.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤቱን እንዲለቅ ትእዛዝና ማስጠንቀቂያ ተሰጠው::‪

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ  በአስቸኳይ እንዲለቅ  ትዕዛዝ ደረሰው። በዛሬው እለት ከሰኣት  በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከአራት ግለሰቦች ጋር በመምጣት ፦”ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው” ሲሉ ከውል ውጪ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ቤቱን ገዛሁት የሚለው  ግለሰብ በበኩሉ፦”ቤቱን የኔ  ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁልኝ፣ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ” ሲል አመራሮቹ ...

Read More »

ኦብነግ ከመንግስት ሀይሎች ጋር መዋጋቱ ተዘገበ

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ኦጋዴን ፕሬስ እንደዘገበው የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ከመከላከያ ሰራዊት እና ከልዩ ሚሊሺያዎች ጋር ባደረገው የተኩስ ልውውጥ 70 የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደተገደሉ በእርሱ ወገንም የተወሰኑ ታጣቂዎች እንደሞቱ ገልጿል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ 3  የመንግስት ወታደራዊ አዛዦችም ተገድለዋል። መንግስት አስተያየተቱን ባይሰጥም ልዩ ሚሊሺያ የሚባለው ሀይል የኦብነግን ወታደራዊ አዛዥ መግደሉን ለጋዜጣው እንደገለጹለት ተዘግቧል። በደጋሀቡር፣ ኮራሄና ፊክ ...

Read More »

70 ድርጅቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከሰሱ

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ፋና እንደዘገበው በአዲስ አበባ በግሉ ዘርፍ ከተሰማሩ 470 ቀጣሪ ድርጅቶች መካከል 70 ዎቹ ሰዎችን በህወጥ መንገድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን ያዘዋውራሉ ተብሎ ክስ ተመስርቶባቸዋል። የሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት ኤፍሬም ግዛው ፣ በድርጅቶች ላይ ክስ ለመመስረት አስፈላጊው መረጃ ሁሉ ተሰብስቧል። የአዲስ አበባ መስተዳድር በበኩሉ እርምጃው በሌሎች ድርጅቶችም ላይ እንደሚቀጥል ...

Read More »

የትምባሆ ፍላጎት መቀነስና የአቅርቦት ቁጥጥር ሥርዓት አገራት እንዲዘረጉ የሚያስገድደውን ዓለምአቀፉ የትምባሆ ቁጥጥር ኮንቬንሽን ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ሊጸድቅ ነው፡፡

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ፓርላማው እ.ኤ.አ በ2003 በጄኔቭ የወጣው ኣለምአቀፍ የጤና ድርጅት የትምባሆ ቁጥጥር ኢትዮጽያ ፈራሚ አገር የነበረች ሲሆን ይህንን ለማጽደቅ ረቂቅ ሕግ በዛሬው ዕለት ለፓርላማው ቀርቦለት በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በሃላ ለሚመለከተው ኮሚቴ መርቶታል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ በኢትዮጽያ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል 8በመቶ ያህሉ የትምባሆ ምርቶችን እንደሚጠቀሙ ጥናቶችን ጠቅሶ አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪም ...

Read More »

በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ አባላት በእስር ቤት ስቃይ እንደተፈጸመባቸው ገለጹ

ታህሳስ ፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስነልቦናዊ እና አካላዊ ስቃይ አድርሰውብናል የሚሉት በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ የደረሱባቸውን በደሎች ዘርዝርው አቅርበዋል።  ” ከአስራ አራት ሰአት በላይ ያለ እረፍት ቀጥ ብለን እንድንቆም በማድረግ፣ ጀርባችን ሰንበር እስኪያወጣ እና እስኪገሸለጥ ራቁታችንን በሽቦ በመግረፍ፣ በሰንሰለት በማሰር እና አይናችንን በጨርቅ በመሸፈን የውስጥ እግራችን ...

