ሁለት የኬንያ ፖሊሶች ከኦጋዴን ነጻ አውጭ ባለስልጣናት ጠለፋ ጋር በተያያዘ ታሰሩ

ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ መንግስት ጋባዥነት ከኢህአዴግ መንግስት ጋር ድርድር ለማድረግ በናይሮቢ የተገኙት ሁለቱ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት አመራሮች አቶ ሱሉብ አህመድና አቶ አሊ ሁሴን ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ መወሰዳቸውን የኬንያ መንግስት ባስታወቀ ማግስት፣ ሁለት ለኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ተቀጥረው ይሰሩ ነበር የተባሉ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ባለሰልጣኖቹ ለምሳ ተጋብዘው በመጓዝ ላይ እንዳሉ ቆመው ይጠብቋቸው በነበሩ የኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ተጠልፈው ተወስደዋል። የኬንያ ፖሊሶች ከኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ጋር በመተባበር ሰዎቹ እንዲጠለፉ በማድረጋቸው የተለያዩ ክሶች እንደሚመሰረትባቸው ዘገባው አመልክቷል። የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊት በሁለቱ ሃይሎች መካከል የሚካሄደውን ድርድር ያሰናክለዋል ተብሎአል።