.የኢሳት አማርኛ ዜና

በቅርቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤ/ክ አባቶች ባሰሙት ጠንካራ ንግግር ላይ የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች አስተያየታቸውን ሰጡ

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጉባኤ ላይ የተሳተፉ አንድ የሀይማኖቱ አስተማሪ ፣ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ  ጉባኤ በ፴፪ኛው ዓመታዊ ስብሰባው ያወጣው መግለጫ ፣ በስብሰባው ላይ የተነሱትን ነጥቦች ዘርዝሮ አቀረበ ነው ብለዋል። ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሀይማኖት አባቶች በድፍረት መናገራቸው ከምን የመጣ ይመስለውታል ተብለው የተጠየቁት መምህሩ፣ ምናልባትም ለውጡ ከፓትርያርኩ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ገምተዋል። እስካሁን የነበረው ልዩነት ...

Read More »

የአቶ አስገደ ገብረስላሴ ልጆች በከፍተኛ ስቃይ ላይ ናቸው

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነባር የህወሀት ተጋይ የነበሩትና በአሁኑ ጊዜ በገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው የሚገኙት ታዋቂው ታጋይ አቶ አስገደ ገብረስላሴ ፣ ልጆቻቸው በከፍተኛ ስቃይ ላይ እንደሚገኙ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል። የማነ  የተባለው ልጃቸው፣ በእስር ቤት ላይ በደረሰበት ግፍ ምክንያት አካል ጉዳተኛ ሆኗል። አህፎም ደግሞ ከስራ ገበታው ላይ ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ፣ ላለፉት 7 ወራት ያለምንም ፍትህ ...

Read More »

በትግራይ አንድ ቄስ ተገደሉ

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ክልተ አውላዕሎ ወረዳ ፣  አይናለም እየተባለ በሚጠራው ጣቢያ በቤተክርስትያን ግንባታ ምክንያት በህዝብና አስተዳዳሪዎች መካከል አምባጓሮ ተፈጥሮ አንድ ቄስ ተገድለዋል። የመቀሌው አብርሀ ደስታ እንደዘገበው ፣ ቄሱ ህዝብና ቤተክርስትያኑ ወክለው ከመንግስት አካላት ጋር ሲከራከሩ የነበሩ ሲሆን በመንግስት ካድሬዎች የተለያየ ዛቻ ሲደርሳቸው ቆይቶ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው በሌሊት ተገድለው ተገኝተዋል። ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም አያይዞ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የውይይት መድረክ በስዊድን የውይይት መድረክ አዘጋጀ

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኒታን በተመለከተ በተለይም በቅርቡ በስዊድን ቴሌቪዥን  የኦጋዴን ህዝብ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ያሳየውን ዶክመንትሪ ፊልም የተመለከቱ የስዊዲን የህግ ጠበቃና የአለም አቀፍ የህግ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጁሪስት ስቴላ ያርዴት የመንግስት ባለስልጣናትን በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለመክሰስ እንደተዘጋጁ በማስታወቃቸው እሳቸውንና ሌሎችን እንግዶች በመጋበዝ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል። በጉራፈርዳ፤በቤንሻንጉል፤በአሶሳ፤በአርባጉጉና ...

Read More »

ኦብነግ በመንግስት ባለስልጣናት ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት በም/ጠ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሚመራው የልኡካን ቡድን ላይ ጥቃት ፈጽሞ በርካታ ወታደሮችን መግደሉን የግንባሩ ቃል አቀባይ ለኢሳት ገለጹ። አቶ ሀሰን አብዱላሂ እንደገለጹት ጥቃቱ የተፈጸመው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ9 የክልል መሪዎችንና ባለሀብቶችን አስከትለው በአካባቢው ጉብኝት ለማድረግ ቀብሪደሀር አየር ማረፊያ ባረፉበት ወቅት ነው። ባለስልጣኖቹ ጉበኝት እንደሚያደርጉ አስቀድሞ ተነግሮን ስለነበር ጥቃቱን ለመፈጸም በበቂ ...

Read More »

በቂ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስት ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ አለበት” ሲል አንድነት ፓርቲ ገለጸ

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ይህን የገለጸው ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ” በቂ ጥበቃ የለንም በሚል ሰላማዊ ሰልፍን እንደሚከለክሉ” መናገራቸውን ተከትሎ በሰጠው መልስ ነው። ” በቂ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስት ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ይቅርታ ጠይቆ መሄድ እንጅ ከአሁን በኋላ መብታችሁን አታገኟትም ” በማለት መዛት ትዝብት ውስጥ የሚጥል ድርጊት ነው ብሎአል አንድነት በመግለጫው፡፡ አንድነት  ” ተገዥነቱን ለህዝቡና ለህግ አድርጎ በአምባገነኖች ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ስር የነበሩ ሁለት ወረዳዎችን በትግራይ ክልል ውስጥ ለማካተት እንቅስቃሴ መጀመሩን ፍኖተ-ነፃነት ዘገበ።

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፦አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ከዚህ በፊት በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ስር የነበሩ ቢሆንም፤  መሬቱ  ግን ባብዛኛው በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል በመጡ ገበሬዎች ተይዟል፡፡ ቦታዎቹ በብዛትና በስፋት የሰፈሩት ገበሬዎቹች አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ጥቅምት 5 ...

Read More »

ሙሉ ክፍያ የከፈሉ የ40/60 መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ቤቱን ራሳቸው እንዲሠሩ መንግስት ማግባባት ጀመረ።

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ራሱ  የ 40 በ 60 መኖሪያ ቤት ሠርቶ  ለመስጠት የሰጠውን መግለጫ አምነው ከ81 ሺህ ሰዎች በላይ ሙሉ ክፍያ ከፈፀሙ በሁዋላ፤  ሀሳቡን በመቀየር ከፋዮቹ በማህበር ተደራጅተው ቤቱን ራሳቸው እንዲሠሩ መወሰኑ ተመዝጋቢዎችን አሳዝኗል። እንደ ሪፖርተር ዘገባ በአሁኑ ጊዜ  መቶ በመቶ  የከፈሉ የ40/60 ተመዝጋቢዎች በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር ወደ ተነደፈው ፕሮግራም እንዲዛወሩ የአዲስ አበባ አስተዳደር ...

Read More »

መለስ የሚባል ራእይ የለም ሲሉ አቶ ስብሀት ነጋ ተናገሩ

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት) ውስጥ የተካረረ አለመግባባት እንደተፈጠረ በስፋት በሚነገርበት በዚህ ወቅት አቶ ስብሀት ነጋ ፣ የኢህአዴግ እንጂ የመለስ የሚባል ራእይ የለም ብለዋል። የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት ከጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። አቶ ስብሀት ፦” መለስ የ ኢህአዴግን ራዕይ ለማስፈፀም ከፊት ሆኖ ብዙ ሥራ ሠራ እንጂ ራዕዩ የመለስ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የወጭ ንግድ ከፍተኛ ድክመት እየታየበት ነው

ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንግድ ሚኒስቴርና የክልሉ ቢሮዎች የ2006 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ  በጊዎን ሆቴል ባደረጉበት ወቅት ሚኒስቴሩ አቶ ከበደ ጫኔ ” በ2005 የበጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም የታሰበውን ያክል ትርፋማ መሆን አልተቻለም፡፡” ብለዋል።  ችግሮቹ ሐገራዊ ፣ አለማቀፋዊና አህጉራዊ ይዘት እንዳላቸውም ሚኒስትሩ አክለዋል። በ2005 በጀት አመት 4 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን  ዶላር ለመሰብሰብ ታቅዶ  68 ነጥብ ስድሰት ...

Read More »