Read More »

በቀብሪ ቤያህ እስር ቤት ውስጥ የሞቱ ሰዎች የሉም ሲል የክልሉ ፖሊስ አዛዥ አስተባበሉ

ታህሳስ ፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- የክልሉ ጽህፈት ቤት ፖሊስ አዛዥ  ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ በምትገኘዋ ቀብሪበያህ እስር ቤት ውስጥ የሞቱ ሰዎች ስለመኖራቸው ሪፖርት እንዳልደረሰቻው ገልጸዋል። አዛዡ እንዳሉት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሽብረተኞችን በተመለከተ ከፌደራል መንገስቱ የጸረ ሽብር ግብረሀይል ጋር በጋራ የሚሰሩ በመሆኑ፣ በዚሁ ወንጀል ተጠርጥረው የሚያዙ ካሉ በጋራ የሚታይ ጉዳይ ይሆናል ሲሉ አክለዋል በጅጅጋ የተከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ የአንድ ለአምስት አደረጃጀትን ወደ ቤተሰብ አወረደ

ታህሳስ ፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ በትምህርት ቤቶች ፣ በአርሶ አደሩና በከተማው ነዋሪዎች ላይ  ሲዘረጋ የቆየውን የአንድ ለአምስት አደረጃጀት በቤተሰብ ደረጃ ለማዋቀር የተለያዩ ደብደባዎችን እየበተነ ነው። የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለወረዳ 02 የቤተሰብ አባላት ባዘጋጀው የቤተሰብ ማቋቋሚያ ቅጽ ላይ የቤተሰብ ፖሊስ መመስረት ያስፈለገበት ዋና ምክንያት ” በቤተሰብዎ መካከል ለሚፈጠሩ የጸጥታ ...

Read More »

በአዳማ ከ25 ሺ ያላነሰ ህዝብ በቤት መፍረስ ምክንያት መንገድ ላይ መውደቁ ተገለጸ

ታህሳስ ፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- መንግስት በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል ያላቸውን በመልካ አባገዳ አካባቢ የሚገኙ ቤቶችን ካለፈው ቅዳሜ ሌሊት ጀምሮ ህዝቡ ቤቱ ውስጥ እንዳለ ማፍረሳቸው ታውቋል። በርካታ ቤተሰቦች መንገድ ላይ መውደቃቸውን ለኢሳት የገለጹት አንድ መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪ፣  የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ቤቶች በፈቃዳችን እንደፈረሱ አድርገው የሚያቀርቡት ዘገባ ሀሰት ነው ብለዋል። የሁለት  ልጆች እናት የሆኑት ግለሰብ በበኩላቸው ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማስወጣት የሚደረግ እንቅስቃሴ የለም ተባለ

ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-  በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ በአገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የደህንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ ቢሆንም መንግስት እስካሁን  እርምጃ እየወሰደ አለመሆኑ ታወቀ። የኢሳት የጁባ ወኪል እንደገለጹት አብዛኛው አገሮች ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው ። ኬንያና ኡጋንዳ አውቶቡሶችን በመላክ ፣ አሜሪካና እንግሊዝ ደግሞ ወታደራዊ አውሮፕላኖችን በመላክ ዜጎቻቻውን እያወጡ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን ጁባ ...

Read More »

ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከፍትህ አካላት ትብብር አጣሁ አለ

ታህሳስ ፲( አስር )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የጸረ ሙስና ኮሚሽን ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን ስራዎች የሚገልጽ ” የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከትናንት እስከ ዛሬ ” በሚል ርእስ አንድ ጽሁፍ አዘጋጅቶ አውጥቷል። ዘጋቢያችን እንደገለጸው በተሻሻለው  የፀረ-ሙስና አዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀፅ 29 መሰረት በሙስና ወንጀል ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ በሙስና ወንጀል የተገኘ ተመጣጣኝ ንብረት እንዲወረስ ፍርድ ቤት ውሳኔ ይሰጣል ቢልም ፍርድ በቶች ...

Read More »