ጳጉሜ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሩሲያ በተካሄደው የቡድን 20 አገራት ስብሰባ ላይ የተገኙት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ፣ ከሩሲያው አቻቸው ጋር በሶሪያ ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ ቢመክሩን ስምምነት ላይ ሳይደርሱ መቅረታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ፕሬዚዳንት ፑቲን በሶሪያ የኬሚካል የጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋሉን አገራቸው ብትቀበልም ድርጊቱን የፈጸሙት ተቃዋሚዎች እንጅ የባሽር አላሳድ መንግስት አለመሆኑን ገልጸዋል። ተቃዋሚዎች የአለማቀፉ ማህበረሰብ ጣልቃ እንዲገባ በማሰብ ድርጊቱን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፉን አራዘመ
ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው የህግ ክፍልና የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ይድነቃቸው ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ቀኑ የበአል ዋዜማ በመሆኑ እና የንግድ ድርጅቶችም እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት በመሆኑ ሰልፉን ለማስተናገድ እንደማይችሉ በመግለጻቸው ለማራዘም እንደወሰኑ ገልጸዋል። አንድነት ፓርቲ መስከረም 5፣ 2006 ዓ/ም የጠራው የተቃውሞ ሰልፍ በመኖሩ በሳምንቱ ሰልፉን ለማካሄድ መወሰናቸውን አስተባባሪው ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ...
Read More »በኢትዮጵያ ከሚሊዮን በላይ በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች አሉ ተባለ
ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ኑሮ ጠንቆች ሲል ባስጠናው እና በዓመቱ መጠናቀቂያ በወርሐ ጳጉሜ ይፋ በሚያደርገው መረጃ እዳመለከተው የልመና ተዳዳሪነት በሐገሪቱ ላይ ጥቁር ጥላውን እያጠላበት ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ የቱሪስቶች የደህንነት ስጋት ከመሆን ባለፈ ለዜጎችም መትረፋቸውን ገልጿል። በመገባደድ ላይ ባለው በ2005 ዓ.ም ብቻ በአማራ ክልል ከሶስት መቶ ሺ ፣ በትግራይ ከሁለት መቶ ሺ ...
Read More »የአርበኞች ግንባር አባላት ናቸው የተባሉ ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን ነዋሪ የሆኑት ጸጋው አለሙ፤ ዋስይሁን ንጉሱ፤ ጎዳዳው ፈረደ፤ ማማይ ታከለ እና ተገኝ ሲሳይ የተባሉት ሰዎች በኤርትራ ስልጠና ካገኙ በሁዋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ በትግራይ ክልል ማካይዳ ከተማ መያዛቸውን ፋና ዘግቧል። ተከሳሾች ኤርትራ እና አውሮፓ ከሚገኙ የአሸባሪው ድርጅት የተለያዩ አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር አባላትን እየመለመሉ ወደ ኤርትራ መላካቸውን ገልጾ ፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት ...
Read More »ለታሰሩት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ረዥም ቀጠሮ ሰጠ።
ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በሽብርተኝነት በከሰሳቸውና ጉዳያቸው በመታየት ላይ ባለው የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ በፍርድ ቤት ረዥም ቀጠሮ መሰጠቱ አነጋጋሪ ሆነ። የኢሳት ዘጋቢ ከአዲስ አበባ እንዳጠናቀረው መረጃ ታሳሪዎቹ ብይን ለመስማት ከ3 ወር በላይ መጠበቅ አለባቸው። በሐምሌ ወር 2004 ኣመተ ምህረት የፈጠራ ሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ላለፉት ሀለት ኣመታት በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ የሃይማኖት ...
Read More »ኬንያ ከአለማቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አባልነት ለመልቀቅ ወሰነች
ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ከአምስት አመታት በፊት የተደረገውን ምርጫ ተከትሎ በሞቱ ከ1ሺ በላይ ዜጎች የአሁኑ አገሪቱ መሪ ኡሁሩ ኬንያታና ምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ በሰው ልጆች ላይ በተፈጸመ ወንጀል በአለማቀፉ ፍርድ ቤት ተጠያቂዎች ሆነዋል። ሁለቱም መሪዎች ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ በሚታወቅበት ሰአት አገራቸውን ከፍርድ ቤቱ አባልነት በማስወጣት ራሳቸውን ከጠጠያቂነት ለማዳን የወሰዱት እርምጃ የአገሪቱን ተቃዋሚዎች አስቆጥቷል። ሁለቱ መሪዎች ከፍርድ ቤቱ ጋር ...
