.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአዳማ/ ናዝሬት የአንድነት ፓርቲ አባላት መዋከባቸው ታውቀ

ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በከተማዋ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ የቅስቀሳ ወረቆቶችን ሲበትኑ የነበሩ ወጣቶች ለአጭር ጊዜ ተይዘው ተፈተዋል። ፓርቲው ሰለማዊ ሰልፍ እንዲአካሂደ ፈቃድ ከተሰጠው በሁዋላ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እንጅ ወረቀት የመበተን ፈቃድ አልተሰጣችሁም በሚል ሰበብ ወጣቶቹ እንዲታሰሩ መደረጉ ታውቋል። ኢሳት ከኢህአዴግ የአዳማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ ፣ ፖሊሶችና የደህንነት ሀይሎች ፓርቲው የሚያደርገውን ...

Read More »

ላለፉት 2 አመታት ስርአቱን በሀይል ለመፈታተን ከሞከሩት ሁሉ የሀይማኖት እንቅስቃሴዎች ዋነኞቹ እንደነበሩ ኢህአዴግ አስታወቀ

ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው አዲስ ራእይ በሚባለው ልሳኑ ” ፣ በሀይማኖት ሽፋን የሚካሄዱ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እየተዳከሙና እየተጋለጡ መሄዳቸው ባይቀርም ባለፉት ሁለት አመታት ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርአቱን በሐይል ለመፈታተን ከመከሩት የሁከት ሀይሎች ዋነኞቹ ነበሩ ማለት ይቻላል” ብሎአል። ኢህአዴግ ከአክራሪዎች ጎን በመቆም አመጽ ለማነሳሳት ሞክረዋል ካላቸው ድርጅቶች መካከል ድምጻችን ይሰማ፣ ግንቦት 7 አሜሪካ ድምጽ ሬዲዮና ቢላል ሬዲዮ በዋናነት ተጠቅሰዋል። ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግሥት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ጥቃት አላደረስኩም ሲል መካዱን ቢቢሲ ዘገበ።

ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ ሊያደርገው የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ በሀይል የጨፈለቀው የ ኢህአዴግ መንግስት፤ በርካታ የፓርቲውን አባላት እንዳሰረ ፣ እንደደበደበና እና የጽህፈት ቤቱን ንብረት እንደመዘበረ ፓርቲው መግለጹን ቢቢሲ በትናንት ዘገባው አመልክቷል። የፓርቲውን  ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነትን በመጥቀስ የዜና አውታሩ እንደዘገበው፤ እሁድ ሊካሄድ ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፓር ቲያቸው የተዘጋጁ የድምጽ መሣሪያዎች በታጣቂዎች ተወስደዋል፤ ሰልፉም ...

Read More »

ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች በድጋሜ ታላቅ ግብዣ ተዘጋጀ

ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአራት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበትና በኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነት የኪነጥበባት ባለሙያዎች፣ ምሁራንና የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን የተሳተፉበት የጉብኝት ፕሮግራም ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 4/2005 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ይህንን መነቃቃትና የገጽታ ግንባታ አጠናክሮ ለመቀጠል ያስችላል የተባለ ታላቅ ድግስ ጳጉሜ 3 ቀን 2005 በሸራተን ሆቴል ተዘጋጀ፡፡ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች የተሰባሰቡበት ...

Read More »

አሜሪካ በሶሪያ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መቃረቡዋን ተከትሎ የመካከለኛው ምስራቅ እንደገና በጦርነት ሊታመስ እንደሚችል ተሰግቷል።

ነሃሴ ፳፰(ሃያ ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦባማ አስተዳደር በዜጎቹ ላይ የኬሚካል መሳሪያዎችን በመጠቀም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ባለው የባሽር አላሳድ መንግስት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ሲያስጠነቅቅ ከቆ በሁዋላ በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ፣ ጉዳዩን ለኮንግረስና ለሴኔት አቅርበው ለማስወሰን በመፈለጋቸው ባለፈው ሳምንት የታየው  የጦርነት ደመና ዝናቡን ሳያርከፈክፍ መጥፋቱ ይታወቃል። ይሁን እንጅ ፕሬዚዳንት ኦባማ የዲሞክራት እና የሪፐብሊካን መሪዎችን ከአነጋገሩ በሁዋላ ፣ ሁለቱም መሪዎች የሰጡዋቸው መልሶች አዎንታዊ ...

