ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ኅብረት በዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ የያዘውን አቋም እንዲደግፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ጥያቄ አቀረቡ፡፡ ጥያቂያቸውን ለመቀበል አውንታዊ ምላሽ እንደገኙ በመግለጽ አፈጉባኤው ለጋዜጠኞች ቢናገሩም ጉዳዩ ተቀባነት ያገኘው ለውይይት እንጅ ለማጽደቅ አይደለም ተብሎአል። የአፍሪካ የካረቢያንና የፓስፊክ አገራት ፓርላማ 34ኛ መደበኛ ጉባዔ ትላንት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን በተካሄደበት ወቅት አፈ ጉባዔ አባዱላ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በጎንደር ዩኒቨርስቲ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ
ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ተማሪ አንተነህ አስፋው የተገደለው በዩኒቨርስቲው የጸጥታ ሀይሎች መሆኑ ታውቋል። ይህን ለመቃወም የወጡ በሺ በሚቆጠሩ ተማሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ከ120 በላይ ተማሪዎች እንደታሰሩ ታውቋል። የተወሰኑ ተማሪዎች ከፉኛ በመደብደባቸው ሆስፒታል ገብተዋል፣ የአንድ ተማሪ ህይወትም በአሳሳቢ ሁኔታ ላኢ እንደሚገኝ ታውቋል።
Read More »የታላቁ ሩጫ ውድድር በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃና አጀብ ተካሄደ
ህዳር ፲፮(አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታላቁ ሩጫ በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ሥር ሆኖ እሁድ ህዳር 15 ቀን 2006 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ መነሻውን ጃንሜዳ በማድረግ ፥ በ6 ኪሎ አደባባይ ፣ በምኒሊክ ሆስፒታል፣ በቀበና ፣በ አቧሬ ፣ በእንግሊዝ ኤምባሲ ፣ በመገናኛ አደባባይ በማደረግ ተመልሶ ጃንሜዳ የተጠናቀቀው ይህ ለ 13ኛ ጊዜ የተካሄደው ውድድር ከወትሮው በተለየ ጥበቃና የፖሊስ ተደጋጋሚ ፍተሻ በመታጀብ ነበር፡፡ ቅዳሜ ...
Read More »መንግስት ከሳዑዲ ዓረቢያ የተመለሱ ኢትዮጵያዊያንን ባለሃብቶች እንዲረዱዋቸው በመማጸን ላይ ነው።
ህዳር ፲፫(አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳዑዲ ዓረቢያ ኢትዮጵያዊያን በአስከፊ ሁኔታ እንዲባረሩ ከተደረገ በኃላ መንግስት በሳዑዲ ስፖንሰርነት ያጓጓዛቸውን ከ10ሺ በላይ ተመላሾች በካድሬዎች ማሰልጠኛ በሆነው የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በማሳረፍ ባለሃብቶች እንዲረዱዋቸው በመማጸን ላይ ነው። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለተመላሾቹ ማቋቋሚያ መንግስት 50 ሚሊየን ብር መመደቡን፣ ገንዘቡ ሊያድግ እንደሚችልና በማቋቋም ረገድ ችግር እንደሌለ ከገለጹ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ...
Read More »በቡራዩ ቤቶችን ማፍረስ ቀጥሎአል
ህዳር ፲፫(አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር ትናንትና ዛሬ በቡራዩ አካባቢ ከ1 ሺ ያላነሱ ቤቶችን ማፍረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎች እንደሚናገሩት መስተዳድሩ ምንም አይነት መጠለያ ሳያዘጋጅ እና ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ እስከ ሙሉ የቤት እቃዎቻቸው ቤቶቻቸውን በድንገት በማፍረሱ ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀዋል። አለማየሁ የተባለ አንድ ወጣት የወላጆቹ ቤት ሲፈርስ በማየቱ ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት፣ በህይወቱ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሲሞክር ...
Read More »በኢትዮጵያ 38 ሚሊዮን ህዝብ የሚጸዳዳው ሜዳ ላይ ነው ተባለ
ህዳር ፲፫(አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዩኒሴፍ ባወጣው ሪፖርት እንደማለከተው ይህን ችግር ለመቅረፍ የኮሚኒቲ አስተባባሪዎች ከፍተኛ ሚና መጫወት አለባቸው። ኤርትራ ውጭ ላይ መጸዳዳትን በማስቀረት ከፍተኛ ድል ማስመዝገቡዋን ዩኒሴፍ ጠቅሷል። በመላው ኤርትራ ውጤታማ ስራ በመሰራቱ አገሪቱ ውጭ ላይ መጸዳዳትን ያስቆመች አገር የሚል ሰርተፊኬት እንደሚሰጣት ድርጅቱ ገልጿል። በአለም ላይ 34 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ንጹህ የመጸዳጃ ቦታ የላቸውም።
Read More »በአቶ መለስ ትእዛዝ በሳውድ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ንብረት ተወርሶ ኢምባሲና የአምባሰደሩ መኖሪያ ቤት እንደተሰራበት ታወቀ
ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በደረሰው አስተማማኝ መረጃ መሰረት በሳውድ አረቢያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ለትምህርት ቤት መገንቢያ እና ለችግር ግዜ ይሆነናል በማለት ከግል ኪሳቸው እያወጡ በደረግ ዘመን ሲያጠራቅሙት የነበረውን ገንዘብ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በሰጡት ትእዛዝ ገንዘቡ ተወርሶ በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲና የአምባሳደሩ መኖሪያ እንዲሁም ጅዳ የሚገኘው የቆንስላ ጽህፈት ቤት እንዲሰራበት ተድርጓል። ኮሚኒቲው በወቅቱ 50 ሚሊዮን ...
Read More »ከሳውድ አረቢያ የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር በተመለከተ የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡት መግለጫ ህዝቡን ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል
ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘግይቶም ቢሆን ችግረኛ ኢትዮጵያውያንን ከሳውድ አረቢያ ማስወጣት የጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት፣ እስካሁን ድረስ የተመላሾችን አሀዝ በተመለከተ የሚሰጠው መግለጫ ግን ህዝቡን ጥርጣሬ ላይ መጣሉን የኢትዮጵያው ዘጋቢያችን ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በቲውተር ወደ አገር ቤት የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 10 ሺ 707 ነው በማለት ገልጸዋል። ይሁን እንጅ የእርሳቸው ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ...
Read More »በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን የመብት ጥሰት ለመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች እንደቀጠሉ ነው
ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሰኞ ኖቬምበር 25፤ 2013 ከ ጠዋቱ 8:30 ጀምሮ ሚድራንድ በሚገኘው ፓን አፍሪካ ፓርላማ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያዘጋጁ ለኢሳት ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ተማጽነዋል።
Read More »በሚኒስትር ማእረግ የሚለው ሹመት ውዝግብ እያስነሳ ነው
ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት አቶ መላኩ ፈንታ ክሳቸው በየትኛው ፍርድቤት ይታይ የሚለውን ጉዳይ ፥ የህገመንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል በሚል ለሕገመንግስት አጣሪ ጉባኤ መምራቱ አንዳንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ሹማምንትን እንዳላስደሰተ ታውቋል። ሰኞ ህዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም በነበረው የችሎት ውሎ አቶ መላኩ ፈንታበሚኒስትር ማዕረግ ተሸመው ሲያገለግሉ እንደነበሩና በወቅቱም የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል ...
Read More »