀረበ በሁዋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ ሰኞ እለት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ በድንገት አገሪቱን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል። ፕሬዚዳንት በሽር ናይጀሪያ ሲገቡ ...

Read More »

በቂልንጦ እስርቤት የእሰረኞች ደም በድብደባ እንደጎርፍ መፍሰሱን የአይን እማኞች ተናገሩ

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርብ ፣ ሀምሌ 6 2005 ዓም በእነ አቶ ተሻለ ኮርኔ መዝገብ የተከሰሱ 69 የኦሮሞ ተወላጆች ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ፍርድ ቤት የሚወስዳቸው ፖሊስ ያጣሉ። በቅጽል ስሙ ሻእቢያ እየተባለ የሚጠራውን የእስር ቤቱን ሀላፊ ሲጠይቁት ቀጠሮአቸው ለ4 ወር መራዘሙን ይነግራቸዋል። እስረኞቹም ” ከ2 አመታት በላይ የላፍትህ ታስረን በመጨረሻ ብይን በሚሰጥበት ወቅት ለ4 ወራት ...

Read More »

በአዲስ አበባ የአንድነት ፓርቲ አባሎች እየታሰሩ ነው

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በደሴና እና በጎንደር የተሳኩ የተቃውሞ ሰልፎችን ባካሄደ ማግስት ከ30 በላይ አባሎቹ በዋና ከተማዋ የተቃውሞ ፊርማ ሲያሰባስቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ባለፉት ሳምንታትትም በተመሳሳይ መንገድ የታሰሩ እና የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ አባላት አሉ። አንድነት ፓርቲ ለ3 ወራት በሚቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ  በዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን ከማካሄድ ባሻገር ቤት ውስጥ ስብሰባዎችንና ...

Read More »

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች አመጽ እንደቀጠለ ነው።

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ሕዝበ ክርስቲያኑ ከጎናቸው እንዲቆም በመጠየቅ ትናንት በአመታዊ የሥላሴ ክብረ በዓል ላይ  መፈክሮችን ሲያሰሙ ውለዋል። ተማሪዎቹ ሲያሰሙዋቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል፦የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው!፣የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት!፣ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን!የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ! “የሚሉት ይገኝበታል። እንዲሁም፦”ልጆቹን የማይጠይቅ አባት ...

Read More »

የፌደራል ፖሊስ የግዥ አፈፃፀም ሥርዓት ለሙስና የተጋለጠ መሆኑን የጸረ ሙስና ኮምሽን በጥናት አረጋገጠ

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን በቅርቡ ባካሄደው የአሰራር ሥርዓት ጥናት በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የግዥ አፈፃፀም ለሙስና እና ብልሹ አሠራር የተጋለጠ ነው ብሎአል፡፡ በፖሊስ ኮምሽኑ የተጠና የጠቀሜታ ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ አዘገጃጀት አሰራር አለመኖር፣ ግዥዎችን በዕቅድና በፕሮግራም አለመፈፀም፣ በጀት መኖሩ ሳይረጋገጥ የግዥ ሂደቶችንማከናወን፣ በግዥ መመሪያው ከተቀመጠው የገንዘብ መጠን በላይ ግዥ መፈፀም እና የጨረታ ኮሚቴው ከግዥ ...

Read More »

በሮመዳን ጾም ጅማሮ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጠንካራ ተቃውሞ አሰሙ

  ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተቃውሞ ተካሂዷል። መንግስት የለም ወይ፣ የሼክ ኑር ኢማም ግድያ ድራማ ነው፣ ድራማው ይብቃ፣      መሪዎቻችን ይፈቱ፣ መሀይም አይመራንም፣ በፍትህ እጦት ድፍን አንድ አመት መንግስት ራሱ ገዳይ ራሱ ከሳሽ፣ ። አሸባሪው  መንግስት ነው፣  ፍትሕ ማዳን። ፍትህ እያሉ ቃሊቲ ገቡ ገደሉት ብለው ድራማ ሰሩ። የመንግስት ...

Read More »

በአዊ ዞን የእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገለጹ

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በሁለቱ ከተሞች በተካሄዱት ስብሰባዎች ህዝቡ በመልካም አስተዳደር ችግሮች እየተሰቃየ እንደሚገኝ በድፍረት ለመንግስት ተወካዮች ሲገልጽ ተሰምቷል። በእንጅባራ አንድ ነጋዴ ሲናገሩ የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀረቡዋቸው ሪፖርቶች ለራሳቸው የሚጠቅሙ እንጅ ህዝቡ የሚያያቸው አይደሉም በማለት በማስረጃ አስደግፈው አቅርበዋል። ነጋዴው እንዳሉት እቃዎች ሳይገዙ እንደተገዙ ተደርጎ ይወራረዳሉ፣ ጥራት ያላቸው እቃዎች አይገዙም፣ የመንግስት መጋዘኖችም በባለስልጣናት ይዘረፋሉ። የከተማዋ ባለስልጣናት ከሙስና ...

Read More »

በ1976 ዓ.ም የተቋቋመው አንጋፋው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ማኔጅመንት ከሠራተኛው ጋር እሰጣ አገባ ውስጥ ገባ

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በሀላፊነት ላይ የሚገኙ የድርጅቱ  ሠራተኛ እንደተናገሩት በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር በቦርድ ሰብሳቢነት ወደመድን ድርጅት ከመጡ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ዘረኝነትና ግልጽ የሆነ ዘረፋ በድርጅቱ ውስጥ በመንሰራፋቱ  በርካታ ባለሙያዎች ድርጅቱን ለመልቀቅ እየተገደዱ ነው። ችግሩን ቦርዱ ተመልክቶ ሠራተኛውን እንዲያወያይ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብለትም እነአቶ ሙክታር ፈቃደኛ ...

Read More »

ታዋቂው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆኖ በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ሊመረጥ እንደሚችል ተጠቆመ

ሐምሌ ፭( አምት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሻለቃ ኃይሌ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት እንዳለው ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መግለጹን ተከትሎ ኢህአዴግ መራሹ ራዲዮ ፋና ባልተለመደ መልክ ዜናውን ደጋግሞ እንዳራገበው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ጠቅሰው ፣ ሀይሌ የሰጠውም መግለጫ ሆነ የሬዲዮ  ፋና ዘገባ በድንገት የሆነ ሳይሆን ታቅዶበት የተደረገእንደሚሆን ግምታቸውን አስቀምጠል፡፡ በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኙት መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሁለተኛውን የሥልጣን ዘመናቸውን ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ በደሴና ጎንደር የሚካሄዱትን ሰላማዊ ሰልፎች ለማደናቀፍ እየሞከረ ነው የፓርቲው ሰዎች በአቋማቸው ጸንተዋል

ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሀምሌ 7፣ 2005 ዓ/ም በደሴና ጎንደር ከተሞች አንድነት ፓርቲ የጠራቸው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች በታቀደላቸው ጊዜ እንደሚካሄዱ ከመንግስት እውቅና የተሰጣቸው ቢሆንም፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና ባለስልጣናት የቅስቀሳ ወረቀቶችን የሚበትኑትን ሰዎች ከማሰር እና ከማስፈራራት አልፈው ፣ ከአዲስ አበባ የሄዱ የፓርቲው አመራሮች አልጋ እንዳያገኙ የሆቴል ባለንብረቶችን እስከ ማስፈራራት መድረሳቸውን የፓርቲው አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል። የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ...

Read More »