.የኢሳት አማርኛ ዜና

በደቡብ እና ምስራቅ ኢትዮጵያ አሰቃቂ ረሀብ መከሰቱ ተዘገበ

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በመጥቀስ እንደዘገቡት በደቡብ እና ምስራቅ ኢትዮጵያ አስከፊ ረሀብ መከሰቱን ተከትሎ የህዝቡ ህልውና አደጋ ውስጥ ወድቋል። የሲኤን ቢሲ ዘጋቢ እንደገለጸው ችግሩን ለመቅረፍ እስከ 100 ሚሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ ያስፈልጋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የያዘው የምግብ ክምችት ማለቁንም በዘገባው ተገልጿል። እንደ ሲኤን ቢሲ ዘገባ በአፍሪካ ወደ 14 ሚሊዮን የሚጠጋ ...

Read More »

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታሳሪ ቤተሰቦች፣ የሚዲያ ባለሞያዎችና የውጭ አገራት ዲፕሎማቶች  በተገኙበት በተካሄደው ችሎት  የታሳሪ ጠበቆች የምስክሮቻቸውን አድራሻ አሟልተው አለማቅረባቸው በፍርድ ቤቱ ተገልጿል። ጠበቆቹ የምስክሮችን ስም በፍጥነት ለማስታወቅ ያልቻሉት ጂሃዳዊ ሐረካት ፊልም ለህዝብ መለቀቁን ተከትሎ በምስክሮች ላይ ፍርሀት በማደሩና የተለያዩ አካላት ስለሚያስፈራሯቸው ለደህንነታቸው በመስጋታቸው መሆኑን እንዲሁም የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃዎች ለማቅረብ ደግሞ ተጨማሪ ጊዜ የሚያስፈልግ መሆኑን ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦን ኢህአዴግን በመድብለ ፓርቲ ስም ለርጅም ጊዜ እንዲሄድ ማድረግ እንደሚገባ ገለጹ

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሚዲያ ዝግ በመሆን ለኢህአዴግ ካድሬዎችና ሹሞች በተዘጋጀው ውይይት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምኦን  በኢትዮጵያ በልማታዊ አጀንዳ የሚወከለው ኢህአዴግ ብቻ ነው ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች ፓርቲዎች ወይ ይህንን የሚጻረሩ ናቸው፣ ወይም ትርጉም የሌላቸው ናቸው ብለዋል።  ኢህአዴግ ለረጅም ጊዜ  በስልጣን ላይ ለማስቀጠል በመድብለ ፓርቲ ስም ይዞ መጓዝ እንደሚጠቅም አቶ በረከት ተናግረዋል። ...

Read More »

ሁለት የኬንያ ፖሊሶች ከኦጋዴን ነጻ አውጭ ባለስልጣናት ጠለፋ ጋር በተያያዘ ታሰሩ

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ መንግስት ጋባዥነት ከኢህአዴግ መንግስት ጋር ድርድር ለማድረግ በናይሮቢ የተገኙት ሁለቱ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት አመራሮች አቶ ሱሉብ አህመድና አቶ አሊ ሁሴን ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ መወሰዳቸውን የኬንያ መንግስት ባስታወቀ ማግስት፣ ሁለት ለኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ተቀጥረው ይሰሩ ነበር የተባሉ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ባለሰልጣኖቹ ለምሳ ተጋብዘው በመጓዝ ላይ እንዳሉ ቆመው ይጠብቋቸው በነበሩ ...

Read More »

በቦዲና በኮንሶ ብሄረሰቦች መካከል በተነሳው ግጭት የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግጭቱ የተከሰተው ባለፈው ሳምንት ሲሆን፣ ለግጭቱ መነሻ የሆነውም ኮንሶዎች ባጋጠማቸው የመሬት እጥረት ሳቢያ ወደ ቦዲዮች አካባቢ ሄደው በመስፈራቸው መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ይገልጻሉ። በግጭቱ ከሁለቱም ወገኖች 4 ሰዎች ሲሞቱ፣ 3 ኮንሶዎች እና አንድ ፖሊስ ቆስለዋል። 72 ቤቶችም እንዲሁ ተቃጥለዋል። ከዚህ በፊት ሁለቱ ብሄረሰቦች በተደጋጋሚ ሲጋጩ ቆይተዋል። ቀደም ሲል መንግስት የኮንሶ ሰፋሪዎችን ወደ ...