Read More »ፕሬዚዳንት ኦባማ በሶሪያ ላይ ለሚወስዱት ወታደራዊ ጥቃት ድጋፍ ለማሰባሰብ እየሞከሩ ነው
ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገራቸውን ወሳኝ ፖለቲከኞች ድጋፍ ያገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ፣ አለማቀፍ ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን ዘመቻ ዛሬ በስዊድን ጀምረዋል። አለም ያስቀመጠው ቀይ መስመር አለ፣ያም መስመር ” የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን መጠቀም አይቻልም” የሚል ነው፤ አለም ለዚህ ውሳኔው በጋራ ሊቆም ይገባል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ከአውሮፓ አገራት መካከል እስካሁን ድረስ ለአሜሪካ እርምጃ ድጋፏን የገለጸችው ፈረንሳይ ብቻ ናት። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩሲያው ...
Read More »በበባህርዳር አንድ የፖሊስ ኢንስፔክተር ተገደለ
ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወረዳ ሁለት እየተባለ ለሚጠራው አካባቢ ሀላፊ የነበረው ኢንስፔክተር ምትኩ ዛሬ ጠዋት በመኪና ተገጭቶ ሞቷል። ድርጊቱን የፈጸሙት ሰዎች እስካሁን ያልተያዙ ሲሆን ፣ ጉዳዩን በመመርመር ላይ የሚገኙት ዋና ኢንስፔተር ውበቱ ለኢሳት እንደገለጹት ድርጊቱ በምን ምክንያት እንደተፈጸመ ለማወቅ ምርመራ እየተካሄደ ነው ብለዋል። በግለሰቡ የተከፉ ሰዎች ሆን ብለው ገድለውት አምልጠዋል ይባላል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ኢንስፔክተሩ እስካሁን ያለን ...
Read More »የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ገጠመው፡፡
ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒቨርስቲው የማስፋፊያ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ መንግሥት በተመደበ 859 ሚሊዮን 514 ሺ 332 ብር ከ42 ሳንቲም በ‹‹CDS consultancy›› ድርጅት አማካሪነት እና በሌሎች 15 ተቋራጮች ከ2001 ዓ/ም እስከ 2003 ዓ/ም ባሉት ጊዚያት ተጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው። አጠቃላይ ፕሮጀክቶቹን ለማጠናቀቅ የተያዘው የጊዜ ሠሌዳ ዝቅተኛው 2 ወር ከ15 ቀናት ከፍተኛው ደግሞ 49 ወራት ነው፡፡ በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ እየተከናወኑ ከሚገኙ ...
Read More »የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚ/ር በትላንትናው ዕለት በሒልተን ሆቴል ድንገት በጠራው የእራት ግብዣ አዲሱ ሚኒስትርን ከጋዜጠኞችና የኮምኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር አስተዋወቀ፡፡
ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ አቶ በረከት ስምኦንን በመተካት በሚኒስትርነት ወደ ጽ/ቤቱ የመጡት አቶ ሬድዋን ሁሴንን ያስተዋወቁት አቶ ሽመልስ ከማል ሲሆኑ ሰውየው ከሚዲያ ጋር ባላቸው ቅርበት፣በአንደበተ ርዕቱነታቸው፣በፖለቲካ ዕውቀታቸው የላቁ መሆናቸውን ለጋዜጠኞች በመንገር አስተዋውቀዋቸዋል፡፡ ከሳምንት በፊት ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርነት ተነስተው በመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታነት ማዕረግ የተሾሙት አቶ እውነቱ ደበላም በተመሳሳይ መንገድ ተዋውቀዋል፡፡ አቶ እውነቱ ወደ ...
Read More »