Read More »

ነሐሴ 26 የመንግስት ድጋፍ ያለው የሀይማኖቶች ጉባኤ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ያልተጠበቁ ነገሮችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  በመንግስት የሚደገፈው የሐማኖቶች ጉባኤ  በመጪው እሁድ አክራሪነት እናወግዛለን በሚል አላማ በጠራው ሰልፍ ላይ የአዲስ አበባ እና እስከ 100 ኪሎሜትር በሚደርስ ርቅት ላይ  በአጎራባች የክልል ከተሞች የሚገኙ ዜጎች በብዛት እንዲገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየዞሩ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሰንብተዋል።  የመንግስት ሰራተኞች ፣ በግል ስራ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ካልተገኙ ግን አክራሪነትን እንደደገፉ እንደሚቆጠርባቸው ...

Read More »

የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ፤

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፋና እንደዘገበው ፤ግለሰቡ በቁጥጥር ስር የዋሉት የነበራቸውን ስልጣን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል  ተጠርጥረው ነው ። ፋና ይህም ቢልም አቶ ወልደስላሴ ከደህንነት ዋና ሹሙ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር ጠብ ውስጥ ገብተው መቆየታቸው በስፋት ሲነገር ቆይቷል። በተለይ መቀሌ በተካሄደው የህወሀት ጉባኤ ላይ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በአቶ ወልደስላሴ መካከል ...

Read More »

በመላ ሐገሪቱ ለህዝብ ተብለው የተገነቡ የኪራይ ቤቶች ድርጅት መኖሪያ ቤቶች በመንግስት ባለስልጣናት የተያዙ መሆናቸውን ከኪራይ ቤቶች ድርጅት ያገኘነው መረጃ አመለከተ፡፡

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከኪራይ ቤቶች ድርጅት ባገኘው መረጃ በአዲስ አበባ የተገነቡ 2345 ቤቶች ለሚኒስትሮች እና ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ባለስልጣናት ተሰጥተዋል። የቤቶች ልማት ባካሄደው ጥናት ፣ አብዛኞቹ ባለስልጣናት የግል ቤቶቻቻውን በማከራየት በመንግስት ቤቶች ውስጥ ይኖራሉ።  ኪራይ ቤቶች ቤቶቹን እንዲለቁ ሲጠይቃቸው በግል የገነቡዋቸው ቤቶች ለደህንነታቸው ዋስትና እንደማይሰጡ በመከራከር ቤቶቹን ለማስረከብ ፈቃደኞች አልሆኑም። በትግራይ ክልለ በመቀሌ 375 ...

Read More »

በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች በስነልቦና ችግር እየተሰቃዩ መሆኑን ተገለጠ

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢትዩ -ኤርትራ ግጭት እና ኢትዮጵያ ከሶማሊያው አልሸባብ ጋር ካደረገችው ጦርነት ጋር በተያያዘ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች በስነልቦና ችግር እየተሰቃዩ መሆኑን የጦር ሃይሎች ሆስፒታል የስነ ልቦና ህክምና ቡድን መረጃ አመለከተ ከመዝገብ ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ፤ በጦርነቱ ስዓት በተከሰተ ምንነቱ ባልታወቀ የሞራል እና የስነ ልቦና ችግር ከ3 ሺ 500 በላይ ወታደሮች እስከ እብደት  በሚያደርስ በሽታ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ ጥራት ደረጃ ሊሻሻል አለመቻሉ ተገለጸ

ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዛሬው እለት 3ኛው የአማራ ክልል ትምህርት ፊስትቫል ምክትል ጠቅላይ ሚነስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን ፤የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሺፈራው ሺጉጤ ፤ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ በተገኙበት ሲከፈት፣ ዶክተር ጸሐይ ጀምበሬ ባቀረቡት ጽሁፍ፣ የመንግስት ትምህርት ቤት አሰተዳደራዊ ችግር ለትምህርት ጥራት እንቅፋት እየሆነ መጥቱዋል ብለዋል።  ከአመቱ ውስጥ  260 ቀናት ይባክናሉ ያሉት ዶክተር ጽሐይ ኢትዮጵያ በትምህርት ጥራት ...

Read More »