Read More »

በርካታ የአዲስ አበባ ቤት ተመዝጋቢዎች ገንዘባቸውን ከባንክ እያወጡ ነው

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማዎቅ እንደተቻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚታየውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር በዘላቂነት ለማቃለል በሚል ከዚህ በፊት ከነበረው የ 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ልማት ፕሮግራም በተጨማሪ በአማራጭ የ 10/90 አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለመለስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው በ40/60 የቁጠባ ቤት ፕሮግራም መቅረጹን ተከትሎ እስከ ...

Read More »

ብኢኮ ለሙስና የተጋለጠ ድርጅት መሆኑን የጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀኔራል ክንፈ ዳኛው ስራ አስኪያጅነት የሚመራው በስሩ ከ13 በላይ ኩባንያዎችን ዬያዘውና በብዙ ቢሊዮን ብር ካፒታል የተቋቋመው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወይም ብኢኮ አሰራር ግለጽነት የጎደለው መሆኑን የጸረ ሙስና ኮሚሽን ባወጣው የ6 ወራት ሪፖርት ገልጿል። ብኢኮ ከተቋቋመበት ከ1995 ዓም ጀምሮ አሰራሩ ለሙስና በር የሚከፍት መሆኑ በተደጋጋሚ በኢሳት ሲዘገብ ቆይቷል። በጥቂት የህወሃት ጄኔራሎች በሚመራው ...

Read More »

የባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የጋዜጠኞችንና የሚዲያ ነፃነትን ገፏል ሲሉ ጋዜጠኞች ተናገሩ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚኒስትሮች በሚመራው የጋዜጠኞች ስልጠና ላይ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ጣልቃ ገብነት የጋዜጠኞችን እና የሚዲያውን ነፃነት የገፈፈ መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡ ባህርዳር ከተማ በማካሄድ ላይ ባለው በዚህ የጋዜጠኞች ስልጠና ላይ ” የፕሬስ ነፃነት በሀገሪቱ ሊኖር ባለመቻሉ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ጋዜጠኞች ሳይቀር ተሸማቀው እንዲሰሩ እየተደረገ ያለው የአስራር ስርዓት እስከ መቼ ፍፃሜ ያገኛል?” ...

Read More »

ኔልሰን ማንዴላ 4 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት እንደነበራቸው ተዘገበ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባወጣው ዘገባ እውቁ የነጻነት ታጋይና በቅርቡ ከዚህ አለም የተለዩት ኔልሰን ማንዴላ ሀብቱን ያፈሩት በጆሀንስበርግ እና በኬፕ ታውን ከነበራቸው ቤት ሽያጭ እንዲሁም ከመጽሃፋቸው ከተገኘ ገቢ ነው። ማንዴላ ከእርሳቸው ጋር ሲሰሩ ለነበሩት ለእያንዳንዳቸው 50 ሺ የደቡብ አፍሪካ ገንዘብ እንዲሁም እርሳቸው የተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች 100 ሺ ራንድ እንዲሰጣቸው ተናዘዋል። ለአራት የትምህርት ተቋማትም ለእያንዳንዳቸው ...

Read More »

የአማራው ክልል መሪ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቁ

ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን “የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል” በማለት፣ ለብአዴን ነባርና አዳዲስ ካድሬዎች ተናግረዋል። ካድሬዎቹ “የአማራው ህዝብ ለምን ይሰደዳል? ለምን በእየክልሉ ጥቃት ይደርስበታል? አማራውን ከጥቃት ለመከላከል ለምን ሙከራ አይደረግም በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን፣ ም/ል ...

Read More »